በተለያዩ ምክንያቶች ከሙዚቃ ገበያ ርቀው የቆዩት ታላላቅ ሙዚቀኞች የፈረንጆች አዲስ ዓመት (2012) ከመግባቱ በፊት በአዳዲስ አልበሞቻቸው ገበያውን እንደሚያጥለቀልቁ ኤምቲቪ አስታወቀ፡፡ ከአዲሱ የፈረንጆች ዓመት በፊት ባሉት ዋዜማ ወራት ከ28 በላይ አዳዲስ የሙዚቃ አልበሞች በገበያ ላይ እንደሚውሉ የገለፀው ኤምቲቪ፤ ከሚጠበቁ
አልበሞች አር ኬሊ፣ ኬሪ ክላርክሰን፤ ድሬክ፤ ሜሪ ጄ ብሌጅ፣ ብራያን አዳምስ፣ ሱዛን ቦይል ፤ ዩ2፤ ሪሃና፤ የብላክ አይድ ፒስ አዳዲስ ስራዎች እንደሚገኙበት ጠቁሟል፡፡ ብዙ ዘፋኞች በአንድ አልበም በአማካይ 300ሺ ቅጂ ብቻ መሸጣቸው ከገበያ አርቋቸው መቆየቱንም ዘገባው xKlÖ ገልል፡፡