Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 November 2011 08:26

አንጋፋው ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን የ60 ሻማ እንግዳ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ሬዲዮ በተለይም በ”ከመፃህፍት ዓለም”፣ “እሁድ ጠዋት” እና “የኪነጥበባት ምሽት” አቅራቢነቱ ታዋቂ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን ለሐዋሳ የኪነጥበብ አፍቃሪዎች ልምዱን ለማጋራት የ60 ሻማ 35ኛ የክብር እንግዳ ሆነ፡፡ ነገ በሐዋሳ ቤተሰብ መምርያ ማህበር አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት በሚቀርበው ዝግጅት የጋዜጠኛው የሕይወት ታሪክ ለታዳሚዎች የሚቀርብ ሲሆን በመድረክ ቃለምልልስ እና ከታዳሚዎች ለሚቀርቡለት ጥያቄና አስተያየቶች መልስ በመስጠት ልምዱን ያጋራል፡፡

ከዚህም ሌላ በዝግጅቱ በአማተር ገጣሚያን ግጥሞች የሚቀርቡ ሲሆን የማህበሩ አባል የሆነችው የደራሲ ሐይማኖት ሙሉጌታ “ና” የተሰኘ የግጥም መድበል እንደሚመረቅ የ60 ሻማ ሥነፅሁፍ ማህበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በሱፍቃድ ተገኝ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡አንጋፋው ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን በአሁኑ ጊዜ “ደጀኔ ጥላሁን ፕሮሞሽን” የሚል ድርጅት የከፈተ ሲሆን በሸገር ኤፍኤም 102.1 “የአዘቦት ተረክ” አዘጋጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡

 

Read 4479 times Last modified on Saturday, 12 November 2011 08:28