Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 12 November 2011 08:28

በዓለም አቀፍ ፊልም አውደርእዩ 17 ፊልሞች ይወዳደራሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ስድስተኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባ ባህልና ትያትር አዳራሽ በተከናወነ ሥነ ሥርዓት የተጀመረ ሲሆን ካለፈው ሕዳር 2003 ዓመተ ምህረት ወዲህ ከተሰሩት ሰማንያ ያህል ፊልሞች አስራ ሰባቱ ብቻ ለሽልማት እንደሚወዳደሩ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ ለመወዳደር ያልተመዘገቡ አንዳንድ ፊልም ሰሪዎች ስለ ፌስቲቫሉ አልሰማንም ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል አዘጋጅ “ሊንኬጅ አርትስ ሪሶርስ ሴንተር” ዳይሬክተር አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ በበኩላቸው በሬዲዮና በጋዜጣ በቂ ቅስቀሳ ማድረጋቸውንና አንዳንድ ተሳታፊዎች አውደርእይን ተወዳድሮ የማሸነፊያ ብቻ አድርገው ስለሚቆጥሩ ተወዳድሬ ባላሸንፍስ በሚል ፍራቻ ሳይመዘገቡ ሊቀሩ እንደሚችሉ ያላቸውን ግምት ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በአውደርእዩ ከሚሳተፉ ባለፊልሞች መካከል የ”ብድራት” ፊልም አዘጋጅ አቶ ምኒሊክ አራጋው “ውድድር ካለ ተወዳዳሪ ቢያሸንፍ ደስ ይለዋል፤ ሚዛናዊ ዳኝነት ካለ ባናሸንፍም ቅር አይለንም” ብለዋል፡፡


ስለ አውደርእዩ ኢትዮጵያዊነትና አለም አቀፋዊነት የተጠየቁት አቶ ይርጋሸዋ፤ ዓለም አቀፍ የሚያደርገውም በተሳትፎና በእውቅና በብዙ ሃገራት የተሳተፉ ፊልሞች፣ ታዋቂ ፊልም ሰሪዎችና ባለሙያዎች ስለሚሳተፉና ልምድ ልውውጥ ስለሚኖር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 24 ፊልሞች በአውደ ርእዩ ለመሳተፍ ከውጭ ሀገራት የመጡ ሲሆን በአውደ ርእዩ ሂደት ለታዳሚዎች ይቀርባሉ፡፡
በሕዝብ ድምፅ የሚመረጠው ፊልም በአጭር መልእክት ማስተላለፊያ ቁጥር 8010 በየፊልሙ ኮድ ለአንድ ጊዜ አንድ ብር ከሃምሳ በመክፈል መምረጥ እንደሚቻልና በተደጋጋሚ መምረጥም እንዳልተከለከ ከአዘጋጆቹ መረዳት ተችሏል፡፡

 

Read 3328 times Last modified on Saturday, 12 November 2011 08:29

Latest from