Print this page
Saturday, 16 March 2013 11:00

ሰራዊት በመድፈር ሙከራ ተከሷል መባሉ፣ “በሬ ወለደ” ነው አለ

Written by  ሰላም ገረመው
Rate this item
(28 votes)

በማስታወቂያና በፊልም ስራ የሚታወቀው አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ፤ በመድፈር ሙከራ አቤቱታ እንደቀረበበት መወራቱን በተመለከተ ተጠይቆ፤ “በሬ ወለደ ወሬ ነው” ሲል አስተባብሏል፡፡ የሠራዊት መልቲ ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሠራዊት ፍቅሬ ላይ አንዲት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለፖሊስ አቤቱታ ማቅረቧን የሚናገሩ ምንጮች፣ ባለፈው ቅዳሜ “ለማስታወቂያ ስራ እፈልግሻለሁ” ብሎ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ለመሳምና ለማሻሸት ሲሞክር አመለጥኩ” የሚል ነው ብለዋል፡፡

ምንጮቹ እንደሚሉት፤ የአቤቱታው ሂደት ተቋርጦ፣ ጉዳዩን በሽምግልና እንዲያልቅ መደረጉን ይናገራሉ፡፡ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ የቀረ ሲሆን፤ ሠራዊት በበኩሉ “ወሬው የበሬ ወለደ አሉባልታ ነው፤ ምንም የማውቀው ነገር የለም” ብሏል፡፡ “ካሁን በፊት ከወገቤ በላይ ብዙ ተብያለሁ፤ አሁን ደግሞ ከወገቤ በታች መጡ” በማለት ቀልድ አዘል አስተያየቱን ሠጥቷል - ሠራዊት፡፡

Read 9667 times Last modified on Saturday, 16 March 2013 13:23