ብሩስ ስፕሪንግስተንና እና “ዘ ስትሪት ባንድ” በበኩላቸው፤ 72 ኮንሰርቶች ላይ በመስራት 199.4 ሚ. ዶላር አስገብተው በሁለተኛ ደረጃ ሲቀመጡ፤ ሮጀር ዋተርስ በ72 ኮንሰርቶች 186.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በመሰብሰብ ሶስተኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡ በቢልቦርድ የሙዚቃ የገበያ ሰንጠረዥ ተቀናቃኝ ያጣችው አሜሪካዊቷ ቴይለር ስዊፍት፤ እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ ሳትገባ መቅረቷ አስገርሟል፡፡ 183 ኮንሰርቶች በመላው ዓለም የቀረቡበት የማይክል ጃክሰን “ዘ ኢሞርታል ዎርልድ ቱር” 147.3 ሚ. ዶላር፤ ኮልድ ፕሌይ 147.3 ሚ. ዶላር፤ ሌዲ ጋጋ 124.9 ሚ. ዶላር፤ ኬኒ ቼዝኒ እና ቲም ማክግሩው 96.5 ሚ. ዶላር፤ ቫን ሄለን 54.4 ሚ. ዶላር፤ ጄይዚ እና ካናዬ ዌስት 47 ሚ. ዶላር እንዲሁም አንድሬ ሬው 46.8 ሚ. ዶላር ገቢ በሰሩት ኮንሰርቶች በማስገባት እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ እንደወሰዱ ፎርብስ አመልክቷል፡፡