Sunday, 03 March 2019 00:00

“ነብይዤሮ” ቴአትር ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)


በእውቁ ናይጄሪያዊ ደራሲና የመጀመሪያ የኖቤል ተሸላሚው ዎሌ ሶይንካ ከ55 ዓመት በፊት የተፃፈውና በአርቲስተ ፈለቀ አበበ የማርውሃ ተተርጉሞ በረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ የተዘጋጀው “ነብይ ዤሮ” ቴአትር ባለፈው ሐሙስ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ተመረቀ፡፡የ2፡20 ሰዓት ርዝመት ያለው ቴአትሩ በዋናነት ራሱን የሀይማኖት መምህርና ነብይ አድርጎ በመቅረብ ሰዎችን በስሩ የሚያንበረከክክና ያልሆነውንና የማያውቀውን በማስተማር በሚያታልል ነብይ
ህይወት ላይ ያጠነጥናል፡፡ሙዚቃዊ ድራማ ዘውግ በተዘጋጀው በዚህ ቴአትር ላይ አርቲስቶቹ ደበበ እሸቱ፣ ፈለቀ የማርውሃ አበበ፣ አስቴር ዓለማየሁ፣ አስታውሺኝ
በነጋ፣ ማስረሻ ገ/ማሪያም (ቤቢ)፣ ቃል ኪዳን አበራና ሌሎችም ከ30 በላይ አጃቢ ተዋንያን የተሳተፉበት ሲሆን ከመጋቢት 1 ቀን 2011 ጀምሮ ዘወትር እሁድ ከ8፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ ለእይታ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡



Read 4663 times