Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 October 2011 12:12

ሲሞን ኮዌል ሌዲ ጋጋ ትደብራለች አለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የቀድሞው የአሜሪካን አይዶል ዳኛና የሙዚቃ ፕሮዲውሰር ሲሞን ኮዌል ..ሌዲ ጋጋ ትደብራለች ማለቱን ዴይሊ ሚረር ዘገበ፡፡ ..ዘ ኤክስ ፋክተር.. በተባለ ፕሮግራሙ ስኬታማ እየሆነ የመጣው የ51 ዓመቱ ሲሞን ኮዌል፤ ሌዲ ጋጋ የዓለማችን ደባሪ ዘፋኝ ብሎ በተቸበት ንግግሩ ኬቲ ፔሪና ቢዮንሴም አይመቹኝም ሲል አጣጥሏል፡፡ ሲሞን ኮዌል የፖፕ ንግስቶቹን እውቀት የሌላቸው ብሏዋቸል፡፡

ከሳምንት በፊት በትዊተር ድረገ ከ11 ሚሊዮን በላይ ተከታታዮችን በማፍራት በጊነስ ቡክ ኦፍ ሬከርድስ ለመመዝገብ የበቃችው ሌዲ ጋጋ፤ በፌስ ቡክ ከ32 ሚሊዮን በላይ ደጋፊዎች በማፍራትም ከመዝናኛው ኢንዱስትሪ የሶሻል ሚዲያ ንግስቶች ግንባር ቀደሟ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ በወጣ ምግባሯ የገነነችው ሌዲ ጋጋ ግራ በሚያጋቡ ፋሽኖቿም እጅግ አነጋገሪ ስትሆን በስጋ የተሰራ ልብስ አድርጋ በግራሚ ሽልማት ከመገኘቷም ባሻገር ከወር በፊት በኤሚቲቪ የሽልማት ስነስርዓት የወንድ ገፀባህርይ ተላብሳ በመታየቷ ጉድ ሎላታል፡፡ ሌዲ ጋጋ የራሷን የወንድ ገፀባህርይ የፈጠረችው ከወር በፊት ለለቀቀችው ..ዩ ኤንድ አይ.. ለተባለ ነጠላ ዜማ የሽፋን ምስል ነበር፡፡ በ2011 በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ገቢ ያገኘችው ሌዲ ጋጋ፤ የዓመት ጠቅላላ ገቢዋ 90 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ፎርብስ መፅሄት ጠቅሶ በመዝናኛው ኢንዱስትሪ የሶሻል ሚዲያ ቀዳሚ ብሏታል፡፡

 

Read 4890 times Last modified on Saturday, 01 October 2011 12:16