Print this page
Monday, 27 May 2013 13:14

ጆን ኬሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ይወያያሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ “ዩዝ ኮኔክት” በሚል አጀንዳ ዙርያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በነገው ዕለት እንደሚወያዩ ተገለፀ፡፡ በዩኒቨርስቲው አይ ኤስ ላይብረሪ ከጠዋቱ ከ2፡30 ጀምሮ የሚካሄደውን ውይይት የምትመራው የቢቢሲዋ ታዋቂ ጋዜጠኛ ዘይና በዳዊ እንደሆነች ታውቋል፡፡

ጆን ኬሪ፤ አሜሪካንን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ከጆርጅ ቡሽ ጋር የምርጫ ፉክክር አድርገው በጠባብ ልዩነት መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጆን ኬሪ ባለፈው አመት የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉትን የቀድሞዋን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተንን ተክተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

Read 1835 times