Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 October 2011 10:21

ኪፈር ሰዘርላንድ ስለሌላ ዓለም ፍጡራን ይናገራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ኪፈር ሰዘርለንድ የሌላ ዓለም ፍጡር መኖራቸውን እንደሚያምን ለዴይሊ ቴሌግራፍ ተናገረ:: ኪፈር ከፍተኛ ስኬት ባገኘው ”24” ተከታታይ ፊልም ውስጥ ጃክ ባወር የተባለውን መሪ ገፀባህርይ በመወከል ለስምንት ተከታታይ ዓመት ሰርቷል፡፡ ኪፈር በየምሽቱ ወደ ሰማይ አንጋጦ ክዋክብቱን ሲመለከት የሚያስበው በሌላ ዓለም ስላሉ ፍጡራን መሆኑን ሲገልፅ፤ መላው ዩኒቨርስ ሰው ብቻ ነው ያለበት ማለት ያዳግታል ብሏል፡፡

“24”ን በአንድ ፊልም አጠቃልሎ ለመስራት ስለተያዘው ፕሮጀክት  አስተያየቱን የሰጠው ኪፈር፤ ስክሪፕቱን ለማዘጋጀት ብዙ መልፋቱን ገልፆ፤ ለስምንት ዓመት የታየውን የቴሌቭዥን  ፊልም በ2 ሰዓት አጠቃሎ መስራት ቀላል እንዳልሆነ ተናግሯል፡፡ በዜግነቱ ካናዳዊ የሆነውና በእንግሊዝ የተወለደው ኪፈር ሰዘርላንድ፤  ከ70 በላይ ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን ፕሮዱዩሰርና ዲያሬክተርም በመሆን ሰርቷል፡፡ ዘንድሮ “ሜላንኮሊ” በተባለ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም ላይ የተወነው ኪፈር ሰዘርላንድ፤ በአራት ፊልሞች ላይ በፕሮዲዩሰርነት ተሳትፏል ፡፡ “ 24” አንድ ወጥ ፊልም  ሆኖ  ለዕይታ የሚበቃው በመጪው የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንደሆነ ዴይሊ ቴሌግራፍ ጠቁሟል፡፡

 

Read 5052 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 10:22