ራፐር ካናዬ ዌስት በበኩሉ፤በሙዚቃ ፕሮዱዩሰርነት፤ በፋሽን ዲዛይነርነት እና በፊልም ተዋናይነት 90 ሚሊዮን ዶላር ሃብት አፍርቷል፡፡ ኪም “ኪፒንግ አፕ ዊዝ ዘ ካርዴሽያን” በተባለውና የመላው ቤተሰቧንና ዘመድ አዝማዷን የእለት ህይወት በሚያሳየው የቴሌቭዥን ሪያሊቲ ሾው ላይ በአንድ ክፍል 40ሺ ዶላር እየተከፈላት ትሰራለች፡፡
በ2012 ከቀረቡ ኮንሰርቶች የገቢ ደረጃ በቢልቦርድ የሙዚቃ የገበያ ሰንጠረዥ ተቀናቃኝ ያጣችው አሜሪካዊቷ ቴይለር ስዊፍት እስከ 10 ባለው ደረጃ ሳትገባ መቅረቷ አስገርሟል፡፡ 183 ኮንሰርቶችን በመላው ዓለም ለማቅረብ የተቻለበት የማይክል ጃክሰን ዘ ኢሞርታል ዎርልድ ቱር 147.3 በሚሊዮን ዶላር፤ በ67 ኮንሰርቶች ያቀረቡት ኮልድ ፕሌይ በ 147.3 በሚሊዮን ዶላር፤ ሌዲ ጋጋ በ65 ኮንሰርቶች 124.9 ሚሊዮን ዶላር፤ ኬኒ ቼዝኒ እና ቲም ማክግሩው በ23 ኮንሰርቶች 96.5 ሚሊዮን ዶላር፤ ቫን ሄለን በ46 ኮንሰርቶች 54.4 ሚሊዮን ዶላር፤ ጄይዚ እና ካናዬ ዌስት በ31 ኮንሰርቶች 47 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም አንድሬ ሬው በ99 ኮንሰርቶች 46.8 ሚሊዮን ዶላር በመላው ዓለም ገቢ በማድረግ እስከ 10 ያለውን ደረጃ እንደወሰዱ መፅሄቱ አመልክቷል፡፡