Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 October 2011 10:40

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከፍፃሜው ደርሷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2012 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ የመጨረሻው ዙር ጨዋታዎች ዛሬና ነገ በመላው አህጉሪቱ ሲከናወኑ ታላላቅ ቡድኖች ላለመውደቅ የገቡበት አጣብቂኝ  ትኩረት ሳበ፡፡ ምድብ 2በናይጄርያና ጊኒ ትንቅንቅ ብቻ ትኩረት ቢያገኝም እዚህ አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ከማጣሪያው በክብር ለመሰናበት ይጫወታሉ፡፡ በአዲስ አበባ ስታድዬም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከማዳጋስካር ጋር ስታድዬም  ሲጫወት በሰፊ የግብ ልዩነት እንዲያሸንፍ ተጠብቋል፡፡ ቡድኑ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የወዳጅነት ጨዋታውን ከማሊ አድርጎ 1 እኩል አቻ ተለያይቷል፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቤልጅማዊው ቶም ሴንትፌይት በሃላፊነታቸው 6 ወር ያለፋቸው ሲሆን ከማዳጋስካር ጋር ከሚደረገው ጨዋታ በኋላ ኮንትራቱ ያበቃል፡፡

አሰልጣኙ ኮንትራቱ እንዲራዘምላቸው ፌዴሬሽኑን የጠየቁ ሲሆን ውሳኔው ምን እንደሚሆን አልታወቀም፡፡ አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ብሄራዊ ቡድኑን ይዘው እስካሁን 6 ጨዋታ ያደረጉት አሰልጣኙ አንዱንም ሳያሸንፉ መቆየታቸው ብቃታቸውን አጠራጣሪ እንዳደረገው ይገልፃሉ፡፡ ኦኑራ 4 ጨዋታ አሸንፎ ከ10 ወራት ቆይታ በሃላ መባረሩ የሚታወስ ነው፡፡  በኦኑራ አሰልጣኝ ነት ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ጋር በአንታናናሪቮ ከ1 ዓመት በፊት አድርገውት በነበረው የ3ኛ ዙር የማጣርያ ጨዋታ 1ለ0 ማሸነፍ ተችሎ ነበረ፡፡በዛሬ ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች የሚመዘገበው ውጤት ደረጃን ከማሻሻል ውጪ ብዙ ጥቅም የሌለው ሲሆን ለቤልጅማዊው ሴንትፌይት ግን የመጀመርያውን ድል ለማስመዝገብ የሚያነጣጥሩበት ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ1 ዓመት የማጣርያ ጉዞ በ5 ጨዋታዎች 3ቱን ተሸንፋ ፤ አንዱን አቻ ወጥታና አንዱን በማሸነፍ በ4 ነጥብ በምድቡ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ነች፡፡ ቶም ሴንት ፌይት በ2012 ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ባንበቃም ለምን 2013ን አናልምም? ብለው ለሱፐር ስፖርት ተናግረዋል፡፡ የማዳጋስካር ቡድን ለጨዋታው የኦሎምፒክ ስብስቡን እንዳዘጋጀም ለማወቅ ተችሏል፡፡ለ2012 የአፍሪካ ዋንጫ  ለማለፍ በመጨረሻው ዙር ማጣሪያ ላይ የሚታየው ትንቅንቅ የሞት ሽረት ይሆናል፡፡ ከአዘጋጆቹ ጋቦንና ኢኳቶርያል ጊኒና ጊኒ ሌላ ቦትስዋና፤ ኮትዲቯር፤ ቡርኪናፋሶና ሴኔጋል ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ነው፡፡ በማጣርያው የመጨረሻ ዙር ጨዋታዎች ግን 21 ብሄራዊ ቡድኖች ለቀሩት 10 የማለፍ እድሎች የሚፋለሙ ይሆናል፡፡ ያለፉትን ሶስት የአፍሪካ ዋንጫ ድሎችን አከታትላ ያሸነፈችው ግብፅ፤ ባለፈው የዓለም ዋንጫ አፍሪካን ከወከሉ 6 አገራት አንዷ የነበረችው አልጄርያና  የአራት ጊዜ ሻምፒዮኗ ካሜሮን ወድቀዋል፡፡ ጋና ከሜዳ ውጪ ከሱዳን ጋር በምታደርገው ግጥሚያ አቻ ከወጣች የማለፍ እድሏን የምትወስን ሲሆን በምድብ 2 ናይጄርያ ከጊኒ ጋር በአቡጃ በምታደርገው ጨዋታ 1ለ ማሸነፍ ከቻለች ምድቡን በመምራት ማለፏን ታረጋግጣለች፡፡ ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ በካምፓላ ኡጋንዳ ከኬንያ የሚገናኙበት ሲሆን አሸናፊው ምስራቅ አፍሪካን ይወክላል፡፡ ደቡብ አፍሪካ፤ ቱኒዚያና በ2010 የአፍሪካ ዋንጫን አዘጋጅታ የነበረችው አንጎላ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው፡፡ ታላላቆቹ ቡድኖች ከአፍሪካ ዋንጫ መውጣታቸው ማለፋቸውን አስቀድመው ያረጋገጡት ኮትዲቯር፤ ሞሮኮና ሴኔጋል ለሻምፒዮናነት እድሉ ግምት አግኝተዋል፡፡

 

Read 2160 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 10:44