Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 07 November 2011 13:36

በሴካፋ ሻምፒዮና ዝግጅትና ምክር ቤት ታንዛኒያ ገዘፈች ሚቾ ሩዋንዳን ይዟል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከወር በኋላ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሊካሄድ የነበረው የሴካፋ ሲኒዬር ቻሌንጅ ካፕ በአንድ ሳምንት እንዲቀደም የፕሮግራም ሽግሽግ መደረጉን የሴካፋ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የሴካፋ ሻምፒዮና 2011 ታስከር ቻሌንጅ ካፕ ካፕ ሲባል ሰረንጂቲ ብሬወሪስ የተባለው ቢራ ጠማቂ ኩባንያ በስፖንሰርኺፕ 823 ሚሊዮን የታንዛኒያ ሽልንግ ሰሞኑን አበርክቷል፡፡ የስፖንሰርሺፕ ድጋፉ ከባለፋው ዓመት በ50 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ከ3 ሳምንት በዃላ ለሚደረገው ሻምፒዮና የምድብ ድልድል በሚቀጥለው ረቡዕ በዳሬሰላም ይወጣል፡፡

በውድድሩ ላይ በተጋባዠነት ሊሳተፉ የነበሩት የምእራብ አፍሪካዎቹ ናይጄርያ እና ካሜሮን ተሳትፏቸውን ሰርዘዋል፡፡ የሴካፋ ምክር ቤት ከደቡብ አፍሪካ፤ ከኮትዲቯር፤ ከማላዊና ከዛምቢያ ከቀረበለት የተሳትፎ ጥያቄ የሁለቱን ለመቀበል እያጤነ ነው፡፡ ናይጄርያና ካሜሮን በሴካፋ ሻምፒዮና ላይ መሳተፍ ያልፈለጉበትን ምክንያት ግልፅ አላደረጉም፡፡ በ2011 ሴካፋ ሲኒዬር ቻሌንጅ ካፕ ላይ 11 የዞኑ አገራት እንደሚካፈሉ ሲጠበቅ እነሱም ሱዳን፤ ኢትዮጵያ፤ ኡጋንዳ፤ ኬንያ፤ ኤርትራ፤ ሩዋንዳ፤ ብሩንዲ፤ ዛንዚባር፤ ጅቡቲ፤ ሶማሊያና ሻምፒዮናውን ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የምታስተናግደው ታንዛኒያ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት ታስካር ቻሌንጅ ካፕ ተብሎ በተደረገው የዞኑ ሻምፒዮና ታንዛኒያ ኮትዲቯርን 1ለ0 አሸንፋ ለሶስተኛ ጊዜ ሻምፒዮን መሆኗ ሲታወስ ሌሎቹ ተጋባዥ አገራት ዛምቢያና ማላዊ ነበሩ፡፡
ከምስራቅ አፍሪካ አገራት መካከል በ2014 እኤአ ብራዚል ለምታስተናግደው 20ኛ ዓለም ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኖችን ለማብቃት እየተዘጋጀ ያለው ሴካፋ ለአፈሪካ ዋንጫ ባለፈችው ሱዳንና ባለቀ ሰዓት ጉሮሮ ለጉሮሮ ተያይዘው የወደቁት ኡጋንዳና ኬንያ እንዲሁም ሩዋንዳና ታንዛኒያ ላይ ተስፋ ቢያደርግም የኢትዮጵያ የሶማሊያና የጅቡቲ ኳስ መዳከም እያሳሰበው ነው፡፡ የሴካፋ ምክር ቤት ከወር በሃላ የዞኑን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራ ፕሬዝዳንት ምርጫ ያደርጋል፡፡ የታንዛንያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንትና ያለፈውን 4 ዓመት በፕሬዝዳንትነት የቆዩት የነበሩት ሊዮዳር ቴንጋ ዋና እጩ ቢሆኑም የምክር ቤቱ ፀሃፊ ኬንያዊው ኒኮላስ ሙንሶኜም ሳይወዳደሩ አይቀርም፡፡
በተያያዘ ዜና ሰርቢያዊው ሰርድጄዬቪች ሚሉቲን ሙቾ የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድንን ያዘ፡፡ ሚቾ ከሩዋንዳ ለስፖርት አድማስ በላከው መግለጫ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነቱን በአፍሪካ ተምሳሌታዊ እድገት በምታሳየው ሩዋንዳ ላይ መጀመሩ እንዳጓጓው ገልጿል፡፡ የ42 ዓመቱ ሚቾ ላለፉት 10 ዓመታት በኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨምሮ በሩዋንዳ፤ ኡጋንዳ፤ ደቡብ አፍሪካና ሱዳን በሚገኙ ክለቦች ዋና አሰልጣኝ ሆኖ በሊግና አህጉራዊ ውድደሮች ውጤታማ ሆኗል፡፡
ሚቾ የሩዋንዳ አሰልጣኝነቱን ባለፈው ሰኞ የተረከበው ከሁለት ወር በፊት ስራቸውን የለቀቁ ጋናዊ በመተካት ነበር፡፡ ሚቾ በሩዋንዳ አሰልጣኝነት ከሳምንት በኋላ ለዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከኤርትራ ጋር በመጫወት ስራውን ሲጀምር በታንዛኒያ የሚካሄደው የሴካፋ ሻምፒዮናም ከጅምሩ ይፈተናል፡፡ የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድንን በ2013 ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የማብቃት እቅድ የተያዘበት ሚቾ በዚህ ቅድመ ማጣርያ ከናይጄርያ ጋር ይጋጠማል፡፡

 

Read 3255 times Last modified on Monday, 07 November 2011 13:39