Saturday, 12 November 2011 08:41

“ከመቶ እርግዝናዎች 15 % ያህሉ እክል ይገጥማቸዋል”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ዩኒሴፍ እና የአለም የጤና ድርጅት (WHO) እንዳወጡት መረጃ ከሆነ እንደውጭው አቆጣጠር በ1990 ዓ/ም በአለም 585000 አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ የሚሆኑ እናቶች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ከተጠቀሰው የሞት ቁጥር 99 የሚሆኑት በታዳጊ አገሮች መሆናቸው ተረጋግጦአል፡፡ በኢትዮጵያ እንደውጭው አቆጣጠር በ2000 ዓ/ም የእናቶች ሞት ቁጥር ከ100000 አንድ መቶ ሺህ 871 ስምንት መቶ ሰባ አንድ ያህል ሲሆን በ2005 በተደረገው ጥናት ደግሞ ከአንድ መቶ ሺህ እናቶች ወደ 673 ስድስት መቶ ሰባ ሶስት ያህሉ በአንድ አመት ጊዜ እንደሚሞቱ ተረጋግጦአል፡፡

ይህም ቁጥር በታዳጊ አገሮች ከተመዘገበው ከፍተኛው መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡በሚሊኒየሙ የልማት ግብ እቅድ መሰረት የእናቶች ሞት እንደውጭው አቆጣጠር ከ1990-2015 ድረስ ከነበረበት በ75 እንዲቀንስ ይጠበቃል፡፡ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ደግሞ እናቶች ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ጊዜ እንዲሁም በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በሁዋላ የተሟላ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢው እርምጃ ነው፡፡ የእናቶች ጤና ተጠበቀ ማለት ደግሞ የሴቶችን ጤና ሁኔታ ብቻ የሚያመላክት ሳይሆን በአጠቃላይ በአገር ደረጃ ያለውን ጤና አጠባበቅ ብቃት የተሟላ መሆንን እና ውጤታማነትን የሚያሳይ እንዲሁም የመላውን ህብረተሰብ ደህንነት የሚያመላት ነው፡፡ 
በኢትዮጵያ ቅድመ ወሊድ ፣በወሊድና ድህረ ወሊድ ምን ያህል እናቶች የህክምና ክትትል ያደርጋሉ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ወደ ኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ተጉዘናል ፡፡ ዶ/ር ታደሰ ከተማ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ መልስ እንዲሰጡን ጋብዘናል፡፡
ዶ/ር ታደሰ ከተማ እንደገለጹት ከሆነ የእናቶች ጤና መጠበቅ ሲባል በመቀጠል የተገለጹትን አገልግሎቶችን ያካትታል፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት፣
የቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል፣
ከአረገዙ በሁዋላ የህክምና ክትትል፣
የማዋለድ አገልግሎት እና ከወለዱ በሁዋላ የሚሰጥ አገልግሎት
ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚሰጠውን አገልግሎት (PMTCT) ይጨምራል፡፡
ቅድመ ወሊደ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ የሚባሉት እናቶች ከአጠቃላዩ ሲታይ ወደ 80 አካባቢ ናቸው፡፡ ይህም ቁጥር ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ይህም በአገር ደረጃ የተሰማሩ የጤና ኤክስንሽን ባለሙያዎች በጤና ኬላዎች እና እናቶች ባሉበት ቦታ ሁሉ በየመኖሪያ ቤቱ ጭምር አገልግሎቱን መስጠት በመቻላቸው ነው፡፡ ከዛሬ አምስት አመት በፊት የነበረው አገልግሎት ከ30 በታች የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ይህ አገልግሎት በእርግጥ በመላው ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ሁኔታ አለ ለማለት የጤና አገልግሎቱን ተደራሽነት የሚወስኑ ዋና ዋና ነገሮች መኖራቸው እሙን ነው፡፡
1/አቅርቦት ፡-
ከአቅርቦት አኩዋያ ያሉ ሁኔታዎች በዝርዝር ሲታዩ የጤና ተቋማት መኖር ፣ወደጤና ተቋማት የሚወስድ መንገድ መኖር ፣ አምቡላንስ ወይንም ተሸከርካሪ መኖር ፣ በጤና ተቋማት ውስጥ ያሉት ባለሙያዎች አገልግሎቱን የመስጠት ብቃት እንዲሁም አቅርቦት መኖሩ ...ሁሉ ከቦታ ቦታ ያለውን የጤና አገልግሎቱን ደረጃ የሚያለያዩ ይሆናሉ፡፡
2/ተጠቃሚነት፡-
ከተጠቃሚነት አንጻር ተጠቃሚዎች የጤና አገልግሎቱ በመኖሩ ሊጠቀሙ የሚችሉ ሲሆን ባለመኖሩ ደግሞ ሳይጠቀሙ ሊቀሩ ይችላሉ፡በሌላ በኩል ደግሞ አገልግሎቱ እያለም የማይጠቀሙበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ ይህ የሚወሰነው በተጠቃሚው ግንዛቤ ማነስና ከፍ ማለት ነው፡፡ የጤና አገልግሎቱን ሊያገኝ የሚገባው ሰው የጤና ተቋምን በመጠቀሙ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ያውቀዋል? ወይንስ አያውቀውም? ስለአገ ልግሎቱስ ጥራት ያለው ግንዛቤ ምን ይመስላል? የሚለው በተለያዩ አካባቢዎች ለሚሰጠው አገልግሎት እንደመመዘኛ ሊያገለግል ይችላል፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው ቅድመ ወሊድ 80 እናቶች ወደጤና ተቋም በመሄድ የእርግዝና ክትትል የሚያደርጉ ቢሆንም በወሊድ ጊዜ ወደሕክምና ተቋማቱ በመሄድ አገልግሎቱን የሚያገኙት 18 የሚሆኑት ናቸው፡፡ በእርግዝና ጊዜ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩት እናቶች ለምን በወሊድ ጊዜ ወደ ጤና ተቋማቱ አልሄዱም የሚለው ሲታይ... አሉ... ዶ/ር ታደሰ ከተማ ...የጤና ተቋማቱ እና ህብረተሰቡ መካከል ያለው የቦታ እርቀት ፣ የመጓጓዣ እጥረት፣ የተጠቃሚዎቹ ግንዛቤ የመሳሰሉት ሁኔታዎች ወላዶቹ በአካባቢያቸው ተወስነው በልምድ አዋላጅና በቤተሰብ በሚደረግላቸው እገዛ የሚወልዱበት አጋጣሚ መኖሩ እሙን ነው፡፡
ዶ/ር ታደሰ ከተማ እንደገለጹት እናቶች በወሊድ ጊዜ የጤና ተቋማቱን ያለመጠቀማቸው ሁኔታ በህይወትና በአካላቸው ጭምር ለጉዳት የሚያጋልጣቸው ሲሆን ይህ እንዳይሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስር አስፈላጊው ጥረት ሁሉ እንዲደረግ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ የእናቶችን ጤና መጠበቅ በምእተ አመቱ የልማት ግብ በአምስተኛ ተራ ቁጥር የሚገኝ ሲሆን ይህንን እውን ለማድረግ እንዲቻል የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር በጤና ሴክተር የልማት እቅዱ እንደ አንድ አንኩዋር ስራ አድርጎ ወስዶታል ፡፡ ለዚህም የተለያዩ የትግበራ ዘዴዎቹን ቀይሶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለምሳሌም እስከ 20015 ደረስ በጤና ተቋማት ውስጥ የሚወልዱት ሴቶች ከ18 ወደ 60 እንዲያድግ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ይህንን እቅድም ከግብ ለማድረስ የተለያዩ ዘዴዎች የተቀየሱ ሲሆን ከነዚህም አንዱ የጤና ተቋማትን ማስፋፋት ነው፡፡ እንደውጭው አቆጣጠር በ2015 ዓ/ም ወደ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ3200 የጤና ተቋማት እንዲኖሩና ስብጥሩም 5000 አምስት ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች አንድ የጤና ኬላ 25000ሀያ አምስት ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች አንድ የጤና ጣብያ 100000 አንድ መቶ ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች አንድ የገጠር ሆስፒታል ለመገንባት እና አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል አስፈላጊው እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ ሌላው በሙያው ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች በጤና ተቋማቱ ውስጥ እንዲኖሩ ማስቻል ሲሆን የተሟላ የጤና አገልግሎትን ለእናቶች በተቻለ መጠን በሁሉም አካባቢ ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ሌላው እናቶች በወሊድ ጊዜ በጤና ተቋማቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ የማያስችላቸው ችግር የመጉዋጉዋዣ ሁኔታ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ስምንት መቶ የሚሆኑ ወረዳዎች ያሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ወረዳ ውስጥ አንዳንድ የአምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች እንዲኖሩ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው፡፡ የመንገድ ስራው በእርግጥ የጤና ሴክተሩ ስራ ባይሆንም ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ተቋማት እየተንቀሳቀሱ ያሉበት ስለሆነ በቅርቡ ህብረተሰቡ ወዳለበት በቀላሉ በመድረስ አገልግሎ ቱን ለመስጠት እና በ2015 የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ የታቀደውን ግብ ለመምታት ያስችላል ተብሎ ይታሰባል እንደ ዶ/ር ታደሰ ከተማ ማብራሪያ፡፡
የእናቶቹን ብቻ ሳይሆን የህጻናቱን ጤና ጭምር ለመጠበቅም የሚያስችል አሰራር መኖር እንዳለበት የታመነ በመሆኑ እናቶች ከወለዱ በበሁዋላ ለራሳቸውም ይሁን ለልጃቸው ተገቢውን ክትትል ለማድረግ ወደህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋቸዋል፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመቶ እርግዝናዎችውስጥ15 ያህሉ እክል የሚገጥማቸው ሲሆን 15 ከሚሆኑት እክሎች ውስጥ ብዙዎቹ የሚከሰቱት ከወሊድ በሁዋላ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከወሊድ በሁዋላ ክትትል የሚያደርጉት እናቶች ከመቶ ወደ 34 የሚያህሉት ናቸው፡፡ በእርግጥ ቀደም ሲል ከነበረው ቁጥር በመጠኑ የተሻሻለ በመሆኑ እንጂ 34 ሲባል ሙሉ በሙሉ ጥሩ ነው የሚባል አይደለም፡፡ የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር መቀነስ የምእተ አመቱ የልማት ግብ እቅድ ሲሆን ቀደም ሲል የነበረውን ቁጥሩን በ20015 ከመቶ ሺህ እናቶች ወደ 267 ዝቅ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህም አንጻር የድህረወሊድ አገልግሎትን ተደራሽነት በማሻሻል በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ከ34 ወደ 78 ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡
ዶ/ር ታደሰ ከተማ ከኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ በስተመጨረሻው እንደገለጹት የእናቶች ጤና አገልግሎት ሲባል ከጤና ተቋሙ ሰራተኞች ጋር ብቻ የተያያዘ ሳይሆን የሚመለከተው ሁሉ ሊያተኩርበት የሚገባው ነው፡፡ የመገናኛ ብዙሀን በየበኩላቸው የጤና ተቋማትን መጠቀም ለእናቶች የሚሰጠውን አገልግሎት በማጉላት ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በህብረተሰብ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች እንዲሁም የተለያዩ አካላት እናቶችን ወደ ህክምና ተቋማቱ በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠ ቃሚ እንዲሆኑ በመምከርና ሁኔታዎችን በማሻሻል በጋራ እንቅስቃሴ ቢደረግ የእናቶችን በእርግዝናና በወሊድ ጊዜ መታመም መሞት የመሳሰለውን አደጋ ለመቀነስ ስለሚያስችል ማንም ወደጎን ሊተወው የማይችለው የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ማስገንዘብ እወዳለሁ ብለዋል ዶ/ር ታደሰ ከተማ፡፡ዩኒሴፍ እና የአለም የጤና ድርጅት (WHO) እንዳወጡት መረጃ ከሆነ እንደውጭው አቆጣጠር በ1990 ዓ/ም በአለም 585000 አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ የሚሆኑ እናቶች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ከተጠቀሰው የሞት ቁጥር 99 የሚሆኑት በታዳጊ አገሮች መሆናቸው ተረጋግጦአል፡፡
በኢትዮጵያ እንደውጭው አቆጣጠር በ2000 ዓ/ም የእናቶች ሞት ቁጥር ከ100000 አንድ መቶ ሺህ 871 ስምንት መቶ ሰባ አንድ ያህል ሲሆን በ2005 በተደረገው ጥናት ደግሞ ከአንድ መቶ ሺህ እናቶች ወደ 673 ስድስት መቶ ሰባ ሶስት ያህሉ በአንድ አመት ጊዜ እንደሚሞቱ ተረጋግጦአል፡፡ ይህም ቁጥር በታዳጊ አገሮች ከተመዘገበው ከፍተኛው መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡በሚሊኒየሙ የልማት ግብ እቅድ መሰረት የእናቶች ሞት እንደውጭው አቆጣጠር ከ1990-2015 ድረስ ከነበረበት በ75 እንዲቀንስ ይጠበቃል፡፡ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ደግሞ እናቶች ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ጊዜ እንዲሁም በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በሁዋላ የተሟላ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢው እርምጃ ነው፡፡ የእናቶች ጤና ተጠበቀ ማለት ደግሞ የሴቶችን ጤና ሁኔታ ብቻ የሚያመላክት ሳይሆን በአጠቃላይ በአገር ደረጃ ያለውን ጤና አጠባበቅ ብቃት የተሟላ መሆንን እና ውጤታማነትን የሚያሳይ እንዲሁም የመላውን ህብረተሰብ ደህንነት የሚያመላት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ቅድመ ወሊድ ፣በወሊድና ድህረ ወሊድ ምን ያህል እናቶች የህክምና ክትትል ያደርጋሉ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ወደ ኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ተጉዘናል ፡፡ ዶ/ር ታደሰ ከተማ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ መልስ እንዲሰጡን ጋብዘናል፡፡
ዶ/ር ታደሰ ከተማ እንደገለጹት ከሆነ የእናቶች ጤና መጠበቅ ሲባል በመቀጠል የተገለጹትን አገልግሎቶችን ያካትታል፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት፣
የቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል፣
ከአረገዙ በሁዋላ የህክምና ክትትል፣
የማዋለድ አገልግሎት እና ከወለዱ በሁዋላ የሚሰጥ አገልግሎት
ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚሰጠውን አገልግሎት (PMTCT) ይጨምራል፡፡
ቅድመ ወሊደ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ የሚባሉት እናቶች ከአጠቃላዩ ሲታይ ወደ 80 አካባቢ ናቸው፡፡ ይህም ቁጥር ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ይህም በአገር ደረጃ የተሰማሩ የጤና ኤክስንሽን ባለሙያዎች በጤና ኬላዎች እና እናቶች ባሉበት ቦታ ሁሉ በየመኖሪያ ቤቱ ጭምር አገልግሎቱን መስጠት በመቻላቸው ነው፡፡ ከዛሬ አምስት አመት በፊት የነበረው አገልግሎት ከ30 በታች የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ይህ አገልግሎት በእርግጥ በመላው ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ሁኔታ አለ ለማለት የጤና አገልግሎቱን ተደራሽነት የሚወስኑ ዋና ዋና ነገሮች መኖራቸው እሙን ነው፡፡
1/አቅርቦት ፡-
ከአቅርቦት አኩዋያ ያሉ ሁኔታዎች በዝርዝር ሲታዩ የጤና ተቋማት መኖር ፣ወደጤና ተቋማት የሚወስድ መንገድ መኖር ፣ አምቡላንስ ወይንም ተሸከርካሪ መኖር ፣ በጤና ተቋማት ውስጥ ያሉት ባለሙያዎች አገልግሎቱን የመስጠት ብቃት እንዲሁም አቅርቦት መኖሩ ...ሁሉ ከቦታ ቦታ ያለውን የጤና አገልግሎቱን ደረጃ የሚያለያዩ ይሆናሉ፡፡
2/ተጠቃሚነት፡-
ከተጠቃሚነት አንጻር ተጠቃሚዎች የጤና አገልግሎቱ በመኖሩ ሊጠቀሙ የሚችሉ ሲሆን ባለመኖሩ ደግሞ ሳይጠቀሙ ሊቀሩ ይችላሉ፡በሌላ በኩል ደግሞ አገልግሎቱ እያለም የማይጠቀሙበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ ይህ የሚወሰነው በተጠቃሚው ግንዛቤ ማነስና ከፍ ማለት ነው፡፡ የጤና አገልግሎቱን ሊያገኝ የሚገባው ሰው የጤና ተቋምን በመጠቀሙ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ያውቀዋል? ወይንስ አያውቀውም? ስለአገ ልግሎቱስ ጥራት ያለው ግንዛቤ ምን ይመስላል? የሚለው በተለያዩ አካባቢዎች ለሚሰጠው አገልግሎት እንደመመዘኛ ሊያገለግል ይችላል፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው ቅድመ ወሊድ 80 እናቶች ወደጤና ተቋም በመሄድ የእርግዝና ክትትል የሚያደርጉ ቢሆንም በወሊድ ጊዜ ወደሕክምና ተቋማቱ በመሄድ አገልግሎቱን የሚያገኙት 18 የሚሆኑት ናቸው፡፡ በእርግዝና ጊዜ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩት እናቶች ለምን በወሊድ ጊዜ ወደ ጤና ተቋማቱ አልሄዱም የሚለው ሲታይ... አሉ... ዶ/ር ታደሰ ከተማ ...የጤና ተቋማቱ እና ህብረተሰቡ መካከል ያለው የቦታ እርቀት ፣ የመጓጓዣ እጥረት፣ የተጠቃሚዎቹ ግንዛቤ የመሳሰሉት ሁኔታዎች ወላዶቹ በአካባቢያቸው ተወስነው በልምድ አዋላጅና በቤተሰብ በሚደረግላቸው እገዛ የሚወልዱበት አጋጣሚ መኖሩ እሙን ነው፡፡
ዶ/ር ታደሰ ከተማ እንደገለጹት እናቶች በወሊድ ጊዜ የጤና ተቋማቱን ያለመጠቀማቸው ሁኔታ በህይወትና በአካላቸው ጭምር ለጉዳት የሚያጋልጣቸው ሲሆን ይህ እንዳይሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስር አስፈላጊው ጥረት ሁሉ እንዲደረግ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ የእናቶችን ጤና መጠበቅ በምእተ አመቱ የልማት ግብ በአምስተኛ ተራ ቁጥር የሚገኝ ሲሆን ይህንን እውን ለማድረግ እንዲቻል የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር በጤና ሴክተር የልማት እቅዱ እንደ አንድ አንኩዋር ስራ አድርጎ ወስዶታል ፡፡ ለዚህም የተለያዩ የትግበራ ዘዴዎቹን ቀይሶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለምሳሌም እስከ 20015 ደረስ በጤና ተቋማት ውስጥ የሚወልዱት ሴቶች ከ18 ወደ 60 እንዲያድግ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ይህንን እቅድም ከግብ ለማድረስ የተለያዩ ዘዴዎች የተቀየሱ ሲሆን ከነዚህም አንዱ የጤና ተቋማትን ማስፋፋት ነው፡፡ እንደውጭው አቆጣጠር በ2015 ዓ/ም ወደ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ3200 የጤና ተቋማት እንዲኖሩና ስብጥሩም 5000 አምስት ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች አንድ የጤና ኬላ 25000ሀያ አምስት ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች አንድ የጤና ጣብያ 100000 አንድ መቶ ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች አንድ የገጠር ሆስፒታል ለመገንባት እና አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል አስፈላጊው እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ ሌላው በሙያው ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች በጤና ተቋማቱ ውስጥ እንዲኖሩ ማስቻል ሲሆን የተሟላ የጤና አገልግሎትን ለእናቶች በተቻለ መጠን በሁሉም አካባቢ ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ሌላው እናቶች በወሊድ ጊዜ በጤና ተቋማቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ የማያስችላቸው ችግር የመጉዋጉዋዣ ሁኔታ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ስምንት መቶ የሚሆኑ ወረዳዎች ያሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ወረዳ ውስጥ አንዳንድ የአምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች እንዲኖሩ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው፡፡ የመንገድ ስራው በእርግጥ የጤና ሴክተሩ ስራ ባይሆንም ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ተቋማት እየተንቀሳቀሱ ያሉበት ስለሆነ በቅርቡ ህብረተሰቡ ወዳለበት በቀላሉ በመድረስ አገልግሎ ቱን ለመስጠት እና በ2015 የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ የታቀደውን ግብ ለመምታት ያስችላል ተብሎ ይታሰባል እንደ ዶ/ር ታደሰ ከተማ ማብራሪያ፡፡
የእናቶቹን ብቻ ሳይሆን የህጻናቱን ጤና ጭምር ለመጠበቅም የሚያስችል አሰራር መኖር እንዳለበት የታመነ በመሆኑ እናቶች ከወለዱ በበሁዋላ ለራሳቸውም ይሁን ለልጃቸው ተገቢውን ክትትል ለማድረግ ወደህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋቸዋል፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመቶ እርግዝናዎችውስጥ15 ያህሉ እክል የሚገጥማቸው ሲሆን 15 ከሚሆኑት እክሎች ውስጥ ብዙዎቹ የሚከሰቱት ከወሊድ በሁዋላ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከወሊድ በሁዋላ ክትትል የሚያደርጉት እናቶች ከመቶ ወደ 34 የሚያህሉት ናቸው፡፡ በእርግጥ ቀደም ሲል ከነበረው ቁጥር በመጠኑ የተሻሻለ በመሆኑ እንጂ 34 ሲባል ሙሉ በሙሉ ጥሩ ነው የሚባል አይደለም፡፡ የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር መቀነስ የምእተ አመቱ የልማት ግብ እቅድ ሲሆን ቀደም ሲል የነበረውን ቁጥሩን በ20015 ከመቶ ሺህ እናቶች ወደ 267 ዝቅ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህም አንጻር የድህረወሊድ አገልግሎትን ተደራሽነት በማሻሻል በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ከ34 ወደ 78 ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡
ዶ/ር ታደሰ ከተማ ከኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ በስተመጨረሻው እንደገለጹት የእናቶች ጤና አገልግሎት ሲባል ከጤና ተቋሙ ሰራተኞች ጋር ብቻ የተያያዘ ሳይሆን የሚመለከተው ሁሉ ሊያተኩርበት የሚገባው ነው፡፡ የመገናኛ ብዙሀን በየበኩላቸው የጤና ተቋማትን መጠቀም ለእናቶች የሚሰጠውን አገልግሎት በማጉላት ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በህብረተሰብ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች እንዲሁም የተለያዩ አካላት እናቶችን ወደ ህክምና ተቋማቱ በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠ ቃሚ እንዲሆኑ በመምከርና ሁኔታዎችን በማሻሻል በጋራ እንቅስቃሴ ቢደረግ የእናቶችን በእርግዝናና በወሊድ ጊዜ መታመም መሞት የመሳሰለውን አደጋ ለመቀነስ ስለሚያስችል ማንም ወደጎን ሊተወው የማይችለው የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ማስገንዘብ እወዳለሁ ብለዋል ዶ/ር ታደሰ ከተማ፡፡

Read 2969 times Last modified on Saturday, 12 November 2011 08:45