Saturday, 16 March 2013 11:53

በብራና ሦስተኛ ዓመት ሰርፀና ዲያቆን ዳንኤል የጥናት ጽሑፍ ያቀርባሉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የንባብ ባህልን ማበረታታት ዓላማው አድርጎ መጋቢት 7 ቀን 2002 ዓ.ም ፕሮግራሙን የጀመረው “ብራና” የሬዲዮ ፕሮግራም ሦስተኛ ዓመቱን ነገ በ8 ሰዓት በጣይቱ ሆቴል ጃዝ አምባ አዳራሽ ሲያከብር፣የሙዚቃ ተመራማሪው አርቲስት ሠርፀ ፍሬስብሃት “ለንባብ ባህል መዳበር የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሚና” በሚል ርእስ ጥናቱን ያቀርባል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “የኢትዮጵያውያን የንባብ ልምድ በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ” በሚል ርእስ አስተውሎቶቹን በቃለ ምልልስ መልክ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡ በ “እናት ማስታወቂያ” እየተዘጋጀ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የሚቀርበው የሬዲዮ ዝግጅት ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት በሚተላለፈው እያንዳንዱ ዝግጅት ላይ ጥያቄ ለሚመልሱ 10 አድማጮች መፃሕፍት እየሸለመ መሆኑን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

Read 2987 times