Saturday, 16 February 2013 12:09

የፖለቲካ ጥግ

Written by  ኤሊያስ
Rate this item
(4 votes)

* የካፒታሊዝም መሰረታዊ ችግር ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል አለማድረጉ ነው፡፡
የሶሻሊዝም መሰረታዊ በረከት ድህነትን እኩል ማከፋፈሉ ነው፡፡
ዊንስተን ቸርችል
(የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስትር የነበሩ)
* እቺ አገር የምትፈልገው ተጨማሪ ሥራ አጥ ፖለቲከኞችን ነው፡፡
ኢድዋርድ ላንግሌይ
(አሜሪካዊ አርቲስት)
* ህግ አውጪው ስብሰባ ላይ ሲሆን የማንም ሰው ህይወት፣ ነፃነት ወይም ንብረት አስተማማኝ አይሆንም፡፡
ማርክ ትዌይን
(አሜሪካዊ ደራሲና ጨዋታ አዋቂ)
* የፖለቲካ ፍላጐት የለህም ማለት ፖለቲካ አይፈልግህም ማለት አይደለም፡፡
ፔሪክለስ
(430 ከክ.ል በፊት)
* ምንም ዝግጅት አያስፈልገውም ተብሎ የሚታሰብ ሙያ አለ ከተባለ ምናልባት ፖለቲካ ብቻ ነው፡፡
ስቲሽንሰን
* ቀልዶችን መፍጠር አይጠበቅብኝም፡፡
መንግሥት የሚሰራውን እያየሁ ብቻ ሪፖርት አደርጋለሁ፡፡
ዊል ሮጀርስ
(አሜሪካዊ ኮሜዲያን)
* የመንግሥት የኢኮኖሚ አተያይ በጥቂት ሃረጐች ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ከተንቀሳቀሰ ግብር ጣልበት፣ መንቀሳቀሱን ከገፋበት ተቆጣጠረው፣ መንቀሳቀሱን ካቆመ ደጉመው፡፡
ሮናልድ ሬገን
(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ)
* ለመንግሥት ገንዘብና ሥልጣን መስጠት ለታዳጊ ወጣት ውስኪና የመኪና ቁልፍ እንደመስጠት ነው፡፡
ፒ.ጄ.ኦ’ሩርክ
(የግለሰብ ነፃነት ተሟጋች)
* መልካም ፖለቲከኛ ማግኘት ታማኝ ቤት ሰርሳሪ እንደማግኘት ነው - አይታሰብም፡፡
ኤች.ኤል ሜንከን

 

Read 3379 times