Saturday, 19 January 2013 14:52

"ግጥም በዋሽንት በመሰንቆ" በቋሚነት እንዲካሄድ ተጠየቀ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

ለ3ኛ ጊዜ በጐንደር ከተማ በተካሄደው "ኢትዮጵያን በጐንደር ብሔራዊ የባህል ፌስቲቫል ላይ በወጣቶች የቀረበው "ግጥም በዋሽንት በመሰንቆ" በቋሚነት እንዲካሄድ ተጠየቀ፡፡ ባለፈው ረቡዕ ማምሻውን በከተማዋ "ዕልልታ አዳራሽ" ተካሂዶ በነበረ ዝግጅት ወጣቶቹ በባህል የሙዚቃ መሣሪያዎች የታጀበ የግጥም፣ የመነባንብ እና የተውኔት ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
ዝግጅቱን የታደሙ ወላጆችና የኪነ -ጥበብ አድናቂዎች ዝግጅቱ በየጊዜው እንዲቀርብና
"ግጥም በዋሽንት በመሰንቆ" በቋሚነት እንዲካሄድ ተጠየቀ
በአዝማሪዎቿ የምትታወቀዋ ከተማ በገጣሚዎቿም እንድትታወቅ ጠይቀዋል፡፡ የከተማዋ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊዎች ዝግጅቱን ወርሀዊ ለማድረግ እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ስዩም ስለጉዳዩ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ "ለወጣቶቹ ስልጠና ሰጥተን ያስጀመርነው እኛ ነን በየወሩ የስነ ጽሑፍ ምሽት ስላለንም ከእሱ ጋር በማቀናጀት እንዲቀጥል ማድረግ እንችላለን፡፡" ብለዋል፡፡

Read 3178 times