Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 11:32

ፈረሱ ምን ሆኖ ነው እየሳቀ የሚያለቅሰው?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የድሮ (ሴት) እመቤት:- . . . አዎ . . . ፈረስን ሳይሆን ሴቶችን የሚያስቅ ዘመን መጥቷል፡፡ የሴቶች ትንሳኤን በልጆቹ ላይ ማየቱ ደስ አሰኝቶ አስቆታል፡፡ . . . እንግዲህ እስቲ ቆይ . . . ለምን አለቀሰ ነው ያልከኝ?. . .አየህ ነፃነትን ላልተረዳ ሰው ነፃነቱን ብትሰጠውም ምን እንደሚያደርግበት አያውቀውም . . . ልጆቻችን፤ ቤት እንጂ ቤተሰብ የማይፈልጉ፣ ልጅ መውለድ እንጂ እናት መሆን የማይችሉ፣ ዶሮ ወጥ መብላት እንጂ መስራት የሚቀፋቸው፣ . . .ለገላቸው የሚገባውን ክብር የሚነፍጉ . . . ምስኪን የነፃነታቸው እስረኞች መሆናቸው ፈረሱን አስለቅሶታል፤ ብል አልተሳሳትኩም አይደል? ኧረ ኤዲያ እቴ!

ዘመናዊት (ሴት) ቺክ:- ፈረሱ ሳይሆን ፈረሷ ስቃለች . . . አገልግሎቷ እና አቅሟ ከወንዱ ፈረስ እኩል ሳይሆን የተሻለ መሆኗ እየታወቀ ስለመጣ ደስ ብሏት፡፡.. .  
. . . የሚያስለቅሳት:- ይሄንን ነፃነቷን በጉልበት ለመግፈፍ የሚነሣው ማህበረሰብ ነው፡፡ ማህበረሰቡ ራሱ ወንድ ነው፡፡ ፈጣሪ ራሱ በወንድ አምሳል የተሠራ ነው፡፡ ሴቷ ላይ አካል ማጉደሉ፣ መድፈሩ፣ አሲድ መድፋቱ . . . በማህበረሰቡ የመጣ ጥቃት ነው፡፡ ይህ ፈረሷን ያስለቅሳታል፡፡ ሴቷ ፈረስ ስታለቅስ…ወንዱ የማህበረሰብ ፈረስ ይስቃል፡፡
ግራ የገባው ወንድ:- ፈረሱ፤ በእናቱ እና በእህቶቹ መሐል ያለውን ልዩነት አይቶ ነው የሣቀው፡፡ በእመቤት እና በቺክ፣ በእቴጌ እና በሚስ ዩኒቨርሲቲዋ መሐል ያለው የልዩነት ርቀት. . . በጡት ማስያዣ ፎቶ እንዲቀረፅ በተፈጠረው እና ለተወለደው ጨቅላ ወተት ለመስጫ የተፈጠረው ጡት መሀል ያለውን ርቀት ሲያስበው . . . በሳቅ ፈረሰ . . .፡፡ ልዩነቱን ለማቀራረብ ከመሞከር፤ የሚቀጥለውን ዘመን መገመት ይሻላል፤ ብሎ ማሰብ ጀመረና . . . እንባው መጣ፤ የፈረሱ፡፡ . . . ታየው፤ እንደ ጥንቱ ባህል ሚስት በተገላቢጦሽ አባወራ ሆና፤ እሷ ሁለት ሦስት ባል ስታገባ፣ እንደ ጥንቱ የህንድ ባህል ሚስት ስትሞት ባል ከነህይወቱ ከሚስቱ ሬሳ ጋር ሲቃጠል . . . ወይንም ከነህይወቱ መቃብር ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አብሮ ሲቀበር፣ ወይንም ሚስቱ ከደጅ ስትገባ . . . ባል ራት ሰርቶ ስላልጨረሰ ማማሰያውን በአንድ እጅ . . . በሌላው እጁ አይኑን ሸፍኖ ከሚስቱ የሚጠብቀውን ድብደባ በመፍራት ሲያለቅስ፣ ሚስቱ ቁማር ስትጫወት ውላ ሰክራ ቤት ስትመጣ . . . (ያረገዘችውን ልጃቸውን ድራፍት ጠጥታ ስትዘል ገጭታ በመሀፀን ውስጥ እንዳለ አካሉን ጐድታው) ”አስይዤ ስጫወት የነበረው አንተን ነበር” ብላ ለፈረሱ ስትነግረውና አልጋው ላይ ስትጋደም፣ ባል ጫማዋን ለማውለቅ ሲጣደፍ . .. በአይነ ህሊናው ታየውና ፈረሱ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ወንድ ፈረስ ድሮ አያለቅስም ነበር፡፡

 

Read 3515 times Last modified on Saturday, 15 October 2011 11:36