Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 October 2011 11:40

ጳጳሱን “ናዚ” ያለችው ተዋናይት ተወገዘች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የካቶሊኩን ጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛ ናዚ ስትል የጠቀሰችው የፊልም ተዋናይቷ ሱዛን ሳራንደን በካቶሊክና አይሁድ ቡድኖች ተቃውሞ ገጠማት፡፡
የካቶሊክ ሊግ የተባለ ተቋም የሱዛን ሳራንደንን ንግግር “ነውር” በሚል የተቸ ሲሆን የፀረ ስም ማጉደፍ ሊግ የሌሎችን እምነት በሚዳፈር አሳፋሪ ተግባሯ ይቅርታ እንድትጠይቅ አሳስቧል፡፡ በርካታ ሃያሲዎች እንደተናገሩት፤ የፊልም ተዋናይቷ አፀያፊ የተባለውን ንግግር የተናገረችው የታሪክ ዕውቀቷ አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡ ሳራንደን በ1995 ዓ.ም በሰራችው የሞት ፍርድን በሚቃወመው “ዴድ ማን ዎኪንግ” የተሰኘ ፊልሟ ኦስካር መሸለሟ ይታወቃል፡፡ ተዋናይቷ በካቶሊክና አይሁድ ቡድኖች ተቃውሞ የገጠመውን አስተያየቷን ሃምፕተን የፊልም ፌስቲቫል ላይ ባደረገችው ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገረች ተገልጿል፡፡ ሳረንደን የጀርመን ትውልድ ያለው ጳጳስ የናዚ ደም አያጣም በሚል አስተሳሰብ መናገሯ ውግዘቱን አስከትሎባታል፡፡

Read 4502 times