Sunday, 16 December 2018 00:00

ሞዛምቢክ ሳይሰሩ በሚከፈላቸው 30 ሺህ ሰራተኞች 250 ሚ. ዶላር አጥታለች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የሞዛምቢክ መንግስት በስራ ገበታቸው ላይ የሌሉና ሳይሰሩ ደመወዝ ሲከፈላቸው የኖሩ 30 ሺህ ሰራተኞች መኖራቸውን በምርመራ ማረጋገጡንና ክፍያቸው እንዲቋረጥ ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ይፋ ያደረገውን መረጃ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ የሞዛምቢክ መንግስት ባለፉት ሁለት አመታት ጊዜ ውስጥ ለእነዚህ የምናብ ሰራተኞች በድምሩ ከ250 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከፍሏል፡፡
የሞዛምቢክ መንግስት ረጅም ምርመራና ክትትል በማድረግ በሞት በመለየታቸው ወይም በስራ ገበታቸው ላይ ሳይኖሩ የሚከፈላቸውን እነዚህን ሰራተኞች ከደመወዝ መክፈያ ሰነዱ ላይ መሰረዙን ተከትሎ የአገሪቱ የመንግስት ሰራተኞች ቁጥር ወደ 318 ሺህ ዝቅ ማለቱንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
ከአገሪቱ አጠቃላይ በጀት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ እንደሚውል የጠቆመው ዘገባው፣ አገሪቱ ባለፉት ሁለት አመታት በከፍተኛ የፋይናንስ እጥረት ችግር ውስጥ ተዘፍቃ እንደቆየችም ገልጧል፡፡
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባለፈው አመት ባወጣው አለማቀፍ የሙስና ደረጃ ሪፖርት ውስጥ ሞዛምቢክ ከ180 አገራት መካከል በሙስና በ153ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

Read 1208 times