የምርጫ የጊዜ ሰሌዳውን በተመለከተ ከምርጫ ቦርድ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ ሲገልፁ የቆዩት 33ቱ ፓርቲዎች፤ ለህትመት እስከ ገባንበት ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ምልክት አለመውሰዳቸውን ለማወቅ ችለናል። ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠውን የጊዜ ቀነ ገደብ እንደማይቀበሉት የገለፁት 33ቱ ፓርቲዎች፤ ቀነ ገደቡ ፓርቲዎችን እርስ በርስ ለመከፋፈልና ለመለያየት የሚደረግ ሴራ ነው ብለዋል፡፡
በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ላይ አለመስማማታችንና በምርጫ ምልክቱ ዙሪያ ውይይት እያካሄድን እንደሆነ ምርጫ ቦርድ ያውቃል ያሉት አቶ አስራት፤ ቀን ገደብ ማስቀመጥ የቦርዱ ስልጣንና ሃላፊነትን አይደለም ብለዋል፡፡
ቦርዱ የውድድር ምልክቱን ቀነ ገደብ ያስቀመጠው ለምርጫው አስቦ ሳይሆን ፓርቲዎችን ለመከፋፈል እንደሆነ አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡