Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 January 2013 10:03

‹‹ሌስ ሚዝረብልስ›› ከሙዚቃዊ ድራማ ፊልሞች በገቢ ተሳክቶለታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በዩናይትድ ኪንግደም የተሰራው እና ባለፈው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ መታየት የጀመረው ‹‹ሌስ ሚዝረብልስ›› የተባለው ሙዚቃዊ ድራማ በሰሜን አሜሪካ በዘርፉ ከፍተኛውን ገቢ እንዳስገባ ዘ ጋርድያን ዘገበ፡፡ ‹‹ሌስ ሚዝረብልስ›› ለእይታ በበቃ በ13 ቀናት በሰሜን አሜሪካ ብቻ 100 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት አዲስ ክብረወሰን እንዳስመዘገበ ታውቋል፡፡

ከ28 ዓመት በፊት ቲያትር ሆኖ የቀረበው “ሌስ ሚዝረብልስ” ዘንድሮ በፊልምነት ሲቀርብ በመላው ዓለም ከ60 ሚሊዮን በላይ ተመልካች ያገኘ ሲሆን ጠቅላላ ገቢው ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በቶም ሁፕር ዲያሬክተርነት በ61 ሚሊዮን ዶላር በጀት በተሰራው በዚህ ልዩ ሙዚቃዊ ፊልም ላይ አና ሃታወይ፤ ሂውጅ ጃክማን እና ራስል ክሮው ተውነዋል፡፡

Read 5224 times