Print this page
Saturday, 16 March 2013 12:24

‹‹...ESOG …21ኛ አመታዊ ጉባኤ... ››

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ (ከኢሶግ)
Rate this item
(2 votes)

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር 21ኛውን አመታዊ ጉባኤ አካሄደ፡፡ እንደኤሮፓውያን አቆጣጠር ማርች 4 እና 5 እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ የካቲት 25 እና 26 በአዲስ አበባ የተካሄደውን ጉባኤ የከፈቱት በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር ከበደ ወርቁ ናቸው፡፡ የኢትዮያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር 21ኛ አመታዊ ጉባኤ መሪ ቃል የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ማስፋፋት ሲሆን የባለሙያዎችን ድርሻም ይመለከታል፡፡ ዶ/ር ከበደ ወርቁ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የዘንድሮው መሪ ቃል ወቅታዊና ትክክለኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስ..ር አማካኝነት ለህብረተሰቡ የተሟላ የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲሰጥ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት አስቸጋሪና ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎችን ሽፋን ለመስጠት ጥረት በማድረግ የተሻለ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

በተለይም ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ከተካሄዱት የማሻሻያ እርምጃዎች የቤተሰብ እቅድ ዘዴም አንዱ ትኩረት የሚሻ በመሆኑ አገልግሎቱን ለማጠናከር የሚያስችል ዝግጅትን በሙያተኞች ዘንድ እንደሚፈጥር እሙን ነው፡፡ መንግስት ሴቶችን ማእከል ያደረገ የጤና ሽፋን እና የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎት የጀመረ ሲሆን በዚህም የሴቶችና ልጃገረዶች ጤና እንደሚሻሻል እሙን ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት እንደገለጹት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጤና ጋር በተያያዘ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ከስራዎቹ መካከልም... * እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2012 /ዓም በስምንት መስተዳድሮች በሚገኙ 22/ሆስፒታሎች ወደ 22.000/ሀያ ሁለት ሺህ የሚሆኑ ሴቶች ሕይወታቸው እንዲተርፍ የሚያስችል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት አግኝተዋል፡፡

* የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከህክምና ማእከላት እርቀው ለሚገኙና በተለያዩ አፋጣኝ እና የተሟላ የወሊድ አገልግሎትን ለሚሹ በቅርብ ለመስጠት እንዲቻል 47/አርባ ሰባት ጠቅላላ ሐኪሞችን እና የጤና መኮንኖችን በቀዶ ሕክምና የማዋለድ ዘዴ እንዲማሩ አድርጎአል፡፡ * ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ በሚደረገው ጥረት ማህበሩ በ6/መስተዳድሮች ውስጥ ከሚገኙ 54/ሀምሳ አራት የግል የህክምና ተቋማት ጋር በሚሰራው ስራ 103, 577/አንድ መቶ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሰባት ሴቶች ተመርምረው ቫይረሱ በደማቸው መኖር ያለመኖሩን እንዲያውቁና ቫይረሱ ከተገኘ ለልጆቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስችሎአቸዋል፡፡ * ማህበሩ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የተሟላ የህክምና አሰጣጥ እንዲጀመር ያደረገ ሲሆን በዚህ አመት ብቻም 1,219/ ሴቶች የጤና አገልግሎቱንና የስነልቡና ድጋፍን አግኝተዋል፡፡

* በተለያዩ መስተዳድሮች በሚገኙ 9/ዘጠኝ ሆስፒታሎችና በዙሪያቸው ከሚገኙ 45/ ጤና ጣብያዎች ጋር በመተባበር የእናቶችንና ጨቅላዎችን ሞት መንስኤ ማወቅ እና ጤንነትን ለመጠበቅ ስራ በመሰራት ላይ ነው፡፡ ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት አያይዘውም የኢሶግ 21ኛ አመታዊ ጉባኤ የአመቱ መሪ ቃል ያደረገውን የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎትን ማስፋፋትና የማዳረስ ተግባር እንዲሁም ሁኔታውን ከሙያተኞች ድርሻ አንጻር መመልከትን በተለይም የማህበሩ አባላት ለውጤቱ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር እስክንድር ከበደ በበኩላቸው መሪ ቃሉ የቤተሰብ እቅድ ዘዴን ማስፋፋትና የሙያተኞችን ድርሻ ያጎላበትን ምክንያት እንደሚከተለው ገልጸዋል፡፡

..... የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት የተመረጠበት ምክንያት የምእተ አመቱን ልማት ግብ ለማሳካት ከሚረዱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ማዳረስ የሚለው ይገኝበታል፡፡ በእናቶች እና ሕጻናት ጤና ላይ መሰራት ካለባቸው ነገሮች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ላይ ጠንክሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑ እሙን ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወሊድ መጠን የማወቂያ እና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን አጠቃቀም ወይንም ስርጭት የሚመለከተው ጥናት የተካሄደው እንደኤውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1994/ዓ/ም ነበር፡፡ በዚያም ጥናት ላይ እንደተገለጸው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት 4 % ብቻ ነበር ፡፡

በ2011ዓ/ም የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ግን ወደ 29 % ደርሶአል፡፡ በእርግጥ ቁጥሩ ከፍ ማለቱ የሚታይ ቢሆንም አሁን ካለው የህዝብ ቁጥር እና ፍላጎት አንጻር ገና ብዙ መስራት ይጠበቃል፡፡ በዚህም ምክንያት አገልግሎቱን በስፋት ለማዳረስና ግንዛቤውን በሙያተኞችም ይሁን በተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የአመቱ መሪ ቃል እንዲሆን መርጦታል፡፡ ከሙያተኞች ድርሻ ጋር በተያያዘ ዶ/ር እስክንድር እንደገለጹት... ‹‹... በአሁኑ ወቅት በትምህርት ቤቶች በሚሰጡ የትምህርት ዝርዝሮች ላይ በትክክል ተቀምጦ ትምህርቱ በመሰጠት ላይ አይደለም፡፡

አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሲያስተምሩ ሌሎች ግን አያስተምሩም፡፡ አልፎ አልፎ ግን ተማሪዎቻቸውን ወደሌላ የጤና ተቋም በመላክ ስለቤተሰብ እቅድ ዘዴ እንዲማሩ የሚያደርጉም አሉ ፡፡ ስለዚህም በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ የትምህርት ዘርፍ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት እንዴት ሊካተት እንደሚችል የቀረብ ጥናት ቢኖርም አሁን ባለው ሁኔታ ግን ትም ህርቱን እንደማያገኙ ተጠቁሞአል፡፡ ነገር ግን በየትኛውም የጤና ትምህርት በሚሰ ጥባቸው ተቋማት ስለቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ከቅድመ ምረቃ እስከ ድህረ ምረቃ በሚገባ በትምህርቱ ውስጥ ተካቶ ሊሰጥ እንደሚገባው የታመነበት ጉዳይ ነው፡፡ ›› የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት መረጃውና እውቀቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ሊኖር ቢችልም አገልግሎቱ ግን የለም የሚባልባቸው አጋጣሚዎች በርከት ያሉ ናቸው እንደ ዶ/ር እስክንድር ማብራሪያ፡፡ ‹‹ ...የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎት አልተገኝም ሊባልባቸው የሚችሉ ምክንያቶች አሉ፡፡

ከእነርሱም መካከል... •አገልግሎቱ የት እንደሚሰጥ አለማወቅ፣ •አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ እርቀት፣ •አገልግሎቱን ለማግኘት ከቦታው ሲደርሱም የአቅርቦት ችግር ማጋጠም የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት 29 % የደረሰ ቢሆንም 30 % የሚያህል ደግሞ አገልግሎቱን ያለማግኘት ችግር አለ፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን እየተጠቀሙ እና መጠቀም እየፈለጉ ባላገኙት መካከል ልዩነት የለም ማለት ይቻላል፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን መጠቀም የምእተ አመቱን የልማት ግቦች ለማሳካት እንደሚረዳ እሙን ነው፡፡ በኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር እድገት በአመት ወደ 3 % የነበረው በአሁኑ ጊዜ ወደ 2.6% ቀንሶአል፡፡ ነገር ግን ምንም ሳይሰራ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ እንደኤሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2050/ዓ/ም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁትር ወደ 150,000, 000/አንድ መቶ ሀምሳ ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል ፡፡

ሌሎቹ አገሮች የህዝብ ቁጥር ምጣኔ ላይ እየሰሩ ከሄዱ ኢትዮጵያ በህዝብ ቁጥር እድገትዋ በአለም ወደ አስረኛ ደረጃ እንደምትቀመጥ መረጃው ያሳያል፡፡የህዝብ ቁጥሩ በዚህ መልክ ከጨመረ ደግሞ ምጣኔ ሀብቱንና ህብረተሰቡን ማገናኘት ስለማይቻል ከፍተኛ ችግር ይከሰታል፡፡ •ድህነትን መቀነስ፣ ኢኮኖሚን ማሳደግ ያስቸግራል፣ •ትምህርትን ፣ጤናን ...ወዘተ ማዳረስ አይቻልም፣ •የጾታን እኩልነት ተግባራዊ ለማድረግ ያስቸግራል፣ •የእናቶችን እና የጨቅላዎችን ጤና መጠበቅ አያስችልም፣ •ልማትን እውን ማድረግ አይቻልም...ወዘተ ፣ ባጠቃላይም የህዝብ ቁጥር እድገቱ ከታሰበው በላይ ከሆነ በምእተ አመቱ የልማት ግቦች ላይ የተጠቀሱ አስፈላጊ ነገሮችን ለማከናወን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡

ስለዚህም የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቱን በተገቢው ሁኔታ ማዳረስ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እና አባላቱ መሪ ቃሉን በመተግበር ረገድ ሊወጡት የሚገባቸው ድርሻ አላቸው፡፡ •ለቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት በስፋት ማዳረስ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በዘርፉ እንዲታወቁ ማድረግ ፣ •ፕሮጀክት ቀርጾ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ፣ •ስልጠናዎችን ማካሄድ •በመገናኛ ብዙሀን ለህብረተሰቡ ተገቢውን መረጃ መስጠት እና ባጠቃላይም ህብረተሰቡ ያለውን አገልግሎት አውቆ እንዲጠቀም የሚያስችሉ መረጃዎችን መስጠት ...ወዘተ የመሳሰሉት ላይ መሳተፍ ይጠበቅበታል፡፡

Read 2838 times