Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 12 November 2011 08:18

ዘውዲቱ የፋሽን ዲዛይን ተቋም ተማሪዎች ያስመርቃል

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ዘውዲቱ የፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ ተቋም ዛሬ 110 ተማሪዎችን ያስመርቃል፡፡ ለ32ኛ ጊዜ በልብስ ፋሽን ዲዛይን፣ በመሠረታዊ ልብስ ስፌትና በጥልፍ ሙያ የሠለጠኑት ተማሪዎች የሚመረቁት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ነው፡፡ ማሰልጠኛ ተቋሙ የዛሬ ሠላሳ ሦስት ዓመት የተቋቋመ ነው፡፡  

ግጥምን በጃዝ ምሽት ረቡዕ ይቀርባል
የመለከት ባንድ ከወጣት ገጣሚያን ጋር የሚያቀርበው ግጥምን በጃዝ ምሽት ረቡዕ ከምሽቱ 12፡30 ሊቀርብ ነው፡፡ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በሚቀርበው ዝግጅት ሥራዎቻቸውን ከሚያቀርቡ ገጣሚያን መካከል ገጣሚና ተዋናይት ሜሮን ጌትነት፣ ሠዐሊና ገጣሚ ቸርነት ወ/ገብርኤል፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ አበባው መላኩ፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ በረከት በላይነህ፣ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ እና ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ ይገኙበታል፡፡

Read 3376 times

Latest from