በታዋቂው የጉራጊኛ ዜማ ድምፃዊ ደሳለኝ መርሻ የተዜመና ሒታኒያ የተሰኘ አዲስ አልበም ገበያ ላይ ዋለ፡፡
በጉራጌው ማህበረሰብ ባህል፣ የአኗኗር ዘዴ፤ የመስቀልና የአረፋ በዓል አከባበር ላይ መሠረት አድርጐ የተሰራው ይኸው አዲስ አልበም፤ በያዝነው ሳምንት በማሬ ሙዚቃ ቤት አሳታሚነት ገበያ ላይ ውሏል፡፡ አዲሱ አልበም ለድምፃዊው 5ኛ አልበሙ ሲሆን ሐታኒያ የሚለው የጉራጊኛ ቃል ፍቺው እርሷ ነች የሚል እንደሆነ ድምፃዊው ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና