Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 13:05

በ“ስኮቲሽ” ደርቢ 19 እኩል ትኩረት ሳበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ዛሬ በአንፊልድ ከሊቨርፑል የሚያደርጉትን ጨዋታ ከኤልክላሲኮ በላይ ነው ብለው ተናገሩ፡፡ ፈርጊ የሊቨርፑልና የማን ዩናይትድ ጨዋታ የፕሪሚዬር ሊጉ ብቻ ሳይሆን የምንዜም የዓለማችን ምርጥ ደርቢ ብለው ሲናገሩ ምናልባትም የሚመጣጠነው ሁለቱ የስኮትላንድ ክለቦች ሬንጀርስና ሴልቲክ የሚያደርጉት ፍልሚያ ነው በማለትም ተናግረዋል፡፡ የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኞች የስኮትላንድ አገር ዜግነት ግጥሚያውን የስኮቲሽ ፍልሚያ አስብሎታል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ማን ዩናይትድና ሊቨርፑል የተገናኙበትን ጨዋታ በኦልድትራፎርድ ከ75ሺ በላይ ተመልካች ታድሞት የነበረ ሲሆን በዛሬ ጨዋታ የበለጠ ታዳሚ በአንፊልድ ሮድ ሊታደም እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚዬር ሊጉ ሲገናኙ ማን ዩናይትድ 71 ሲያሸንፍ ሊቨርፑል 61 ረትቶ በ50 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል፡፡ ባለፉት ሰባት የሁለቱ ክለቦች ፍጥጫዎች 5 ቀይ ካር መታየታቸው የጨዋታውን ክብደት የሚያሳይ ሲሆን ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ማን ዩናይትድን በገጠመባቸው ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሽንፈት አልገጠመውም፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ሁለቱ ክለቦች በተገናኙበት ወቅት ኦልድ ትራፎርድ ላይ ቤርባቶቭ ለማን ዩናይትድ ሃትሪክ ሲሰራ አንፊልድ ላይ ደግሞ ለለሊቨርፑል ደርክ ካይት ሃትሪክ ማስመዘገቡ ይታወሳል፡፡ማን ዩናይትድ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ፍልሚያ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘው ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ የውድድር ታሪክ እኩል 19 ግዜ ሻምፒዮን በመሆናቸው ነው፡፡ ሁለቱ ክለቦች በእንግሊዝ እግር ኳስ ከፍተኛውን ክብረወሰን መያዛቸው ትንቅንቁን አጋግሎታል፡፡ የዘንድሮው የውድድር ዘመን ሲጀመር ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የሊጉን ሻምፒዮናነት በክለቡ ታሪክ ለ20ኛ ግዜ በማግኘት በእንግሊዝ የክለብ ውድድር የከፍተኛ ውጤት ክብረወሰኑን ለማስመዝገብ እንደሚፈልጉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ በተያያዘ ዜና ሊቨርፑል የብሮድካስቲንግ መብትን በተናጠል ለመደራደር ማሰቡ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 20 ክለቦች በ2013 የሚያበቃውን የ1.4 ቢሊዮን ፓውንድ የቴሌቭዝን ስጭት መብት በየዓመቱ እኩል ሲካፈሉ የቆዩ ሲሆን ይሄው ኮንትራት ሲያበቃ የአንፊልዱ ክለብ ሊቨርፑል የራሱን የብሮድካስቲንግ ውል ተገንጥሎ ለመፈፀም መፈለጉን ሃለፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ ማን ዩናይትድና ሌሎቹ ትልልቅ ክለቦች ይህን የሊቨርፑል አቋም የስፖርቱን የፉክክር መንፈስ ይቀንሰዋል በሚል ላለመደገፍ ይወስናሉ እየተባለ ነው፡፡ ሊቨርፑል የብሮድካስቲንግ መብቱን በራሱ ለማድረግ የፈለገው ከእንግሊዝ ውጭ ክለቡ በዓለም ዙርያ ያለውን ገናናት ወደገንዘብ ለመለወጥ ካለው ፅኑ ፍላጎት መሆኑን ሃላፊዎቹ ይገልፃሉ፡፡

 

Read 2955 times Last modified on Saturday, 15 October 2011 13:07