Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 October 2011 11:03

“ፀሐዩ ንጉሳችን፤ ልማታዊው መንግስታችን”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“የዘመን ተልእኮና የትውልድ ጥያቄዎች” በሚል ርእስ የቀረበው የዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ፅሁፍ፤ የንጉሱንና የደርግን ዘመን እንዲሁም የኢህአዴግን ዘመን በምሳሌነት ጠቃቅሶ ሃሳቡን ሲቋጭ ውይይትን ይጋብዛል። የአፄ ሃይለስላሴ እና የደርግ መንግስታት፤ የታሪክ ተልእኳቸውን እንደፈፀሙና ከተልእኳቸው ውጭ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ከሄግል ፍልስፍና ጋር አያይዘው የጠቀሱት ዶ/ር ዳኛቸው፤ ወደኋላ ተመልሰን ስለመብት ጥያቄ እያነሳን ብናወግዛቸው ትርጉም የለሽ ነው ይላሉ። በተመሳሳይ መንገድ፤ የኢህአዴግ መንግስት ላይ የሚሰነዘሩ ጥያቄዎችም ትርጉም ላይኖራቸው ይችላል ብለዋል - ፀሃፊው።

“የታሪክ ተልእኮ” የተሰኘው የተድበሰበሰ አባባል፤ ግር ስለሚያሰኝ ዘርዘር አድርገን ብናየው ይሻላል። አባባሉ ለአገራችን አዲስ ነው ማለቴ አይደለም። እንዲያውም የተለመደ አባባል ነው - ብዙ የተነገረለትና የተፃፈለት። ዋናው ምንጭ ፈላስፋው ሄግል እንደሆነ የማያውቁ ብዙ የአገራችን ሰዎቸም፤ “ታሪካዊ ሃላፊነት”፤ “ታሪክ የጣለብን አደራ” እየተባለ ሲነገር መስማታቸው አይቀርም። ምንጩን ባናውቀው እንኳ፤ ከአገራችን ፖለቲካና ከህይወታችን ጋር ተሳስሯል። ፍልስፍና (ትክክልም ይሁን ስህተት)፤ እንዲሁ አየር ላይ የሚቀር ሳይሆን፤ ዞሮ ዞሮ ህይወታችንን በበጎም ሆነ በክፉ ይነካል። ለምን? 
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በፍጥነትም ሆነ በሂደት፤ የሰዎች ህይወት የሚመራው በሃሳቦች አማካኝነት ነው - ከፍልስፍና እየተተነተኑና እየተዘረዘሩ የሚመጡ ሃሳቦች። በጭፍን ስሜትና በደፈናው እየተቀበልን የስብእናችንና የባህሪያችን አካል የምናደርጋቸው ሃሳቦች፤ ወይም በሎጂክና በጠራ አእምሮ እየመረመርን የምንመርጣቸው ሃሳቦች ሊሆኑ ይችላሉ። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በእነዚሁ ሃሳቦች ነው፤ ድርጊታችንና ህይወታችንን የምንመራው - ለጥፋትም ሆነ ለልማት።
እና ታዲያ፤ ከሄግል ፍልስፍና ጋር በማያያዝ፤ ዶ/ር ዳኛቸው ያቀረቡትን ሃሳብ እንዴት አያችሁት? “ታሪክ የጣለብኝን አደራ እፈፅማለሁ” እያለ ግፍ የሚሰራ ሁሉ አለፈለት አያስብልም? ዘርዝረን እንየዋ። ዶ/ር ዳኛቸው፤ ለአዲስ አመት በታተመው የአድማስ ጋዜጣ ላይ ባቀረቡት ፅሁፋቸው ለውይይት ጋብዘውን የለ? “የአበሻ ነገር” ሆኖ፤ ለግብዣው ብንዘገይ እንኳ፤ በሩን እንደማይዘጉብን ተስፋ ይዘን እንቅረብ።
የመንግስት ስልጣን ከምን ይመነጫል በሚል ሃሳብ ዙሪያ ፅሁፋቸውን የጀመሩት ዶ/ር ዳኛቸው፤ ቀጠል አድርገው የማኪያቬሊን አስተሳሰብ በአጭሩ ይዳስሳሉ - መንግስታትን የምንዳኝበት የሞራል ሚዛን ምን መሆን በመጠቃቀስ። የፅሁፋቸውንሁለት ሶስተኛውን ያህል ስንጨርስ ነው፤ ዋናውን ርእሰ ጉዳይ በቀጥታ የምናገኘው - “የዘመን ተልእኮ እና የትውልድ ጥያቄ”። ማጣቀሻቸውም ሄግል ነው - ጀርመናዊው የ19ኛው ክፍለዘመን ፈላስፋ። የሄግልን አስተሳሰብ መሰረት አድርገው፤ የአፄ ሃይለስላሴን፤ የደርግንና የኢህአዴግን ዘመን እንዴት መዳኘት እንደሚኖርብን ይገልፃሉ - ዶ/ር ዳኛቸው።
በእርግጥ፤ ዶ/ር ዳኛቸው በዚሁ ጥያቄ ዙሪያ፤ “የሄግል አስተሳሰብ ትክክል ነው” ብለው እንደሚያስቡ ወይም እንደማያስቡ በግልፅ አልፃፉም። ሄግል እንዳለው፤ ከሄግል አኳያ፤ በሄግል አነጋገር... በሚሉ የጥንቃቄ አጀቦች ታጥረው ነው፤ ዶ/ር ዳኛቸው ስለ ንጉሱ፤ ስለ ደርግና ስለ ኢህአዴግ ዘመን የሚናገሩት። የራሳቸውን ሃሳብ በሚገልፅ መንገድ አልፃፉም - ከተወሰኑ ቦታዎች በስተቀር። ለምሳሌ፤ መንግስታት የየራሳቸው ተልእኮ እንዳላቸው ዶ/ር ዳኛቸው የገለፁት፤ “በሄግል አባባል” ከሚል ማጀቢያ ጋር አይደለም። ወደ ዋና ርእሰ ጉዳያቸው ሲገቡ፤ ያሰፈሯቸውን የመጀመሪያ አረፍተነገሮች ተመልከቱ።
“ስለ ዘመን መንፈስ (ተልእኮ) ተጠቃሽ ድርሳን የጻፈው፤ [ታዋቂው የ19ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ጀርመናዊ ፈላስፋ] ቬልሄልም ሄግል ነው” በማለት የፃፉት ዶ/ር ዳኛቸው፤ “እያንዳንዱ መንግሥት የራሱ ተልእኮ አለው” ይላሉ። ይህንንም ለማብራራት ፈላስፋውን ይጠቅሳሉ - እንዲህ በማለት። ...ሄግል እንደሚያብራራው “መንፈስ ለግለሰብም ሆነ ለመንግሥት፤ ወይም ለአንድ የተደራጀ ኃይል፤ ተልእኮ ታሸክመዋለች። ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ ግን ምንም ማድረግ አይችልም”...፡፡
እዚህ ላይ ጥያቄዎች ቢፈጠሩብን አይገርምም። “የታሪክ ተልእኮ” እና “የትውልድ ጥያቄ” የተሰኙትን አባባሎች አይተን በወጉ ትርጉማቸውን ሳናጣጥም፤ “የዘመን ተልእኮ”፤ “የመንፈስ ተልእኮ” የሚባሉ ነገሮችም ተጨምረውብናል። ሄግል፤ ፊሎዞፊ ኦፍ ሂስትሪ በሚል ርእስ ባቀረበው ትምህርት ውስጥ፤ ዋነኛውን ስፍራ ይዞ የምናገኘው “መንፈስ” የሚለው ቃል ነው። ቃሉን በሃይማኖታዊና በተፈጥሯዊ ገፅታው ስንጠቀምበት፤ ትርጉሙ ያምታታ የለ? ሄግልም ቃሉን የሚጠቀምበት በሚያምታታ መንገድ ነው። በአንድ በኩል፤ ተፈጥሯዊ ትርጉም ይሰጠዋል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ሃይማኖታዊ መሰል ትርጉም።
ሄግል፤ ለምሳሌ አለምን በሁለት ይከፍለዋል - ቁሳዊ አለም እና መንፈሳዊ አለም በማለት። ድንጋይ፤ ከዋክብት፤ ፀሃይ፤ ፕላኔት በቁሳዊ አለም ውስጥ ሲፈረጁ፤ ሰዎች ደግሞ በመንፈሳዊ አለም ውስጥ ፈርጇቸዋል - ማሰብ፣ መምረጥ፣ መወሰንና ድርጊት መፈፀም ይችላሉ በማለት። በሌላ አነጋገር፤ ከሰው ተፈጥሮ ጋር በማያያዝ ነው፤ ሄግል “መንፈስ” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው - “የህዝብ መንፈስ”፤ “የአለም መንፈስ”፤ “የዘመን መንፈስ” ወይም በአጭሩ “መንፈስ” እያለ። እነዚህ ሁሉ ሃረጋት ትርጉማቸው አንድ አይነት እንደሆነ ሄግል ቢጠቁምም፤ ያ ትርጉም ምን እንደሆነ በግልፅ አይናገርም።
በጥቅሉ፤ መንፈስ ማለት፤ አለምን የሚመራ፤ በአለም ውስጥ የሚከናወኑና የሚከሰቱ ነገሮችን፤ በአጠቃላይ የታሪክን ሂደት የሚወስን ነገር ነው፤ የሚወስን ሃይል ነው ይላል - ሄግል። ምናልባት፤ የህዝብና የዘመን መንፈስ እያ ሲናገር፤ በየዘመኑ አብዛኛው ሰው የሚያምንበትን ወይም የበላይነት የያዘውን ሃሳብና መርህ ለመጥቀስ ፈልጎ ይሆን? አብዛኛው ሰው የያዘውን ዝንባሌና ባህርይ፤ የአብዛኛው ሰው የሚከተለውን አኗኗር በአጠቃላይ የየዘመኑን ፍልስፍናና ባህል ለመግለፅ አስቦ ይሆን? ፍልስፍናና ባህልኮ፤ ከሰዎች ድርጊትና ከታሪክ ጋር በጣም የተቆራኙ ናቸዋ።
ለምሳሌ፤ በ60ዎቹ አ.ም፤ በአገራችን የበላይነት አግኝተው የነበሩ የኮሙኒዝምና የፋሺዝም ፍልስፍናዎችን እዩ። ለእውነታና ለሳይንስ ክብር የሌለው፤ ለሰው ህይወትና ለግል ነፃነት ዋጋ የማይሰጥ፤ ለብልፅግናና ለኩሩ ስብእናም አድናቆት የሚነፍግ ኋላቀር ባህል በአገራችን ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነም ተመልከቱ።
ታዲያ፤ የአፈናና የእልቂት ፍልስፍናዎች፤ ከኋላቀር ባህል ጋር አብረው በገነኑባት አገር፤ የበርካታ ሰዎች ድርጊት ምን ሊሆን እንደሚችል መተንበይ ይከብዳል? በዚያ ዘመን፤ የግድያ፣ የእስር፣ የስደት፣ የዝርፊያ፣ የድህነትና የረሃብ ዘግናኝ ስርአት መንገሱ አይቀሬ ነበር። ኮሙኒስት ደርግ ባይኖር፤ ኮሙኒስት ኢህአፓ ይኖራል። ኢህአፓ ባይኖር ኮሙኒስት መኢሶን ይኖራል። ፍልሚያው በእነዚሁ ተመሳሳይ አስተሳሰብና አላማ በያዙ ቡድኖች መካከል ስለሆነ፤ ማንም ቢያሸንፍ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው - አይቀሬ አሳዛኝ ውጤት። በእጅጉ ልናወግዛቸውና ልንወቅሳቸው የሚገባውም በዚሁ ምክንያት ነው።
የዚያ ዘመን ምሁራን፤ የአገራችንን ኋላቀር ባህል በስልጡን ባህል ለመቀየር ከመነሳት ይልቅ፤ ለዚህም ትክክለኛ ፍልስፍናን በመምረጥ ከመጣጣር ይልቅ፤ የጥፋትን መንገድ መርጠዋል። ኋላቀሩን ባህል ወደ አሰቃቂ ደረጃ የሚያሸጋግር የአፈናና የእልቂት ፍልስፍናን መምረጣቸው፤ ይህንኑም በተግባር መፈፀማቸው ነው ትልቁ ጥፋታቸው። ፍልስፍናም ሆነ ባህል፤ በሰዎች አቅም ስር ነው - ሰዎች በምርጫ የሚይዙት ወይም የሚጥሉት። ፍልስፍናም ሆነ ባህል፤ ሰው ሰራሽ ነገር ነው - በጎ ወይም ክፉ። የዚያኑ ያህልም፤ ክፉ ወይም በጎ የሆነውን እየመዘንን መዳኘት ይኖርብናል - በተገቢው አድናቆት ወይም ውግዘት።
ፍልስፍናና ባህል፤ ከሰዎች ድርጊትና ከታሪክ ጋር ምን ያህል የተቆራኘ እንደሆነ አያችሁ? ምናልባት ሄግል፤ “የዘመን መንፈስ፤ የታሪክ ሂደትን ይወስናል” እያለ የሚናገረው፤ በየዘመኑ ገንኖ የሚታየውን ፍልስፍናንና ባህልን ለመግለፅ ፈልጎ ይሆን? ቢፈልግ ኖሮ፤ ጥርት አድርጎ መግለፅ አያቅተውም ነበር። ፈላስፋ አይደል!
“መንፈስ”፤ በሄግል አገላለፅ፤ ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ሄግል ይናገራል - ... መንፈስ ማለት፤ የራሱ አላማና እቅድ ያለው፤ ይህንንም የሚመራና የሚያስፈፅም ዘላለማዊ ነገር ነው፤ ሁሉን የሚችል ሃይል ነው። ይህ የህዝብ መንፈስ፤ ወይም የሰዎች መንፈስ፤ የራሱን እቅድና አላማ የሚያስፈፅመው፤ እንደ ቄሳርና ናፖሊዮን በመሳሰሉ ሰዎች ወይም በህዝብ አማካኝነት ነው - ተልእኮ እየሰጠ። ... በእርግጥ ሰዎቹ ተልእኮ እንደተሰጣቸው አያውቁም። የየራሳቸውን ፍላጎቶች ለማሳካት ነው የሚጣጣሩት። ነገር ግን፤ ሳይታወቃቸው የመንፈስን እቅድና አላማ በወኪልነት ይፈፅማሉ። ለምሳሌ ቄሳር፤ ስልጣኑንና ክብሩን ላለማጣት ነው፤ ከተቀናቃኞቹ ጋር የተፋለመው። ነገር ግን፤ እሱ አልታወቀውም እንጂ፤ በፍልሚያው አማካኝነት፤ አዲስ አገር፣ አዲስ የመንግስት አወቃቀርና አዲስ ታሪክ ፈጥሯል - ሳይታወቀው የመንፈስን እቅድ በወኪልነት እየፈፀመ ነበር ...
ሄግል ይቀጥላል - ...በአጠቃላይ፤ አለማችን፤ በመንፈስ የታቀደ ታሪክ በሰዎች አማካኝነት የሚተወንባት ትልቅ መድረክ ነች። ሰዎች የተውኔቱ ተካፋይ እንደሆኑ አያውቁም እንጂ ...። እንዲህ እንዲህ እያለ ይናገራል ሄግል።ለመሆኑ፤ ይሄ ሰዎች የማይወቁትና በወኪልነት የሚያገለግሉት “መንፈስ” ምንድነው? የት ነው ያለው? ሄግል ብዙ ብዙ ይናገራል። ግን፤ ነገሩን ከማብራራት ይልቅ፤ ይብስ የተምታታ እንዲሆን ያደርገዋል። ሁሉም ሰዎች፤ የመንፈስ ተጨባጭ ገፅታዎች እንደሆኑ፤ የመንፈስ ፍፁማዊ መገለጫ ደግሞ መንግስት እንደሆነ የሚናገረው ሄግል፤ የመንፈስን ምንነት በጥቂቱ ለመገንዘብ፤ “ፈጣሪ” ከሚለው ሃይማኖታዊ ሃሳብ ጋር እንድናነፃፅረው ይጠቁመናል። “የመንፈስ አላማና እቅድ” ሲባል ደግሞ፤ “የፈጣሪ እቅድና አላማ” ከሚባለው ሃይማኖታዊ ሃሳብ ጋር ተመሳሳይ ነው ይላል ሄግል።
የሄግል ሃሳብ፤ ግራ የተጋባና የተምታታ ሃሳብ ቢሆንብን አይገርምም። ምክንያቱም የተምታታ ነው። ይልቅስ፤ ከዚህ የተምታታ ሃሳብ በመነሳት፤ ምን ላይ ደረሰ? ዶ/ር ዳኛቸው በፅሁፋቸው እንደጠቀሱት፤ ከሄግል ሃሳቦች የምናገኛቸው የተወሰኑ መደምደሚያዎች አሉ።
1ኛ. ሰዎች፤ በተለይም ቄሳርና ናፖሊዮን የመሳሰሉ ሰዎች፤ እንዲሁም በየጊዜው የሚፈጠሩ ቡድኖችና መንግስታት፤ በመንፈስ የተሰጣቸውን ተልእኮ የሚፈፅሙ ናቸው - ከዚሁ ውጭ ምንም ማድረግ አይችሉም።
የአለማችን ታሪክ በሙሉ፤ ሰዎች እንዲሁ ሳይታወቃቸው ሳይታወቃቸው፤ “መንፈስ” በሚሰጣቸው ተልእኮ የሚፈፅሙት ሂደት ከሆነ፤ ማንም ሰው ለድርጊቱ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም። ሚሊዮኖችን ለእልቂት የዳረገው ሂትለርም ሆነ፤ የአሜሪካን የነፃነት መግለጫ የፃፉት ቶማስ ጃፈርሰን፤ ተመሳሳይ ናቸው እንደማለት ነው። ንጉሱ፤ ደርግ፤ ኢህአዴግ... ያው ተልእኳቸውን ነው የሚፅሙት። “ይህንን ወይም ያንን ጥፋት ሰርተዋል” ብሎ መተቸት ከንቱ ነው። የታሪክን ተልእኮ ሲፈፅሙ፤ ብዙ ሰዎችን ቢገድሉ ወይም ቢያስሩ፤ ብዙ ሰዎችን ቢዘርፉ ወይም ቢያደኸዩ፤ ወደ ውግዘት መሮጥ የለብንም። የታሪክን ተልእኮ የሚፈፅሙ ሰዎች፤ በመንገዳቸው የሚያገኙትን ሁሉ ቢጨፈላልቁ፤ እጅግ ብዙ ንፁሃን ሰዎችን ደፍጥጠው ቢቀጩ አይገርምም፤ በተጠያቂነት መወገዝም የለባቸውም ይላል - ሄግል።
2ኛ. የመንፈስ ዋነኛና ፍፁም መገለጫ መንግስት እንደሆነ የሚገልፀው ሄግል፤ ስነምግባር ማለት ለመንግስት መገዛት እንደሆነ ይገልፃል። እውነተኛው ስነምግባር፤ ከመንግስት የሚጠበቅብህን ግዴታ መፈፀም ነው በማለት በግልፅ ይናገራል። “ያኛው ህግ ጥሩ ነው፤ ይሄኛው መጥፎ ነው”፤ “መንግስት ያኛውን ጥፋት ሰርቷል፤ ይሄኛውን መልካም ነገር አልሰራም” ... እንዲህ እያሉ ማማረጥና መተቸት ከንቱ እንደሆነ ሄግል ሲገልፅ፤ በአለም የምናየው ሁኔታ ሁሉ፤ መሆን የነበረበት ነው፤ ከዘመኑ አንፃር ሲታይም እንከን አይወጣለትም ይላል። ስለዚህ፤ ፀሐዩ ንጉሳችን፤ አብዮታዊው ደርጋችን፤ ልማታዊው ኢህአዴጋችን በማለት በፀጋ መቀበል፤ እናም ሳናንገራግርና ሳናማርጥ ትእዛዝ መፈፀም ይጠበቅብናል ማለት ነው።ግፍ ለመፈፀም የተነሳሱና ክፉ ስብእና ያዳበሩ ሰዎች፤ መንገዱ ወለል ብሎ ሲከፈትላቸው አይታያችሁም? “የታሪክ ተልእኮ” የሚባል መሳሪያ ታጥቀዋል። ማንኛውም የአምባገነን አይነት፤ “ታሪክ የጣለብኝን አደራ በተግባር እፈፅማለሁ” እያለ በሰዎች ላይ መጋለብ ይችላል። እነ ሌኒንና ስታሊን፤ እነ ሂትለርና ሞሶሎኒ፤ በታሪክ ሂደት ከሄግል በኋላ መምጣታቸው ይገርማል? መንገዱን ለአምባገነኖች አመቻችቶላቸዋላ፤ የጥፋት ፍልስፍና አስታጥቋቸዋል። ንፁሃን ሰዎች ደግሞ፤ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ተደርገዋል - በዚሁ የጥፋት ፍልስፍና አማካኝነት ለመንግስት ታዛዥ ሁኑ ተብለዋል። ግፍ ቢፈፀምባችሁ እንኳ መቃወምና ማውገዝ የለባችሁም ተብሎ ተነግሯቸዋል። መንግስትንና የመንግስትን ተግባራት ለመመዘን ወይም ለመዳኘት መሞከር ከንቱ እንደሆነም ጭምር በሄግል ተሰብከዋል።
እና ይሄ ፍልስፍና ትክክል ነው? በዚሁ ፍልስፍና መመራት አለብን? ለዶ/ር ዳኛቸው የማቀርባቸው የውይይት ጥያቄዎች ናቸው።

Read 4579 times Last modified on Saturday, 22 October 2011 11:11