Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 January 2013 09:58

በ2012 የፊፋ ክዋክብት ምርጫ የ“ምድብ 3” ሚና ምን ይመስላል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በሳምንቱ መጀመርያ ፊፋ የ2012 የእግር ኳስ ኮከቦችን በየዘርፉ የሸለመ ሲሆን ሊዮኔል ሜሲ ለአራተኛ ጊዜ የዓለም ኮከብ ተጨዋች ሆኖ በመመረጥ የመጀመርያው ተጨዋች ሆነ፡፡
ሊዮኔል ሜሲ የወርቅ ኳሱን ሊሸለም የበቃው የፊፋ አባል አገራት የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች እና አምበሎች ከሰጡት ድምፅ 41.6 በመቶውን በማሸነፍ ነው፡፡ክርስትያኖ ሮናልዶ በ23.6 በመቶ እንዲሁም ኢኒዬስታ በ10.91 በመቶ ድምፅ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ወስደዋል፡፡ የስፔን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቪሰንቴ ዴልቦስኬ የ2012 ኮከብ አሰልጣኝ ሆነው ሲመረጡ በ2012 የዓለም እግር ኳስ ምርጥ 11 ቡድንን የስፔኑ ላሊጋ አምስት ከሪያል ማድሪድ፤ አምስት ከባርሴሎና እንዲሁም 1 ከአትሌቲኮ ማድሪድ በማስመረጥ ተቆጣጥሮታል፡፡

በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተደለደሉት አራት አገራት ብሄራዊ ቡድኖች አሰልጣኞች እና አምበሎች ምርጫ ከዚህ በታች በዝርዝር እንደተቀመጠው ነበር፡፡
በኮከብ ተጨዋች ምርጫ
አምበሎች
ደጉ ደበበ - ከኢትዮጵያ ሮናልዶ፤ ሜሲ፤ ዣቪ
ክሪስቶፈር ካቶንጎ ከዛምቢያ - ሜሲ፤ዣቪ፤ ኢንዬስታ
ማሙኒ ዳጋኖ ከቡርኪናፋሶ - ሜሲ፤ ኢንዬስታ ፤ሮናልዶ
ጆሴፍ ዮቦ ከናይጄርያ - ሜሲ፤ሮናልዶ፤ ኔይማር
አሰልጣኞች
ሰውነት ቢሻው ከኢትዮጵያ - ሮናልዶ፤ ሜሲ፤ ዣቪ
ሄርቬ ሬናርድ ከዛምቢያ - ሜሲ፤ዣቪ፤ ኢንዬስታ
ፓል ፑት ከቡርኪናፋሶ - ሜሲ፤ሮናልዶ ፤ ኢንዬስታ
ስቴፈን ኬሺ ከናይጄርያ - ቱሬ፤ድሮግባ፤ ቫንፒርሲ
በኮከብ አሰልጣኝ ምርጫ
አምበሎች
ደጉ ደበበ ከኢትዮጵያ - ሞውሪንሆ፤ጋርዲዮላ፤ፈረጉሰን
ክሪስቶፈር ካቶንጎ ከዛምቢያ - ዴልቦስኬ፤ሞውሪንሆ፤ ጋርዲዮላ
ማሙኒ ዳጋኖ ከቡርኪናፋሶ - ጋርዲዮላ፤ ጆአኪም ሎው ፤ሞውሪንሆ
ጆሴፍ ዮቦ ከናይጄርያ ማንቺኒ፤ዲማትዮ፤ ዴልቦስኬ
አሰልጣኞች
ሰውነት ቢሻው ከኢትዮጵያ - ሞውሪንሆ፤ ጋርዲዮላ፤ ፈርጉሰን
ሄርቬ ሬናርድ ከዛምቢያ - ዴልቦስኬ፤ሞውሪንሆ፤ ጋርዲዮላ
ፓል ፑት ከቡርኪናፋሶ - ዴልቦስኬ፤ጋርዲዮላ፤ ሞውሪንሆ
ስቴፈን ኬሺ ከናይጄርያ - ሞውሪንሆ፤ክሮፕ፤ ዴልቦስኬ
የኢትዮ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አምበል የሆነችው ብዙሃን እንዳለ በኮከብ ሴት ተጨዋች ምርጫ ሳማ ኦሃሬ፤ ማርታና ሞርጋን አሌክስ ከ1 እስከ 3 ደረጃ ሰጥታ ስትመርጥ የሉሲዎች አሰልጣኝነትን የወከለው ብርሃኑ ዘርጋውም በተመሳሳይ ድምፁን ሰጥቷል፡፡
የስፖርት ጋዜጠኛው መንሱር አብዱል ቀኒ በበኩሉ በኮከብ ተጨዋች ምርጫው በመሳተፍ ሜሱ፤ ሮናልዶ እና ፋልካኦን በመመረጥ ተጠቅሷል፡፡

Read 8645 times