Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 10:14

የአንደኛ ደረጃ መፃሕፍት እጥረት ተባብሷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያ መፃሕፍት ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡ አስተያየታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን የሰጡ ወላጆች በእጥረቱ የልጆቻችን ትምህርት አቀባበል ተጽእጸኖ ውስጥ ወድቋል ብለዋል፡፡ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች በበኩላቸው መፃሕፍቱ የሚሸጡት በጥቂት ቦታ በመሆኑ በወረፋ እየተጉላሉ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

አራት ኪሎ አካባቢ መጽሐፍ ሲገዛ ያገኘነውና ልጁን መካነኢየሱስ ት/ቤት የሚያስተምረው አቶ አሻግሬ ሲሳይ የአንደኛ ክፍል መማሪያ መፃሕፍት ለመግዛት ከአንድ ሰዓት በላይ ወረፋ መጠበቁን ተናግሯል፡፡ ሌሎች ወላጆች በበኩላቸው ከሁለት ሰዓት በላይ ወረፋ ጠብቀው ባለማግኘታቸው ሁለት እና ሦስት ጊዜ ለመመላለስ ጊዜ እና ጉልበት ማባከናቸውን ይናገራሉ፡፡
መፃሕፍቱን የሚያከፋፍለው የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ሥነምግባር መኮንን አቶ ግርማ ረጋሳ በአዲስ አበባ አራት መፃሕፍት ማከፋፈያዎች እንዳሉዋቸውና በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች በተማሪ መታወቂያ በሽሮሜዳ፣ አራት ኪሎ፣ ጉርድሾላ መሳለሚያ መደብሮች መፃፍት እንደሚሸጡ ተናግረዋል፡፡ የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎችንስ ብለን ለጠየቅናቸው ያለን ቅጂ በጣም አነስተኛ በመሆኑ ለግል ትምህርት ቤት መሸጡን አቁመናል፤ ብለውናል፡፡

 

Read 3992 times Last modified on Saturday, 24 September 2011 10:18