Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 October 2011 12:12

“...በሎሚ እና በጨው ብልትን ...መታጠብ ...”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“...እኔ እድሜዬ ወደ ሀያ አምስት አመት የሚሞላኝ ነኝ ፡፡ የ12ኛ ክፍል ትምህርን ጨርሼ ወደዩኒቨርሲቲ ስገባ ከቤተሰቤ ስለተለየሁ የነበረኝን የጤና ችግር የማዋየው ለጉዋደኞቼ ነበር፡፡ ከማህጸኔ የሚፈሰው ፈሳሽ እጅግ የሚዘገንን ነበር፡፡ መልኩ ደስ አይልም ሽታ አለው፡፡ ጉዋደኞቼ ስነግራቸው ብዙዎቹ እኔም አለብኝ የተፈጥሮ ጉዳይ ነወ የሚሉ ነበሩ፡ እኔ ግን በፍጹም ልታገሰው አልቻልኩም፡፡ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቼ የምሄደው በአመት አንድ ጊዜ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከርቀት የተነሳ ነው፡፡ ወደ ቤተሰቦቼም ስሄድ ችግሩን ተናግሮ ወደ ሐኪምቤት መሄድ ስላስፈራኝ ዝም ነበር የምለው፡፡ በአጠቃላይም ይህንን ችግር ይዤ ከሁለት አመት በላይ ተሰቃየሁ የሚገርመኝ ነገር እናቴ ስለሁኔታዬ በጭራሽ አትጠይቀኝም ነበር፡፡

በሁዋላ ግን እኔ በድፍረት ለእናቴ ስነግራት በሎሚና በጨው ታጠቢ አለችኝ ሞከርኩት ፡፡ ግን አላሻለኝም፡፡ በስተመጨረሻ ግን ለአባቴ ነግሬ ወደ ሕክምናው ስለወሰደኝ መፍትሔ አግኝቻለሁ፡፡ እኔ በዚሁ አጋጣሚ የማስተላልፈው መልእክት...
ሴት ልጆች ለቤተሰባቸው ግልጽ ሆነው እያንዳንዱን ችግራቸውን በወቅቱ መናገር ይገባቸዋል፡፡
ወላጆች ስለልጆቻቸው ጤንነት በቅርብ ሆነው መከታተል እና ማወያየት ይገባቸዋል፡፡
------------------------////--------------------------
ባለፈው ሳምንት ለንባብ ካልነው የማህጸን ፈሳሽን ከሚመለከተው ጽሁፍ ቀጣዮቹ በትኩረት ልንመለከታቸው የሚገቡ በመሆናቸው አንባቢን ማስታወስ ወደድን፡፡ በእንግሊዝኛው Vaginal Discharge የሚባለው ከማህጸን የሚወጣው ፈሳሽ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡
ተፈጥሮአዊው የማህጸን ፈሳሽ ምንጩ ፡-
የማህጸን በር ከሚያመነጨው እጢ ወይንም ሴል ፣
ከማህጸን ግድግዳው ላይ እየተቀረፉ የሚወጡ ሰሎች፣
በግብረስጋ ግንኙነት መሟሟቅ ጊዜ ከደም ወደብልት የሚፈስ ፈሳሽ ..ወዘተ የማህጸን ፈሳሽን ይፈጥራሉ፡፡
ተፈጥሮአዊ የማህጸን ፈሳሽ፡-
ተፈጥሮአዊ የማህጸን ፈሳሽ የሚባለው ባብዛኛው ውሀማ ወይም ወተትማ መልክ ያለው እና የመጎተት ባህርይ ያለው ነው፡፡
ተፈጥሮአዊው የማህጸን ፈሳሽ ብዛቱ በሀያ አራት ሰአት ጊዜ ውስጥ ከአንድ እስከ አራት ሲሲ የሚደርስ ነው፡፡
ተፈጥሮአዊው የማህጸን ፈሳሽ በመጠኑ የሚሸት ነገር ሊኖረው ይችላል፡፡
Vaginal Discharge - ከማህጸን የሚወጣው ፈሳሽ ጤነኛ አይደለም የሚባልበት ደረጃ፡-
ቀለሙን ሲለውጥ /ማለትም/ ብጫ፣ ነጭአረፋ ፣ አረንጉዋዴ ፣ቡናማ ...ወዘተ የመሳሰሉትን ሲመስል ነው፡፡
ከላይ ለንባብ ያልነውን ነጥብ የገለጹት ዶ/ር: እያሱ መስፍን የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስትና ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ዶ/ር: እያሱ በዚህ አምድ የማህጸን ፈሳሽን ጤና በሚመለከት የሰጡንን ቀሪውን ማብራሪያ ለንባብ ብለናል ፡፡
ኢሶግ: በግብረ ስጋ ግንኙነት ሳቢያ ከሚተላለፉ ሕመሞች የማህጸን ፈሳሽ ሊከሰት ይችላልን?
ዶ/ር: ተፈጥሮአዊው የማህጸን ፈሳሽ ወደታማሚነት የሚለወጥበት በርካታ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፉ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ጨብጥ የላይኛው የማህጸን ክፍል ወይንም የማህጸን በርን በመመረዝ ፈሳሽ እንዲበዛና ጠረኑም እንዲበላሽ ያደርጋል፡፡ በጨብጥ ምክንያት የሚከሰተው መግል የመሰለ ፈሳሽ ነው ፡፡ በጨብጥ ምክንያት የሚከሰተው ሌላው ችግር ከፈሳሽ በተጨማሪ ሕመምም መኖሩ ነው፡፡ ሴቶች በታችኛው ሆዳቸው አካባቢ ወይንም ማህጸናቸው ውስጥ በእንቅስቃሴ ግዜ ወይንም ሆዳቸው በሚነካበት ወቅት አለበለዚያም በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ሕመም እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ ሌላው ወደ ነጭ ያደላ ፈሳሽን የሚያስከትለው በጀርም ምክንያት የሚመጣው ፈሳሽ ነው፡፡
ኢሶግ: በስራ እንቅስቃሴ ምክንያት የማህጸን ፈሳሽ ጤነኛ አለመሆን ሊከሰት ይችላልን?
ዶ/ር: የማህጸን ፈሳሽ ጤነኛ አለመሆን በቀጥታ ስራ ከመስራት ጋር ሳይሆን ስራ በመስራት ምክንያት ከሚከሰት የሰውነት መጎዳት ጋር በተያያዘ ሊከሰት ይችላል፡፡በተጨማሪም ስራውን የሚሰሩበት ቦታ ንጽህናና የአየር ጸባይን በመሳሰለው ምክንያት የተፈጥሮ የመከላከል አቅም ከቀነሰም ተፈጥሮአዊ ላልሆነው ፈሳሽ ሊዳርግ ይችላል፡፡
ኢሶግ: ተፈጥሮአዊ ያልሆነው የማህጸን ፈሳሽ ከንጽህና አጠባበቅ ጋር ሊያያዝ ይችላልን?
ዶ/ር: የንጽህና አጠባበቅን በተመለከተ ሴቶች ቀላል የሚመስላቸውና በየእለቱ ሊጠቀሙበት የሚችሉት ...ነገር ግን ለጉዳት ሊያጋልጣቸው የሚቸሉ ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በብልት አካባቢ የጠረን መለወጫ የመሳሰሉ ኩሚካሎች፣ የላብ ማድረቂያ ፓውደር፣ የመሳሰሉትን የሚጠቀሙ ከሆነ ለችግር ስለሚያጋልጣቸው ያንን ማቋረጥ ይገባቸዋል፡፡ በመታጠብም በኩል ምናልባት ገላን በሚታጠቡበት ወቅት ካልሆነ በስተቀር በየእለቱ በሳሙና መታጠብ አስፈላጊ አይደለም፡፡ በተለይም የብልትን የውስጠኛውን ክፍል ምንጊዜም ቢሆን በሳሙና መታጠብ ተገቢ አይደለም፡፡ የሚጠቀሙባቸውንም ሳሙናዎች የኬሚካል ውህደት ምን ያህል የጠነከረና ያልጠነከረ ወይንም አሲዳቸው የበዛና ያልበዛ መሆኑን በማየትም ቀለል ያሉ ሳሙናዎችን መጠቀም ተገቢ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ደግሞ በሎሚ እንዲሁም ጨው በመሳሰሉት ነገሮች የሚታጠቡ ሲሆን ይህ ትክክለ አለመሆኑን ቢያውቁ ይጠቅማል፡፡
ኢሶግ: አለባበስ ምን ያህል ተፈጥሮአዊ ላልሆነው የማህጸን ፈሳሽ ይዳርጋል?
ዶ/ር: አለባበስን በተመለከተ ብዙ ሊስተዋል የሚገባው ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ሰውነት ላይ በጣም ጥብቅ የሚሉ እና ወደወገብ የሚያልፈው የሱሪ ክፍል አጫጭር የሆኑ ሱሪዎች በገበያ ላይ በብዛት ስላሉ ሴቶች ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ፡፡ የውስጥ ሱሪዎችንም በሚመለከት በጣም ትናንሽ የሆኑና ሰውነት ላይ የሚጣበቁ እንዲሁም ከጥጥ ያልተሰሩ ጨርቆች በጥቅም ላይ ሲውሉ ይስተዋላሉ፡፡ ይህ ግን በሰውነት ላይ ሙቀት ሊፈጥር የሚችል ስለሆነ ላብ በማምጣት አዋራ በመሳብ በመሳሰሉት የባክሪያ ቁጥር እንዲዛባ ስለሚያደርግ ተፈጥሮአዊ ላልሆነው ፈሳሽ ሊዳርግ ይችላል፡፡
ኢሶግ: ከማህጸን ውስጥ የሚወጣ አየርና ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ፈሳሽ ግንኙነት አላቸውን?
ዶ/ር: ከማህጸን አየር ሊወጣ የሚችለው ከፈሳሽ ጋር በተያያዘ ወይንም ባልተያያዘ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማህጸንን ደግፈው የሚይዙት ቋበቅቅቄቈሽቃሸ ቋቈበሰበቈስ የሚባሉት መላላት ሲደርስባቸው ማህጸን ይላላል፡፡ በዚህን ጊዜ ማህጸን ጠበቅ ብሎ የሚቀመጥበት ሁኔታ ስለሚጎድል አየር ወደውስጥ መሳብ ይጀምራል፡፡ ሌላው አየር ከማህጸን ሲወጣ ፊስቱላ ከሚባለው የጤና ችግር ጋር የተያያዘ መሆን ያለመሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ከአንጀት ጋር የተያያዘ ፌስቱላ ሲኖር አየር ስለሚያፈተልክ ወደውጭ ሲወጣ ሊሰማ ይችላል፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ አንዳንድ ባክሪያዎችሮቈሯቄቃ ሳሽቄቦሽሳስ የተሰኘውን አየር ያመነጫሉ፡፡ ለምሳሌም አረፋ የመሰለው የማህጸን ፈሳሽ በባክሪያ ከተፈጠረው አየር የሚመጣ ሊሆን ይችላል፡፡
ኢሶግ: ተፈጥሮአዊውን ፈሳሽ ጠብቆ ለማቆየት ምን ማድረግ ይመከራል?
ዶ/ር: ወደመፍትሔው ስንመጣ ፡-
ትክክለኛ የሆነ የብልት ንጽህና አጠባበቅን መከተል ...ማለትም ሴቶች ጠዋትና ማታ ሲታጠቡ ከሳሙና ውጭ በውሀ ብቻ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ሴቶች ገላቸውን በሚታጠቡ ጊዜም ቢሆን የብልታቸውን የውስጥ ክፍል ሳሙና እንዳይነካው መጠንቀቅ አለባቸው፡፡
ሴቶች እንደጠረን መለወጫ የመሳሰሉትን ኬሚካሎች በብልታቸው አካባቢ መጠቀም አይገባቸውም፡፡
ለሰውነት ተስማሚ ያልሆኑ ልብሶችን ማለትም ጥብቅ የሚሉ ሙታንታ እና ሱሪ እንዲሁም ከጥጥ ያልተሰሩ ሙታንታዎችን መጠቀም የመሳሰሉትን ልምዶች ማስወገድ ይገባል፡፡
ከዚህ ሁሉ ጥንቃቄ ባለፈ የማህጸን ፈሳሽ ጤናው የሚታወክ ከሆነ ወደሐኪም ዘንድ ቀርቦ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው ፡፡

 

Read 7075 times Last modified on Saturday, 22 October 2011 12:26