Saturday, 24 November 2018 13:06

“ይቺ ናት ሀገሬ” የኪነ ጥበብ ድግስ ነገ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን “ይህቺ ናት ሀገሬ” የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት ነገ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ በምሽቱ የአገርን አንድነት፣ ፍቅርና መተሳሰብ የሚሰብኩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ምስክር ጌታነው ገልጿል፡፡ በዝግጅቱ ላይ መጋቤ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ኡስታስ ሀሰን ታጁ፣ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚና ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፣ ገጣሚና ተዋናይ ተፈሪ አለሙና ገጣሚና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሃይለኢየሱስ ግጥሞችና ወጐች ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ የባህል ሙዚቃና ውዝዋዜ ዝግጅቱን እንደሚያደምቁት ተጠቁሟል፡፡ 100 ብር የመግቢያ ዋጋ የተተመነለት ሲሆን የመግቢያ ትኬቶቹ በጃፋር መፃህፍት መደብር፣ በዮናስ መፃህፍት መደብር፣ በጣይቱ ሆቴል፣ በሳሚ ካፌና ሬስቶራንት፣ በዓይናለም መፅሐፍት መደብር እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

Read 1022 times