Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 10:02

..ኤሊት ሞዴል ሉክ.. ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ይችላል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በኬንያ በተካሄደው ..ኤሊት ሞዴል ሉክ.. ውድድር ላይ የ2009 ሚስ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አሸናፊ ፈትያ አህመድ እና በ2010 ሚስ አርዝ ኢትዮጵያ የተባለችው ራሄል ደበበ ተሳተፉ፡፡ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን በሞዴል ማፈላለጉ ስራ ላይ በዳኝነት ሰርተዋል፡፡ በዓለማችን ትልቁ የሞዴል አፈላላጊ የሆነው ..ኤሊት ሞዴል ሉክ.. ውድድር፣ በኬንያ ሲካሄድ ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሆን ታላላቅ ዲዛይነሮች፤ የፋሽን ባለሙያዎችና የሞዴሊንግ ኩባንያዎች ተሳትፈውበታል፡፡ በውድድሩ ላይ 32 የኬንያ ሞዴሎች ተወዳድረዋል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ የምትሆነው፣ የሞዴሊንግ ስራዎች ኮንትራት እና ሌሎች በምስራቅ አፍሪካ ያሉ ስራዎችን እንደምትሰራ ታውቋል፡፡ በውድድሩ ያሸነፈችው የ15 ዓመቷ ታዳጊ ሚቼል ዳካ ስትሆን ኬንያን በመወከል ከሁለት ሳምንት በኋላ በቻይና በሚደረገው የ..ኤሊት ሞዴል ሉክ.. ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ በድጋሚ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡
በኬንያው የ..ኤሊት ሞዴል ሉክ.. የዳኝነት ተሳትፎ ከነበራቸው ኢትዮጵያውያን አንዷ የሆነችው ሞዴል ፈቲያ አህመድ፣ ተመሳሳይ የሞዴሊንግ ሙያ ስራዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት በኬንያ ካገኘቻቸው አዘጋጆች ጋር ምክክር ማድረጓን ገልፃ፣ አዘጋጆቹም ፍላጎት እንዳላቸው ነግረውኛል ብላለች፡፡

Read 3486 times