Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 08 October 2011 10:01

“ዕጣ ፈለግ” ትያትር ረቡዕ መታየት ይጀምራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለንደን ሊጓዙ አንድ ሌሊት ብቻ የቀራቸው ወጣቶች በመሸኛ ድግሳቸው ላይ የሚገጥማቸውን ፈተና ለመወጣት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያሳየው “ዕጣ ፈለግ” የተሰኘ ትያትር መታየት ሊጀምር ነው፡፡ ትያትሩን የጻፈው ጋዜጠኛ ዘካርያስ ብርሃኑ ሲሆን፤ ረቡዕ ከቀኑ 11 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚጀመረውንና ደራሲው ከታጠቅ ነጋሽ ጋር ያዘጋጁትን ትያትር ሐረገወይን እሸቱ፣ ታጠቅ ነጋሽ፣ መስከረም ኪዳኔ፣ ሀረጓ እንድሪስ፣ ዘካሪያስ ብርሃኑ፣ ወርቅነህ ማሞ እና ጌጤ ታደሰ ይተውኑበታል፡፡

በዳንኤል አርጋው እና ዘካርያስ ብርሃኑ ፕሮዲዩስ ተደርጐ በሚሙ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ትያትር ዘወትር ረቡዕ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ለሕዝብ ይቀርባል፡፡ከጋዜጠኝነቱ ባሻገር በአጫጭር ጭውውቶቹና በተውኔቶቹ የሚታወቀው ዘካርያስ ብርሃኑ ካሁን ቀደም በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ “የተረሳው ዕዳ”፣ በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ደግሞ “ናፋቂዎች” የተሰኙ ትያትሮች ደርሶ ለሕዝብ አቅርቧል፡፡

 

Read 5145 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 10:10

Latest from