ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ2005/06 ዓ.ም. የመጀመርያውን ውድድር ነገ በጎንደር ከተማ ሊያካሂድ ነው፡፡ የጎንደሩ ውድድር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተመሠረተበት 1993 ዓ.ም. ጀምሮ የተካሔዱትን ውድድሮች 83 ያደርሳል፡፡
በጎንደር ከተማ የሚካሔደው የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ 2,500 ተወዳዳሪዎች ይሳተፉበታል፡፡ የልጆችም ውድድር መዘጋጀቱን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡የታላቁ ሩጫ ውድድር በጎንደር ከተማ የተዘጋጀው ለመጀመርያ ጊዜ ቢሆንም በአማራ ክልል ውድድሩ በባህርዳር፤ ላሊበላ እና ደብረማርቆስ ውስጥ ተካሂዶ ያውቃል፡፡
Published in
ስፖርት አድማስ