Saturday, 10 September 2011 12:03

የዓለማችን አንኳር ክስተቶች በ2003

Written by  ጥላሁን አክሊሉ
Rate this item
(2 votes)

ባገባደድነው የ2003 ዓመት ዓለማችን የተለያዩ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አሳዛኝ፣ አስደንጋጭ፣ አስገራሚ እና አሰቃቂ ነገሮች ተፈመውባታል፡፡     ከሁለት ቀን በኋላ አምና ብለን በምንጠራው ዓመት፤ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ስደት፣ ረሃብ፣ በስልጣን መባለግ፣ የታዋቂ ሰዎች ሕልፈት፣ የተፈጥሮ አደጋ እንዲሁም የበርካታ ጦርነቶችና ግጭቶች የትእይንት ማዕከል በመሆን አልፏል፡፡ እኛም ለዛሬ አንኳር  የሆኑት ክስተቶች ለመቃኘት እንሞክራለን፡፡
የጃፓን ርዕደ መሬት

በ2003 ከተከሰቱት አስደንጋጭና አሳዛኝ ሁነቶች ውስጥ በጃፓን የደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ዋነኛው ነበር፡፡ በአገሪቱ ሰሜን ምስራቅ ክፍል በሬክተር ስኬል ዘጠኝ በሚደርስ የመሬት መንቀጥቀጥ ከተመታ በኋላ ከ10 ሜትር ከፍታ በላይ የሆነ የሱናሜ ማዕበል ተከስቷል፡፡ በጃፓን የደረሰው አደጋ 27 ሺህ ጃፓናዊያንን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ በሰዓት 500 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ያለው የሱናሜ ማዕበል በፈጠረው ጐርፍ የተጠቃው የፉኩሺማ የኒውክሊየር የሃይል ማመንጫ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የኒውክሊየር ማብለያ ላይ አደጋ ደርሷል፡፡
©­N ከተፈጥሮ አደጋው ገና ሳታገግም አስፈሪው የራዲዮ አክቲቭ ጨረር ከጣቢያው አፈትልኮ በመውጣት ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሮ ነበር፡፡ በተለይ የጨረሩ ወደ ውቅያኖስ መግባት ሁኔታውን የበለጠ አወሳስቦት እንደነበረ አይዘነጋም፡፡
ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አይታው ወደማታውቀው ማህበራዊ ምስቅልቅል ውስጥ ገብታ የነበረ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጐቿም የውሃ፣ የኤሌክትሪክና የቤት ችግር ገጥሟቸው ነበር፡፡ ሀገሪቱም 100 ሺህ ወታደሮች የምግብ፣ የውሃ እና መድሃኒት እደላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን በፍርስራሽ ስር ያሉ እና በሕይወት የሚገኙ ዜጐቿን በመታደግ ስራ በማሰማራትም ከ450 ሺህ በላይ ዜጐቿን ከቦታው የማስወጣት ስራም ሰርታለች፡፡
በፉኩሺማ ኒውክለር ጣቢያ አካባቢ የሚወጣው ጨረር መጠን በሰዓት 400 ሚሊ ሲሊቨርት (የራዲዮ አክቲቭ ጨረር መለኪያ) ደርሶ ነበር፡፡ ይህም አንድ የኒውክሊየር ኢንዱስትሪ በዓመት ከሚለቀው በ20 እጥፍ የሚበልጥ ነበር፡፡ ከጃፓን አፈትልኮ በወጣው የራዲዮ አክቲቭ ጨረር ፍርሃት የተነሳ በርካታ የዓለማችን አገሮች የኒውክሊየር ጣቢያዎቻቸው ላይ ጥንቃቄ ለማድረግ ተገደው ነበር፡፡ በሌላም በኩል የራዲዮ አክቲቭ ጨረር ንክኪ ያላቸው ምግቦች በጃፓን በመከሰቱ ከቶኪዮ አንስቶ እስከ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጀርመን፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ቻይና እና ሌሎች የጃፓን ጐረቤት አገሮች ላይ ስጋት ፈጥሮ ነበር፡፡ በርካታ አገራትም የጃፓንን ምግቦች ላለማስገባት እገዳ አድርገው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
የአሜሪካንን ነፍስ ያስጨነቀው ዊክሊክስ
ባገባደድነው ዓመት ላይ መላውን ዓለም ካነጋገሩ አሰገራሚ ክስተቶች ውስጥ ዊክሊክስ በተባለው ድረገ የወጡ ሚስጥራዊ መረጃዎች ናቸው፡፡ የዊክሊክስ መስራች የሆነው ጁሊያን ፖል አሳንጌ ራሱን እንደ ጋዜጠኛ፣ አሳታሚና የኢንተርኔት አቀንቃኝ (Internet Activist) እንደሚቆጥር ይታወቃል፡፡ ዊክሊክስ በአጠቃላይ ከ250 ሺህ በላይ የአሜሪካንን የዲፕሎማቲክ ሰነዶች ያሰባሰበ ሲሆን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጋልጡ መረጃዎች መልቀቁ ይታወሳል፡፡ አሜሪካም የአሳንጌ ድርጊት እጅግ አደገኛ ነው በማለት ግለሰቡ እንዲያዝ መግለጫ አውጥታ የነበረ ሲሆን፡፡ ከአሜሪካ ውጪም በአውሮፓ፣ በኢስያና በአፍሪካ የሚገኙ ከባድ ሚስጢሮችን ይፋ አድርጓል፡፡ ይሁንና አሳንጌ ስዊዲን ውስጥ ሁለት ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል በሚል ክስ ተመስርቶበት ከተያዘ በኋላ እንደገና በዋስ መለቀቁ የ2003 ትዝታ ነው፡፡
ታላቁ ሰው በወሲብ ቅሌት
በአንድ ወቅት ኒውስዊክ መሔት “Top World Guy” ሲል ያቆለጳጰሳቸው የአይኤምኤፍ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶሚኒክ ስትራስ ከሃን፤ አለም ከገባችበት የገንዘብ ቀውስና የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ያወጧታል ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው ሰው እንደሆኑ ገልፃ ነበር፡፡ ሆኖም በኒዮርክ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ የምትሰራ የዳት ሰራተኛ አስገድደው ለመድፈር ሞክረዋል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በዚሁ በ2003 ዓ.ም ነበር፡፡ ጉዳያቸውን ሲከታተል የነበረው የኒዮርክ ፍርድ ቤትም፤ የወሲብ ትንኮሳ ተፈሞበታል የተባለችው ወጣት ለፍርድ ቤቱ በሰጠችው የተምታታ ንግግር ክሱን ውድቅ አድርጐ በነፃ ለቋቸዋል፡፡ ስትራስ ከሃን በቀጣዩ ዓመት በፈረንሳይ በሚካሄደው ምርጫ የመወዳደር እቅድ የነበረችው ሲሆን በወሲብ ቅሌት ከተከሰሱ በኋላ እቅዳቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል፡፡
የምግብ ዋጋ ንረት
ባጠናቀቅነው ዓመት የዓለማችን አሳሳቢ ጉዳይ ከነበሩት ውስጥ በዓለም ዙሪያ የተከሰተው የምግብ ዋጋ መናር ነበር፡፡ Foreign Policy የተባለው መሔት በግንቦት ወር እትሙ፤ “The New Geopolitics of Food” በሚል ርእስ ባስነበበው ሁፍ፤ በ21ኛው ክ/ዘመን ዓለማችን አዲስ የምግብ ጦርነት ውስጥ ገብታለች ብሏል፡፡ የሁፍ አቀራቢ ሌስተር ብራውን እንዳለው፤ ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ማዳጋስካር፣ ከቶኪዮ እስከ ሪዮ ደጄኔሮ ድረስ አለም በምግብ ዋጋ መናር እየተናጠች ነው ብሏል፡፡ “We come to the New Food Economic 2011” በሚል ርዕስ የቀረበው ሁፍ እንዲሁ በዓለም ላይ የምግብ ዋጋ ከሚጠበቀው በላይ መናሩን ጠቅሶ ነበር፡፡ የምግብ ዋጋ መናር በሰሜን አፍሪካ አገራት የሚገኙ ጨቋኝ መንግስታት ከሥልጣን መንበራቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የቢንላደን መገደል
ቀድሞ የአሜሪካ ወዳጅ የነበረው ኋላ ላይ ግን አሜሪካ በምትከተለው የውጭ ፖሊሲዋ፣ በተለይም ፍልስጤማዊያን ላይ ጫና በማሳደር ለእስራኤል በምታደርገው የተለየ ድጋፍ ተቃውሞውን የጀመረው ቢንላደን፤ እ.ኤ.አ በ1998 አልቃይዳን ካቋቋመ በኋላ በርካታ የሽብር ድርጊቶችን ፈሟል፡፡ በተለይም በመስከረም 2001 በኒዮርክ መንታ ሕንፃዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ከ3000 በላይ ዜጐችን ጨርሷል፡፡ አሜሪካም ከቶራ ቦራ እስከ ፓኪስታን ድንበር ለድፍን 10 ዓመታት ስትፈልገው ከቆየች በኋላ ባለፈው ሚያዚያ ወር ፓኪስታን ውስጥ በልዩ ኮማንዶዎቿ ልትገድለው ችላለች፡፡
168 ዓመት የቆየ ጋዜጣ መዘጋት
በዓለም አንጋፋ የነበረው “News of the world” የተባለው ታዋቂ ጋዜጣ የተዘጋው በዚሁ ባገባደድነው ዓመት ነው፡፡ ጋዜጣው በተደጋጋሚ የታዋቂ ሰዎችን፣ የባለስልጣናትን፣ የአርቲስቶችን እንዲሁም መንግስታዊ መረጃዎችን በስልክ በመጥለፍ በዜና እንደሚያሰራጭ የተደረሰበት ሲሆን፣ የጋዜጣው አዘጋጆችም ታስረዋል፡፡ የጋዜጣው ባለቤትና ሚሊዬነሩ ሩፐርት ሙድሮክ ለተፈፀመው ክስተት ከፍተኛ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ሩፐርት ሙድሮክ ከጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩንና ከሌሎችም ታዋቁ ሰዎች ጋር የጠበቀ ወዳጅነት የነበራቸው በመሆኑ ጉዳዩ ሁሉንም አስደንግጦ አልፏል፡፡
ሎራን ባግቦ
በ2003 አጀብ ከሚያሰኙት ጉዳዮች ውስጥ በኮትዲቩዋር የተፈፀመው ክስተት ሲሆን፣ ኮትዲቩዋርን ለ10 ዓመታት የመሩት ሎረን ባግቦ፣ በህዳር ወር በተካሄደ ምርጫ በተቀናቃኛቸው በአላሳን ዋተራ ከተሸነፉ በኋላ፣ ከሥልጣን አልወርድም በማለታቸው በአገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት፣ ብጥብጥና የፖለቲካ አለመረጋጋት ሰፍኖ ነበር፡፡ በግጭቱ ከ1000 በላይ ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይቮሪያውያን ደግሞ አገራቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡ ሎረን ባግቦ በአላሳን ዋታራ ከተሸነፉ በኋላ፣ በምርጫ መሸነፋቸውን እንዲቀበሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን (ኢኮዋስ)፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ፈረንሣይና ሌሎች ምዕራባዊያን አገሮች ለማግባባት ሞክረው ነበር፡፡
በሚያዚያ ወር መግቢያ ላይ በምድር ቤታቸው ተደብቀው እያሉ መያዛቸው የዓለም አቀፍን ሚዲያ ትኩረት ስቦ ነበር፡፡ አንዳንድ ሚዲያዎች ሎረን ባግቦ በአላሳን ዋታራ ወታደሮች ከተደበቁበት እጃቸውን ተይዘው እንደተራ ወንጀለኛ እየጐተቱ ሲያወጡ በመላው ዓለም አሰራጭተዋል፡፡ ሮይተርስ ሁኔታውን ሲዘግብ፣ የዋተራ ቃል አቀባይ የተናገሩትን በመጥቀስ ነበር፤ “Yes, he has been arrested” ሮይተርስ ጨምሮ እንደገለፀው፣ ባግቦ የተያዙት በዋታራ ወታደሮች ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ የቀድሞ ቅኝ ገዢ በነበረችው በፈረንሳይ ወታደሮችና በሂሊኮፕተር በመታገዝ ጭምር ነው ሲል ዘግቦ ነበር፡፡ AFP ደግሞ ሎረን ባግቦ በጥፊ መመታታቸውን ጠቅሷል፡፡ ሎረን ባግቦ በአጨቃጫቂ ሁኔታ ወደ ስልጣን እንደወጡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሥልጣን ወርደዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን ነፃ መውጣት
ለሦስት አስርት አመታት ነፃነቷን ለማግኘት ስትዋጋ የነበረችው ደቡብ ሱዳን ነፃነቷን ያገኘችው ባገባደድነው ዓመት ነበር፡፡ በ2003 ዓ.ም በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 99 በመቶ ድም በማግኘት ነፃነቷን ለመቀዳጀት ችላለች፡፡
ደቡብ ሱዳን ነፃ አገር ከሆነች በኋላ በ54 አገራት ውስጥ የዲፕሎማቲክ /ቤት ለመክፈት ያቀደች መሆኑንና እስካሁንም ኢትዮጵያን ጨምሮ በ13 አገራት መክፈቷን የደቡብ ሱዳን ቃል አቀባይ ዶ/ር ቤንጃሚን በርናባ አስታውቀዋል፡፡
ቃል አቀባዩ አያይዘውም ደቡብ ሱዳን ከአባይ ተፋሰስ አገሮች ጋር ያለውን ስምምነት በማጤን ከአገሪቱ ጋር ስምምነት እንደምታካሂድ ገልፀዋል፡፡ በሌላም በኩል ደቡብ ሱዳን ለምና ለኢንቨስትመንት ምቹ አገር መሆኗን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፤ የተለያዩ ኢንቨስተሮች በአገሪቷ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ይችሉ ዘንድ በሩ ክፍት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ ደቡብ ሱዳን የተፈጥሮ ሀብትና ነዳጅ ያላት ስትሆን በርካታ አገራት አይናቸውን ወደ አዲሲቷ የአፍሪካ አገር ሱዳን ጥለዋል፡፡
የእንግሊዙ ነውጥ
በእንግሊዝ ማርክ ዱጋን የተባለ ወጣት በፖሊሶች ከተገደለ በኋላ በበርሚንግሃም፣ በሊቨርፑል፣ በማንቸስተር፣ በብሪስቶል እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ከፍተኛ ነውጥ ተከስቷል፡፡ መነሻው የማርክ ዱጋን መገደል ይሁን እንጂ፣ የኑሮ ውድነት፣ ማህበራዊ ዋስትና መቀነስ እና ስራ አጥነት እየተስፋፋ በመምጣቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የአመፁን ድርጊት የፈፀሙት ተቃዋሚዎች፤ መኪኖችንና ሕንፃዎችን በመሰባበራቸው ከእንግሊዝ ፖሊሶች ቁጥጥር ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ በአመፁ 5 የሚሆኑ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ታዳጊ ሕፃን ልጅም በፖሊስ ተገድሏል፡፡ እረፍት ላይ የነበሩት የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት በአስቸኳይ ከእረፍታቸው ተመልሰው የተሰበሰቡ ሲሆን፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን፤ የ..ጋንግስተሮች.. (ወሮበሎች) አመ እንደሆነ ለፓርላማው በመናገር ፖሊስ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸው አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም እንግሊዝ ፀረ-ጋንግ ወጣቶችን በማሰማራት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር አድርጋዋለች፡፡ ራሷን የዲሞክራሲ አቀንቃኝ እንደሆነች በምትገልፀው እንግሊዝ፤ ፖሊሶች የኃይል እርምጃ መውሰዳቸው ለካ እንዲህም አለ! አሰኝቷል፡፡
የአረቡ ዓለም አመ
ባገባደድነው 2003 የተከሰተው አስገራሚና አስደማሚ ክስተት በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ የተፈፀመው ሕዝባዊ አመ ነው፡፡
የአረቡ ዓለም አመ የተጀመረው በቱኒዚያው ወጣት ሲሆን በመንግሥት ላይ ያለውን ተቃውሞ ለመግለ ሲል ራሱን በእሳት አቃጥሎ ከገደለ በኋላ፣ ሕዝባዊ አመ ተቀጣጥሎ ፕሬዝዳንት ቤን አሊን አገር ለቀው እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል፡ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አመፁ ወደ ግብ አምርቶ ለ30 ዓመታት ግብን ተደላድለው ሲመሩ የነበሩትን ሁስኒ ሙባረክን ከስልጣን አውርዷል፡፡ በተለይ በግብ ለ18 ቀንና ሌሊት በታሀሪር አደባባይ የከተሙት ተቃዋሚዎቿ፤ ሙባረክ ካልወረዱ ወደ ቤታቸው እንደማይገቡ ማስታወቃቸው ጥንካሬያቸውን አሳይቷል፡፡
እንዳልተጠበቀ አውሎነፋስ ሳይታሰብ የአረቡን ዓለም ያጥለቀለቀው የዲሞክራሲ ጥያቄ፤ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ባይካድም በአረብ አገራት የፖለቲካ ለውጥ ሊኖር የሚችለው በወጣቶች እንቅሰቃሴ ሳይሆን በእስልምና ኃይሎች ወይም በወታደራዊ ኃይሎች በተወጠነ ኩዴታ ሊሆን እንደሚችል ይታመን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወጣቶች በኢንተርኔት፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በሞባይል ስልክ ተጠቅመው ተራራ የሚያክሉ መሪዎችን ይገረስሳሉ ብሎ የጠበቀ የለም፡፡
አብዛኞች በ1848 በአውሮፓ ከተከሰተው ሕዝባዊ አመ ጋር አመሳስለውታል፡፡ በቱኒዚያና በግብ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመ በመቀጠል በየመን በሶሪያ፣ በሊቢያ፣ በአልጄሪያ፣ በባህሪን እና በሌሎች የአረብ አገራት ተዛምቷል፡፡ በሶሪያ አሁንም በሽር አላሳድን ለማውረድ ሕዝባዊ አመፁ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል፡፡ አሜሪካና ሌሎች ምዕራባዊያን አገራት የሶሪያ መንግስት ከስልጣን እንዲወርድ በተደጋጋሚ አሳስበዋል፡፡ በሶሪያ ከሊቢያ ባልተናነሰ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐች በመንግስት ወታደሮች ተገድለዋል፡፡
ሊቢያን ለ42 ዓመት የመሩት ጋዳፊ፤ ገና ሕዝባዊ አመፁ እንደተቀሰቀሰባቸው ..አይጦችና በአልኮል የሰከሩ.. ብለው በማጣጣል በአውሮፕላን ሳይቀር በሕዝባቸው ላይ የጭካኔ እርምጃ መውሰዳቸው አይዘነጋም፡፡ የጋዳፊ ድርጊት አለም አቀፉን ማህበረሰብ ያስቆጣ ሲሆን፣ ኔቶም ጦሩን ወደ ሊቢያ በመላክ በመንግሥት ጦር ላይ የአውሮፕላን ድብደባ በመፈፀም የጋዳፊን መንግስት አዳክሟል፡፡ የነፃነት ናፋቂ የሆኑት የጋዳፊ ተቃዋሚዎች ላለፉት ስድስት ወራት እልህ አስጨራሽ ውጊያ ካደረጉ በኋላ ዋና ከተማዋን ትሪፖሊን መቆጣጠራቸው ይታወቃል፡፡ ትሪፖሊ ከተያዘ በኋላ የሽግግር ምክር ቤቱ አገሪቷን ማስተዳደር የጀመረ ሲሆን፣ የጋዳፊ ደብዛ ግን አሁንም አልተገኘም፡፡ አነጋጋሪና አስገራሚ የሆኑት ኮ/ሌ መሀመድ ጋዳፊ ጉዳይ በቀጣይ የ2004 ዓመትም የሚተላለፍ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡
መልካም አዲስ አመት!!

 

Read 9575 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:05