Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 10:01

ማርቆስ ሳሙኤልሰን ለኢትዮጵያ የገቢ ማሰባሰቢያ ግብዣ አዘጋጀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በፓሪስና በኒውዮርክ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ኢትዮጵያዊው የምግብ ዝግጅት ባለሙያ (chef) ማርቆስ ሳሙኤልሰን ከባለቤቱ ሞዴል ሚያ ሃይሌ ጋር  በመኖሪያ ቤታቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ግብዣ ማድረጉን ዎልስትሪት ጆርናል ዘገበ፡፡ ..ብራንች ፎር ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ.. በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የቁርስና የምሳ ግብዣ (ብራንች)፣ እሰከ 200 ሰዎች የ50 ዶላር ትኬት በመቁረጥ ታድመዋል፡፡ ከእራት ግብዣው የተሰበሰበውን ገቢ በኢትዮጵያ ለሚገኝ አንድ የበጎ አድራጎት ተቋም እንደሚለግስም ታውቋል፡፡ ማርከስ ሳሙኤልሰን በታላቁ የአሜሪካ አየረንሼፍ 8ኛ ውድድር ከሌሎች ዝነኛ ምግብ አብሳዮች ጋር ሊወዳደር መመዝገቡን ኒውዮርክ ዴይሊኒውስ ዘግቧል፡፡
ሞዴል ማያ ሃይሌ የተሰበሰበውን ገቢ ለተመረጠ ተቋም ለማበርከትና ለጉብኝት ከወር በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመጣ ዎልስትሪት ጆርናል ጨምሮ አመልክቷል፡፡

Read 3602 times