Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 29 October 2011 15:46

ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያዊውን ወጣት በ700ሺህ ብር ከሞት አተረፈ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ከሦስት ዓመታት በፊት መቀሌ የሚገኙትን ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ ኑሮውን ለማሸነፍ ለሥራ ወደ ፑንትላንድ ያመራው ኢትዮጵያዊው የ31 ዓመት ወጣት አስመሮም ኃይለሥላሴ፤ እዛው ሆቴል ከፍቶ እየሠራ ነበር፡፡ ከባለቤቱ እና ከአንዲት ሴት ልጁ ጋር አንድ ዓመት ያህል እንደቆየም፤ በታኅሣሥ 2002 ዓ.ም አምስት የታጠቁ ሶማሊያውያን በሌሊት ለዝርፍያ ባለቤቱን ለመድፈር እና ግድያ ለመፈፀም ግብግብ ይገጥሙታል፡፡ በወቅቱም አብረውት ከነበሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ራሳቸውን ለመከላከል በወሰዱት እርምጃ ከዘራፊዎቹ አንዱ ህይወቱ ያልፋል፡፡ አብረውት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አምልጠው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡

አስመሮም ግን ታስሮ ጉዳዩን ሲከታተል ይቆያል፡፡ ቤተሰቦቹ እንደሚሉትም በአካባቢው የሚኖሩ ሶማሊያውያን አስመሮም ጥፋት እንደሌለበት እና በሰዓቱም ተኝቶ እንደነበር ምስክርነታቸውን ሰጥተውለታል፡፡ ሆኖም ምስክርነታቸው ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከአንድ ዓመት እስር በኋላ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡ 
አስመሮም በእስር ቤት ሳለ ሚስት በግብግቡ ወቅት ጉዳት የደረሰባትን የሰባት ዓመት ሴት ልጇን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰች ሲሆን ታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር ህይወቷ አልፏል፡፡ የልጇን መሞት እና በባለቤቷ ላይ ሞት መፈረዱን መቋቋም ያቃታት ባለቤቱ በአሁኑ ሰዓት የት እንዳለች እንደማይታወቅ የአስመሮም እህት ሉአም ኃይለሥላሴ ለአዲስ አድማስ ተናግራለች፡፡  
እህቱ እንደምትለው ወንድሟ ከታሰረ ሁለት ዓመት ሆኖታል፤ ጉዳዩም ፑንትላንድ ውስጥ በምትገኘው ቦሳሶ ከተማ ሲታይ ቆይቶ በከተማዋ ያሉ የጐሳ
አባላት በሞት እንዲቀጣ ይወስናሉ፡፡ የሞት ቅጣቱ የሚነሳለት ደግሞ 700ሺ የኢትዮጵያ ብር ወይም ወደ 40ሺህ ዶላር አካባቢ ሲከፍል ብቻ እንደሆነ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡ ሁኔታው እጅግ ያስጨነቃቸው ቤተሰቦቹ፤ በተለያየ ጊዜ በርካታ ደብዳቤዎችን ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመፃፍ መንግሥት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ የወጣቱን ህይወት እንዲያተርፍላቸው ቢማፀኑም ምላሽ ሳያገኙ መቅረታቸውን የወጣቱ እህት ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ ጥቅምት 7 ቀን 2004 ዓ.ም ወጣት አስመሮም ቤተሰቦቹን እንዲሰናበት በማለት አሳሪዎቹ ስልክ ወደ ቤተሰቦቹ እንዲደውል ያደርጋሉ፡፡ በተደወለው ስልክም እስከ አርብ መስከረም 17 ቀን ድረስ ገንዘቡን መክፈል ካልቻለ የሞት ፍርዱ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተናግሮ የ”ደህና ሁኑ” መልዕክት ለቤተሰቦቹ አስተላልፎ ቤተሰቦቹን ይሰናበታል፡፡ እህቱ እንደተናገረችው፤ “ቅጣቱ ፍትሃዊ ባለመሆኑ ተፈፃሚ እንዳይሆን የቻልነውን ሁሉ ሞከርን፤ የሞት ፍርዱ ሊፈፀም ሁለት ቀናት ብቻ ሲቀሩት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ምናልባት በሥራ ጫና ወይም ከሱ የባሰ ጉዳዮችን ሲፈጽሙ አቤቱታችንን አልሰሙም ይሆናል በሚል አስበን የመጨረሻ ዕድል ለመሞከር ጉዳዩን ለሪፖርተር ጋዜጣ አስረዳን፤ እነሱም ዜናውን ረቡዕ እለት አወጡት፡፡ እስከ ሐሙስ ማታ ድረስም ምንም የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ ሐሙስ ምሽት ላይ ግን አንድ ስልክ ተደወለልኝ፤ አንድ ሰው ገንዘቡን ከፍሎ የወንድማችሁን ህይወት ሊታደግ ነውና ነገ ትገናኛላችሁ የሚል ነበር” ስትል ሁኔታውን ታስረዳለች፡፡ እህቱ እንደምትለው፤ ቤተሰቦቹ የጠበቁት የመንግሥት አካላት ጋዜጣውን አይተው ምላሽ ይሰጡናል ብለው እንጂ አንድ ግለሰብ ገንዘቡን ከፍሎ ያስለቅቅልናል የሚል ግምት አልነበራቸውም፡፡ በትናንትናው ዕለትም የወንድሟ መትረፍ እንጂ የወንድሟን ህይወት ለመታደግ ያሰበው ግለሰብ ማንነት ሳያስጨንቃት በደስታ እና በሲቃ ተውጣ የተባለው ቦታ ስትሄድ፤ ገንዘቡን ከፍሎ የወጣቱን ህይወት ለመታደግ የወሰነው ግለሰብ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) መሆኑን ትረዳለች፡፡ “ገንዘቡን የሰጠኝ በቼክ ነው፡፡ ይህንን ያደረኩት እኔ ሳልሆን እግዚአብሔር ነው፡፡ አይዞሽ ተጽናኚ ብሎ 700ሺህ ብር የያዘ ቼክ ሰጠኝ፤ ማመን አልቻልኩም፤ ምን እንደምናገርም አላውቅም፤ ብቻ እኔ ሰው ነኝ ግን በእግዚአብሔር እና በቤተሰቦቼ ስም እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ” ብላለች፡፡ አክላም ዱሮም ቢሆን ቴዲን በጣም እወደው ነበር፤ አሁን ደግሞ በጣም ወደድኩት” ብላለች፡፡ ገንዘቡን ካገኘች በኋላም ስለ ገንዘቡ አከፋፈል እና አስመሮም ከእስር ተለቆ ወደ አገር ስለሚመለስበት ሁኔታ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጋር  ቤተሰቦቹ እየተነጋገሩ መሆኑን በመግለጽ፤ ቴዲ አፍሮ የሰጣትን ቼክ በዛሬው ዕለት መንዝራ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ገንዘቡ ተከፍሎ ወንድሟ ከእስር እንዲለቀቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኗን ገልፃልናለች፡፡ ወጣት አስመሮምን በተመለከተ “ወገናችንን ከሞት እናድን” በሚል ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ በራሪ ወረቀት ጽፈው በድረ ገጽ የልመና ድምፃቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸውን በመግለጽ “በመጨረሻ ቴዲ አፍሮ ደረሰልን” ብለዋል -ቤተሰቦቹ፡፡  ከሦስት ዓመታት በፊት መቀሌ የሚገኙትን ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ ኑሮውን ለማሸነፍ ለሥራ ወደ ፑንትላንድ ያመራው ኢትዮጵያዊው የ31 ዓመት ወጣት አስመሮም ኃይለሥላሴ፤ እዛው ሆቴል ከፍቶ እየሠራ ነበር፡፡ ከባለቤቱ እና ከአንዲት ሴት ልጁ ጋር አንድ ዓመት ያህል እንደቆየም፤ በታኅሣሥ 2002 ዓ.ም አምስት የታጠቁ ሶማሊያውያን በሌሊት ለዝርፍያ ባለቤቱን ለመድፈር እና ግድያ ለመፈፀም ግብግብ ይገጥሙታል፡፡ በወቅቱም አብረውት ከነበሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ራሳቸውን ለመከላከል በወሰዱት እርምጃ ከዘራፊዎቹ አንዱ ህይወቱ ያልፋል፡፡ አብረውት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አምልጠው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡ አስመሮም ግን ታስሮ ጉዳዩን ሲከታተል ይቆያል፡፡ ቤተሰቦቹ እንደሚሉትም በአካባቢው የሚኖሩ ሶማሊያውያን አስመሮም ጥፋት እንደሌለበት እና በሰዓቱም ተኝቶ እንደነበር ምስክርነታቸውን ሰጥተውለታል፡፡ ሆኖም ምስክርነታቸው ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከአንድ ዓመት እስር በኋላ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡ አስመሮም በእስር ቤት ሳለ ሚስት በግብግቡ ወቅት ጉዳት የደረሰባትን የሰባት ዓመት ሴት ልጇን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰች ሲሆን ታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር ህይወቷ አልፏል፡፡ የልጇን መሞት እና በባለቤቷ ላይ ሞት መፈረዱን መቋቋም ያቃታት ባለቤቱ በአሁኑ ሰዓት የት እንዳለች እንደማይታወቅ የአስመሮም እህት ሉአም ኃይለሥላሴ ለአዲስ አድማስ ተናግራለች፡፡  እህቱ እንደምትለው ወንድሟ ከታሰረ ሁለት ዓመት ሆኖታል፤ ጉዳዩም ፑንትላንድ ውስጥ በምትገኘው ቦሳሶ ከተማ ሲታይ ቆይቶ በከተማዋ ያሉ የጐሳ አባላት በሞት እንዲቀጣ ይወስናሉ፡፡ የሞት ቅጣቱ የሚነሳለት ደግሞ 700ሺ የኢትዮጵያ ብር ወይም ወደ 40ሺህ ዶላር አካባቢ ሲከፍል ብቻ እንደሆነ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡ ሁኔታው እጅግ ያስጨነቃቸው ቤተሰቦቹ፤ በተለያየ ጊዜ በርካታ ደብዳቤዎችን ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመፃፍ መንግሥት ዲፕሎማሲያዊ ጥረትበማድረግ የወጣቱን ህይወት እንዲያተርፍላቸው ቢማፀኑም ምላሽ ሳያገኙ መቅረታቸውን የወጣቱ እህት ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ ጥቅምት 7 ቀን 2004 ዓ.ም ወጣት አስመሮም ቤተሰቦቹን እንዲሰናበት በማለት አሳሪዎቹ ስልክ ወደ ቤተሰቦቹ እንዲደውል ያደርጋሉ፡፡ በተደወለው ስልክም እስከ አርብ መስከረም 17 ቀን ድረስ ገንዘቡን መክፈል ካልቻለ የሞት ፍርዱ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተናግሮ የ”ደህና ሁኑ” መልዕክት ለቤተሰቦቹ አስተላልፎ ቤተሰቦቹን ይሰናበታል፡፡ እህቱ እንደተናገረችው፤ “ቅጣቱ ፍትሃዊ ባለመሆኑ ተፈፃሚ እንዳይሆን የቻልነውን ሁሉ ሞከርን፤ የሞት ፍርዱ ሊፈፀም ሁለት ቀናት ብቻ ሲቀሩት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ምናልባት በሥራ ጫና ወይም ከሱ የባሰ ጉዳዮችን ሲፈጽሙ አቤቱታችንን አልሰሙም ይሆናል በሚል አስበን የመጨረሻ ዕድል ለመሞከር ጉዳዩን ለሪፖርተር ጋዜጣ አስረዳን፤ እነሱም ዜናውን ረቡዕ እለት አወጡት፡፡ እስከ ሐሙስ ማታ ድረስም ምንም የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ ሐሙስ ምሽት ላይ ግን አንድ ስልክ ተደወለልኝ፤ አንድ ሰው ገንዘቡን ከፍሎ የወንድማችሁን ህይወት ሊታደግ ነውና ነገ ትገናኛላችሁ የሚል ነበር” ስትል ሁኔታውን ታስረዳለች፡፡ እህቱ እንደምትለው፤ ቤተሰቦቹ የጠበቁት የመንግሥት አካላት ጋዜጣውን አይተው ምላሽ ይሰጡናል ብለው እንጂ አንድ ግለሰብ ገንዘቡን ከፍሎ ያስለቅቅልናል የሚል ግምት አልነበራቸውም፡፡ በትናንትናው ዕለትም የወንድሟ መትረፍ እንጂ የወንድሟን ህይወት ለመታደግ ያሰበው ግለሰብ ማንነት ሳያስጨንቃት በደስታ እና በሲቃ ተውጣ የተባለው ቦታ ስትሄድ፤ ገንዘቡን ከፍሎ የወጣቱን ህይወት ለመታደግ የወሰነው ግለሰብ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) መሆኑን ትረዳለች፡፡ “ገንዘቡን የሰጠኝ በቼክ ነው፡፡ ይህንን ያደረኩት እኔ ሳልሆን እግዚአብሔር ነው፡፡ አይዞሽ ተጽናኚ ብሎ 700ሺህ ብር የያዘ ቼክ ሰጠኝ፤ ማመን አልቻልኩም፤ ምን እንደምናገርም አላውቅም፤ ብቻ እኔ ሰው ነኝ ግን በእግዚአብሔር እና በቤተሰቦቼ ስም እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ” ብላለች፡፡ አክላም ዱሮም ቢሆን ቴዲን በጣም እወደው ነበር፤ አሁን ደግሞ በጣም ወደድኩት” ብላለች፡፡ 
ገንዘቡን ካገኘች በኋላም ስለ ገንዘቡ አከፋፈል እና አስመሮም ከእስር ተለቆ ወደ አገር ስለሚመለስበት ሁኔታ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጋር ቤተሰቦቹ እየተነጋገሩ መሆኑን በመግለጽ፤ ቴዲ አፍሮ የሰጣትን ቼክ በዛሬው ዕለት መንዝራ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ገንዘቡ ተከፍሎ ወንድሟ ከእስር እንዲለቀቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኗን ገልፃልናለች፡፡ 
ወጣት አስመሮምን በተመለከተ “ወገናችንን ከሞት እናድን” በሚል ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ በራሪ ወረቀት ጽፈው በድረ ገጽ የልመና ድምፃቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸውን በመግለጽ “በመጨረሻ ቴዲ አፍሮ ደረሰልን” ብለዋል -ቤተሰቦቹ፡፡

 

Read 9905 times Last modified on Tuesday, 22 November 2011 14:08