Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 05 January 2013 11:51

የኦስካር እጩዎች ሰሞኑን ይገለፃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኦስካር ሽልማት ከወር በኋላ የሚካሄድ ሲሆን ለሽልማት የሚፎካከሩት እጩዎች ሰሞኑን እንደሚገለፁ ይጠበቃል፡፡የስቴቨን ስፒልበርግ ፊልም “ሊንከን” እና የቤን አፍሌክ ፊልም “አርጎ” በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በበርካታ ዘርፎች የመታጨት እድላቸው ሰፊ መሆኑን ዩኤስኤ ቱዴይ ዘግቧል፡ በሌላ በኩል 70ኛው የጎልደን ግሎብ አዋርድ ከሳምንት በኋላ በካሊፎርንያ ቤቨርሊ ሂልስ በሚገኘው የቤቨርሊ ሆቴል ይከናወናል፡፡ ለዚሁ ሽልማት የቀረቡ እጩዎች ከወር በፊት ይፋ የተደረጉ ሲሆን የሽልማት ስነስርዓቱ የኦስካር አሸናፊዎችን ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል ተብሏል፡፡

ለጎልደን ግሎብ በሰባት ዘርፎች በመታጨት የተሳካለት የስቴቨን ስፒልበርግ ‹ “ሊንከን” ሲሆን እያንዳንዳቸው በአምስት ዘርፎች በመታጨት የቤን አፍሌክ “አርጎ” እና የኪዊን ቲንታረንቲኖ “ዲጃንጎ አንቼንድ” ይከተላሉ፡፡ ኦሳማ ቢን ላደንን ለማደን በተደረገው ጥረት ዙሪያ የተሰራው የካተሪን ቢገሎው “ዜሮ ዳርክ ሰርቲ” በአራት ዘርፎች ታጭቷል፡፡በጎልደን ግሎብ በበርካታ ዘርፎች በመታጨት የተሳካላቸው ፊልሞች በኦስካርም ለምርጥ ፊልም፤ ለምርጥ ተዋናዮች እና ለምርጥ ዲያሬክተር ምርጫ እንደሚፎካከሩ ይጠበቃል፡፡ የጎልደን ግሎብ አሸናፊዎችን የሚመርጡት በሎስአንጀለስ ከተማ የሚሰሩ 90 የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ የጎልደን ግሎብ ተሸላሚዎች በኦስካር የማሸነፍ እድላቸው ሰፊ እንደሚሆን እየተገለፀም ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በጎልደን ግሎብ ምርጥ ድራማ ተብሎ የተሸለመው “ዘ ዲሴንዳንትስ” ሲሆን ምርጥ ኮሜዲ ወይም ሚዩዚካል በተባለው ዘርፍ ደግሞ “ዘ አርቲስት” እንደተሸለመ ይታወሳል፡፡
ለ2013 የኦስካር ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች የታጩ ፊልሞችና ባለሙያዎች ዝርዝር በቀጣይ ሳምንት አጋማሽ ላይ ይፋ ይሆናል፡፡ ሽልማቱን የሚያዘጋጀው አካዳሚ ኦፍ ሞሽን ፒክቸርስ አርትስ ኤንድ ሳይንስ አባላት ድምፅ እየሰጡ ቆይተው ትላንት ተጠናቅቋል፡፡

Read 4253 times