“ኢያሪኮ 777” የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መፅሐፍ በአዘርግ (Adamu G) ተዘጋጅቶ ለንባብ በቃ፡፡
ደራሲው 70 በመቶ ምናባዊ ፈጠራ፣ 30 በመቶ እውነተኛ ገጠመኝ ላይ የተመሰረተ አዝናኝ መፅሐፌን በማህበራዊ ድረገፅ (ፌስቡክ) ላይ ማስተዋወቄ ለመፅሃፉ ሸያጭ አግዞኛል በማለት የመፅሃፉ ገበያ መድራቱን ተናግረዋል፡፡ 146 ገፆች ያሉት መፅሐፍ በ30 ብር እየተሸጠ ነው፡፡በሌላም በኩል በሴቶች ጥቃት ላይ የሚያተኩረው “ያልተደመጡ ነፍሶች” የግጥም መድበል ዛሬ ከጧቱ ሦስት ሰዓት በሐገር ፍቅር ትያትር ቤት ይመረቃል፡፡ በገጣሚ ዘመላክ ብርሃኑ የተፃፈው መጽሐፍ በአዘጋጁና በአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ቢሮ ትብብር ለሕትመት የበቃ ነው፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና