Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 November 2011 08:22

“ርዕዮት” አንደኛ ዓመቱን በቀጥታ ስርጭት ያከብራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ርእዮት” የሬዲዮ ዝግጅት አየር ላይ መዋል የጀመረበትን አንደኛ ዓመት በዓል ነገ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን አካባቢ በሚገኘው ወይን ኢትዮጵያ የባህል አዳራሽ” ያከብራል፡፡ የምስረታውን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የሚቀርበው ዝግጅት መገናኛ ብዙሃንን የትልልቅ ሀሳቦች መፍለቂያ ማድረግና ማህበረሰቡን እንደሚመስሉ ማሳየት ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡
ነገ ከቀኑ 4፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት የሚቀርበውን የቀጥታ ስርጭት ዝግጅቶች አስመልክቶ የጠየቅናቸው የ”ርዕዮተ” ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛና ገጣሚ ቴዎድሮስ ፀጋዬ፤ በነገው ልዩ ዝግጅት የአይነስውራን የሙዚቃ ቡድን ጣዕመ ዜማዎችን እንደሚያሰማና አርቲስት መርዓዊ ስጦት፣ ንዋይ ደበበ፣ ሠራዊት ፍቅሬ፣ ሐይሉ ፀጋዬ እና ሌሎችም እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀውልናል፡፡ “ርእዮት” በኤፍኤም አዲስ 97.1 ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 4 ሰዓት እስከ 6፡30 የሚተላለፍ የሬዲዮ ፕሮግራም ነው፡፡

Read 2478 times