Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 October 2011 10:33

የአካል ብቃት ማዘውተሪያ ፊልም ተሰርቷል፣ ለምን?

Written by 
Rate this item
(3 votes)

በአዲስ አበባ የአካል ብቃት እንቅስቅሴ የሚደረግባቸው የስፖርት ቤቶች ወይም ጂሞች እየበዙ  ናቸው፡፡  በበቂ ሁኔታ ነው ለማለት ባይቻልም በህብረተሰቡም እየተለመዱ መጥተዋል፡፡ በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎችም ብቅ እያሉ ነው፡፡ በጥሩ ደረጃ እየሰሩ ያሉ የአዲስ አበባ ጂሞች ከ10 አይበልጡም፡፡ ጥሩ ጂሞች የተሟላ የሚባሉት በሚይዟቸው የስፖርት መሳርያዎች ዘመናዊነት፤ በወቅታዊ ቴክኖሎጂና በሳይንስ የተደገፈ የስልጠና መመርያቸው፤ በሚኖራቸው ተገልጋይ ብዛት፤ በባለሙያዎቻቸው ወይም በአሰልጣኞቻቸው የሙያ ብቃትና ደረጃ ይሆናል፡፡

በአዲስ አበባ በጥሩ ደረጃ ላይ እየሰሩ ከሚገኙ ጂሞች ብዙዎቹ በአንድ ጊዜ ከ50 ሰው በላይ የማስተናገድ አቅም ያላቸውም ናቸው፡፡ ላፍቶ ኢንተርፕራይዝ፤ ሸገር ፊትኒስ፤ ላይፍ ስፖርት ጂም፤ ቦዲ ዋይዝ፤ ቦሌ ሮክ፤ ሮክ ቦተም፤ ጎልደን ጂም፤ ፓወር ጂም እና ኬር ፊትነስ በከተማችን ውስጥ የሚገኙ እውቅና ያላቸው ጂሞች ናቸው፡፡ በብዙዎቹ የአካል ብቃት ማዘውተርያዎች ለሚሰሩ የግል አሰልጣኞች የሙያ ክፍያ በሰው ከ1500-3000 ብር ይገመታል፡፡ የጂም ደንበኞች በመደበኛነት ሲሰሩ በሳምንት ከ3-5 ቀን ለ12 ሰአታት ፕሮግራም የሚኖራቸው ሲሆን፤ በየጂሞቹ በአባልነት ተመዝግቦ ለመገልገል ደግሞ በወር ከ400-1700 ብር ይከፈላል፡፡  
ደረጃውን የጠበቀ ጂም የመሮጫ ማሽኖች፤ የማሟሟቂያ ብስክሌቶች፤ በድምፅና በምስል የሚደረጉ ስልጠናዎች በአዝናኝ መንገድ የሚሰጥበት ነው፡፡ የኤሮቢከስ፤ የዮጋና ሌሎች ልምምዶችም ይኖራሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጂሞች ሳውና ባዝና የውሃ ዋና አገልግሎትም ይሰጣሉ፡፡ በጂሞች ያሉ የግል አሰልጣኞች ስፖርተኞችን በተጠና የስልጠና መመርያ፤ ፕሮግራምና የግዜ መጠን ያሰራሉ፡፡ በብቃት ሁኔታ፤ በጤና ጉዳዮች መመርያ የመስጠትና የማማከር አገልግሎትም ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ አሰልጣኞች ለደንበኞቻቸው እንደ አስፈላጊነቱ በተናጠል የልምምድ ስርዓትና የተለያየ እቅድ ነድፈው ሊሰሩም ይችላሉ፡፡ አሰልጣኞች ያላቸውን ብቃት ወይም የስራቸውን ውጤታማነት `bdNb®ÒcW አካላዊ ብቃትና ጤና ላይ በሚታየው ለውጥ የመፈተሽ እድል አላቸው፡፡ ለዚህ ውጤት ግን ስፖርተኞች ለአሰልጣኞች በማንኛውም መመርያና የልምምድ ስርዓት እንደወታደር ታዛዠ ሆነው መስራት ይገባቸዋል፡፡ አሰልጣኞች በስራ እቅዳቸው በስፖርተኞች የልምምድ ብቃት፤ የጊዜ አጠቃቀምና አመጋገብ ላይ ቁጥጥርም ያደርጋሉ፡፡ በአጠቃላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የኑሮ አንድ አካል አድርጎ ህይወትን መምራት በብዙ መልኩ በጣም ጠቃሚ ነገር መሆኑ ምንም የሚያጠያይቅ ነገር አይደለም፡፡ የአካል ብቃትን ማዳበር (physical fitness) ሰዎች የየቀን ተግባራቸውን ያለ ድካም በብቃትና በጥራት ለማከናወን እንዲችሉ የሚያደርግ ሲሆን ከእንቅስቃሴ ማነስ ጋር በተያያዘ ሊመጡ እንደ ከልክ ያለፈ የስብ ክምችት፤ የስኳር በሽታ፤ የደም ግፊት፤ የልብና የደም መዘዋወር ችግር፤ የታችኛው የወገብ በሽታ ያሉ በሽታዎችንም ለመከላከል መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው፡፡  
አምሳሉና የአካል ብቃት
ሙያተኞች
አምሳሉ ፍቃዱ በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት የመጀመርያ ዲግሪውን ከሰራ በኋላ ማስተርሱንም አግኝቷል፡፡ በአካል ብቃት አሰልጣኝነት  በወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን 2ኛ ደረጃ፤ በላይፍ ፊትነስ ተቋም 3ኛ ደረጃ እንዲሁም ከዱባይ በፊትነስ ማኔጅመንት  እውቅና ያለው ከመሆኑም በላይ በኢንተርናሽናል የአካል ብቃት አሰልጣኝነትም ሰርተፍኬት አለው፡፡ አምሳሉ ፍቃዱ በኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን የቴክኒክ (ክፍል) ሰብሳቢና በምክትል ፕሬዝዳንት እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን በስፖርት ማዘውትርያ ስፍራ ማነጀርነት፣ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በመምህርነት ሰርቷል፡፡ በዘመናዊ የአካል ብቃት ባለሙያነት ወይም አሰልጣኝነት ሲሰራ 4 ዓመታት ሆኖታል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአካል ብቃት ማዘውተርያ ስፍራዎች በመዘዋወር በፍሪላንስ ባለሙያነት እየሰራ ነው፡፡ ከደንበኞቹ መካከል ታዋቂ አትሌቶች፤ ከጉዳት ለማገገም የሚሰሩ የእግር ኳስ ተጨዋቾችና ከውድድር ዘመን መጀመር በፊት አንዳንድ ክለቦች በሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ስራ ውስጥም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ክብደት ለመቀነስ፤ በስኳር፤ በጀርባ ህመምና በሌሎች የጤና ችግሮች ሳቢያ ከገጠማቸው የተለያዩ የጤና እክሎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማገገም ለሚፈልጉ ሰዎች በግል አሰልጣኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡ ወጣቱ አምሳሉ ፍቃዱ በአሰልጣኝነቱ በቀን 8 በሳምንት እስከ 21 ደንበኞችን በሙያው እያገለገለ ሲሆን ለጀማሪዎች በቀን የአንድ ሰአት ተኩል እንዲሁም ልምድ ላላቸው በቀን የ1 ሰዓት ስልጠና ይሰጣል፡፡ በኢትዮጵያ የአካል ብቃት አስተማሪነት ስልጠናን የሚሰጡ  ባለሙያዎች በቂ አይደሉም፡፡ በትምህርት ተቋማት በተለያዩ የስፖርትና የሰውነት ማጎልመሻ የስልጠና ዘርፎች ብቁ ባለሙያዎችን የማፍራት ተግባር ብዙም እንዳልዳበረ የሚገልፀው አምሳሉ ይህም በአገራችን የስፖርት እንቅስቃሴ መዳከም (አሉታዊ) ተፅእኖ  እየፈጠረ እና ጤናማና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ እንዳይፈጠር እያደረገ ያለበት ሁኔታ ስላለ ነገሩ ሊታሰብበት እንደሚገባ ያስገነዝባል፡፡ እሱ በተሰማራበት የአካል ብቃት ስልጠና ሙያ ስፔሻላይዝ አድርገው 16 ባለሙያዎች ዘንድሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መመረቃቸው አበረታች ጅምር መሆኑን  ግን ይገልፃል፡፡ ሙያው በዲግሪ ደረጃ መሰጠት አለበት የሚለው አምሳሉ ራሱን የቻለ የስራ መስክ መሆኑን የትምህርት ተቋማት ከተገነዘቡ በሙያው በርካታ ባለሙያዎችን ማፍራትና በርካታ የስራ እድሎችን መፍጠር እንደሚቻል  ገልፆልኛል፡፡
ፊልሙ ምን?nW?
በአሁኑ ወቅት በአገራችን የአካል ብቃት ማዘውተሪያዎች  (gyms) መስፋፋታቸው ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ  ደግሞ ለስራ ፈጠራ የሚያነሳሳ ምክንያት ይሆናል፡፡ በአካል ብቃት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በተለያየ ምክንያት ተገኝተው እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችሉ ደግሞ በቤታቸው ሆነው እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት የሚፈልጉ ሰዎች ወደ ማዘውተሪያ ስፍራ ሄደው ወይም በቤት ውስጥ መስራት ያለባቸው ምን እንደሆነ፤ እንዴት መስራት እንዳለባቸው ግንዛቤ ያላቸው በጣም ጥቂት መሆናቸውን የጠቀሰው አሰልጣኝ አምሳሉ፤ ሰዎች ዘመናዊ መመሪያ እያገኙ በትኩረት ባለመስራታቸው ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማግኘት የሚገባቸውን ጠቀሜታዎችና የተፈለገውን ውጤት ሳያገኙ የሚቀሩበትን ሁኔታ ለማስቀረት ቆርጦ ተነስቷል፡፡ በመሆኑም  በዘርፉ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት እንደ መመሪያ በመሆን የሚያገለግል፤ በተጨማሪም መሰረታዊ የሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም በቤት ውስጥ በተገቢው መልክ ለመስራት ያስችላል ያለውን የአካል ብቃት ማስተማርያ ፊልም በዲቪዲ ሰርቶ ለማሰራጨት ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ በዲቪዲ የተዘጋጀው ይህ ፊልም መሠረታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርህን ይዟል፡፡ በነጻ ክብደት (Free weight) ለሰውነታችን ዋና ዋና ጡንቻዎች (Major muscles) የሚሆኑ እንቅስቃሴãCN\ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሳሪያዎች አጠቃቀም ወቅት ስለሚታዩ የተለመዱ የአጠቃቀም ግድፈቶች ማብራሪያዎችና ስለ ትክክለኛ አጠቃቀማቸው የሚያስረዱ ገለፃዎች፤ ጡንቻን ለማጠንከር የሚሰሩ እንቅስቃሴãCÂ ሌሎች ልምምዶችን የሚያሳይና ስለ ባህላዊ ምግቦች ይዘትና አመጋገብን የተመለከተ ማብራራሪያም እንደሚሰጥበት አምሳሉ የገለው፡፡  
በስድስት ሰዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየታገዘ በባለሙያ ገለፃ የተዘጋጀው ይህ ፊልም በተለያዩ ምእራፎች የተከፋፈለ ነው፡፡ በተባባሪነት አብሮት የሚሰራው ዘሌ ማን ፕሮዳክሽን መሆኑን የጠቀሰው አምሳሉ ፊልሙን ለመስራት ከ90 ሺብር በላይ እንደፈጀ በመግለጽ ዋና ዓለማውም ስራውን በፈርቀዳጅነት በማከናወን ለሁሉም ፆታና እድሜ የሚሆን የስልጠና መመርያና ምክርን ያካተተ ፊልም መስራት እንደሆነ ነው ያብራራው፡፡
እነማን ይጠቀማሉ?  
በአካል ብቃት ማዘውተርያዎች በግል አሰልጣኝነት የሚሰራው አሰልጣኝ አምሳሉ ፍቃዱ በዲቪዲ ስለተዘጋጀው ፊልም መሰረታዊ አላማዎች ሲያብራራ ያስቀደመው ፈርቀዳጅ ለውጥ ለማድረግ መነሳቱን በመግለፅ ነው፡፡
ስለ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ ስፍራራዎች መሰረታዊ የሆነ እውቀት ያስፈልጋል፡፡ በቤት ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወን የሚፈልጉ በምን መልኩ ቢሰሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ ምክር መስጠት ሙያዊ ተግባሩ እንደሆነ አምሳሉ ይናገራል፡፡ ይህንን ፊልም ያዘጋጀበት አንደኛው ምክንያትና ዓላማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ወይንም በማዘውተሪያ ስፍራ ለመጀመር የሚፈልጉ ሰዎችን ለማገዝ እንደሆነ የገለው አምሳሉ በብዛት የሚታዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወኛ መሳሪያዎች (gym machines) የአጠቃቀም ስህተቶችን ለማረምና ትክክለኛውን አሰራራር ለማሳወቅ፤ በየትኛውም ስፍራ ያለአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአሰሪ (fitness trainer) እና በራስ የሚሰሩ እንቅስቃሴãCN ለማለማመድ  እንዲሁም እንዴት ቢሰሩ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ለማስገንዘብ የፊልም ስራውን ተጠቅሞበታል፡፡ የአመጋገብ ባህላችን (diet) እንዴት ቢሆን ጤናችንን መጠበቅ እንደምንችልና የባህላዊ ምግቦችን (local foods) ለጤና ተስማሚ በሆነ መልኩ እንዴት መጠቀም እንደሚቻልም ለማስተማር መሞከሩን ይናገራል፡፡ በፊልሙ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያለ አሰልጣኝ በግል በመኖሪያ ቤታቸው የሚያከናወኑ ግለሰቦች በዋነኛነት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የገለው አምሳሉ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ ማእከላት፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች፤ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የስፖርት ክለቦች፤ አትሌቶች እና የስፖርት ማህበራትም እንዲሁ ፊልሙን ይገላገሉበታል ብሎም ይጠብቃል፡፡

 

Read 6221 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 10:39