Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 09:55

በአዲሱ ጊነስ ባለሪከርድ ሙዚቀኞችና ተዋናዮች በዝተዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት ይፋ በተደረገው የ2012 የዓለም የጊነስ ሪኮርድ መዝገብ፤ ከመዝናኛው ኢንዱስትሪ በርካታ የሙዚቃና የፊልም ባለሙያዎች ባስመዘገቧቸው ሪከርዶች እንደተካተቱ ታወቀ፡፡ በጊኒስ መጽሐፉ ላይ ከሙዚቀኞች ሌዲ ጋጋ፣ ሪሃና፣ አዴሌ፣ ዩ2 እና ሊል ዋይኔ፤ ጀስቲን ቢበር... ከፊልም ተዋናዮች ደግሞ፣ ጆኒ ዲፕና ሳንድራ ሊሎክ በሪኮርዱ መዝገቡ ውስጥ ተካትተዋል፡፡  

ሌዲ ጋጋ፤ እስከ 11.3 ሚሊዮን የትዊተር ተከታታዮች በማፍራት፤ ሊል ዋይኔ ለ64 ጊዜ በአሜሪካ የትኩስ ሙዚቃዎች ደረጃን በአንደኛነት በመምራት፣ ጀስቲን ቢበር በኦንላይን ቪዲዮ እስከ 464 ሺ ተመልካች በማግኘት፤ ዩ2 የሙዚቃ ቡድን በ2 ዓመት ጊዜ በኮንሰርት 539 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማጋበስ፣ ሪሃና በአሜሪካ የሙዚቃ ደረጃ ሰንጠረዥ ለበርካታ ጊዜያት 1ኛ የሆኑ ነጠላ ዜማዎች በመስራት ፣ ቴይለር ስዊፍት በዲጂታል አልበሟ ከፍተኛ ሽያጭ በማስመዝገብ... እንዲሁም አዴሌ በአንድ ዓመት ብቻ በእንግሊዝ ከ3 ሚሊዮን በላይ የአልበሞቿን ቅጂ በመሸጥ በክብረወሰን መዝገቡ ሰፍረዋል፡፡ ከፊልም ተዋናዮች መካከል በአንድ ዓመት ውስጥ በሰራቸው ፊልሞች 75 ሚሊዮን ዶላር የተከፈለው ጆኒ ዲፕና 56 ሚሊዮን ዶላር ያገኘችው ሳንድራ ቡሎ... እንዲሁም፣ የሃሪ ፖተር መጽሐፍት ደራሲ የሆነችው ጄ.ኬ. ሮውሊንግስ የመጀመርያዋ ቢሊዬነር ደራሲ ተብላ በሪከርድ መዝገቡ ተካትተዋል፡፡

Read 3811 times