Saturday, 06 July 2013 11:41

“....የወር አበባ መዛባት ....”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ (ከኢሶግ)
Rate this item
(17 votes)

“....በአለማችን ሴት ልጆች የወር አበባ የሚጀምሩበት እድሜ ወደ 11 እና ከዚያም በታች ዝቅ በማለት ላይ ይገኛል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከ13-15 አመት እድሜ ባለው ጊዜ ይመዘገብ የነበረው የወር አበባ መምጫ ጊዜ በዚህ መልኩ የመቀነሱ ምስጢር የአኑዋኑዋርን ደረጃ ባማከለ መልኩ መሆኑን ጥናቶች ያስረዳሉ....”
ከላይ ያነበባችሁት ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያ የተናገሩት ነው፡፡ በዚህ እትም ለንባብ የምንለው በወር አበባ ምክንያት የሚፈጠር ሕመምንና ህመም አልባነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡
የወር አበባ ሴቶች በእድሜያቸው ከ11-13 አመት ጀምሮ እስከ 45-50 አመት ድረስ በየወሩ ከማህጸናቸው የሚፈሳቸው ደም ነው፡፡ ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ እንደገለጹት ሴቶች ከወር አበባ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሕመሞችን ለሐኪማቸው ይገልጻሉ፡፡ አንዳንዶች
ደሙ በትክክለኛው ስሌት መሰረት በየወሩ አይፈስም ፣
ወይንም ወቅቱን ሳይጠብቅ ይፈሳል፣
መጠኑ ትንሽ ነው ወይንም ይበዛል፣
ወቅቱን ሳይጠብቅ ተቋርጦአል...ወዘተ
ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪም አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ በሚመጣ ጊዜ ጭርሱንም ተንቀሳቅሶ ስራራን ለመስራራት የሚቸገሩበት ሁኔታም ያጋጥማል፡፡
የወር አበባ ሲመጣ የሰውነት ለውጥ ይታያል፡፡ እረፍት ማጣት ፣መቅበዝበዝ ፣በቀላሉ መናደድ፣ አልፎ አልፎ የሚሰማ የእራራስ ምታት ፣የአግር ማበጥ፣ ክብደት መጨመር፣ ጡት የማጋት የመሳ ሰሉት ይከሰታሉ፡፡ የተጠቀሱት ምክንያቶች የሚከሰቱት በተፈጥሮአዊ ሁኔታ በሆርሞን መለወወጥ ምክንያት ሲሆን ነገር ግን እንደችግር የሚቆጠሩ አይደሉም፡፡ ሕመም ነው አይደለም የሚለውን ለመለየት ግን የተጠቀሱት ምክንያቶች ድግግሞሽ ሁኔታውን ይወስነዋል፡፡ የወር አበባ ሲመጣ ሊታዩ የሚገባቸው ተፈጥሮአዊ የሰውነት ለውጦች በአካበቢ ለውጥ ሁኔታ፣ ከስነልቡና ጋር በተያያዘ ፣የስራራ ጫና፣የቤተሰብ ሁኔታ የመሳሰሉት መጠኑን ሊያሰፉት ወይንም ሊያባብሱት ስለማችሉ ሕመሙ ሐኪም ዘንድ መቅረብ ሊያስፈልገው ይችላል፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ በወር አበባ ምክንያት የሚፈጠር ሕመም ወይንም ስቃይ ተብሎ የሚገለጸው በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡
Primary Dysmenorrhea የሚባለው ሲሆን ይኼውም አንዲት ሴት ልጅ የወር አበባ ካየች ጊዜ ጀምሮ ለሁለት እና ሶስት አመታት ያህል ስቃይ ያለው ሕመም መሰማት ነው፡፡ የዚ ህም ምክንያት የማህጸን የውስጥ ግድግዳ አካባቢ ያለው ሆርሞን የወር አበባ በሚፈ ስበት ጊዜ ጥንካሬ ስለሚሰማው ሕመምን ያስከት ላል፡፡ ይህ ሁኔታ ረጅም አመታት ሳይቆይ ሕመሙ ሊቀረፍ የሚአወለወ ሆነወ ሁኔታው ሳይቋረጥ ለብዙ አመታት ከቀጠለ ግን በመድሀኒት እንዲታገስ ይደረጋል፡፡
በማህጸን ወይንም እንቁላል ማምረቻው አካባቢ ባለ እጢ ምክንያት ሕመም ካለ Secondary Dysmenorrhea ይባላል፡፡ ይህም ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚሰማ ሕመም ነው፡፡ ስለዚህም ሴትየዋ የወር አበባ ሲመጣባት የሚሰማትን ሕመም ለማከም ሕመሙን ያመጣውን ነገር ማስወገድ ተገቢ ይሆናል፡፡
እጢ ከሆነ እጢውን ማውጣት፣
የወር አበባው የሚፈስበት መንገድ መዘጋት ወይንም መጥበብ ከሆነ መፍትሔ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የወር አበባ ሲመጣ ሕመም የሚሰማቸው ሴቶች ባል ሲያገቡ ወይንም ልጅ ሲወልዱ ሕመሙ ይወገድላቸዋል የሚለው አባባል ተለምዶአዊ እንጂ ሳይንሳዊ አይደለም፡፡ ዶ/ታደሰ እንደሚገልጹት ሕመሙ ምክንያት ያለው ወይንም Secondary Dysmenorrhea ከሆነ (...የማህጸን በር ወይንም የማህጸን አንገት ተዘግቶ ከሆነ...) ምክንያቱን ለማስወገድ አስፈላጊውን ሕክምና ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡
እንደ ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት ማብራራሪያ የወር አበባ ጊዜውን ጠብቆ የሚመጣው በእድሜያቸው ከ20-40 አመት ድረስ ባሉ ሴቶች ነው፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያው ወቅት የሆርሞን መስተካከልንና የሰውነት መልመድን ስለሚፈልግ በሶስት ወር ወይንም ከዚያ በታች እና በላይ በተዛባ ሁኔታ ሊታይ ይችላል፡፡ እንደዚሁም (T@•þ´)የወር አበባ ሊቋረጥ በሚዘጋጅበት ጊዜም እንደዚሁ ወቅቱን ሳይጠብቅ በተዛባ ሁኔታ ይፈሳል፡፡ በሁለቱ ጫፍ ያለው የወር አበባ አፈሳሰስ ባህርይ የሆርሞኖችን መዛባት የሚያመለከት ነው፡፡ ነገር ግን በመሀከል ላይ ባለው እድሜ የወር አበባ በየወሩ ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ ከሆነ ከአካላዊ ችግር ከአካባቢ ጋር ...መኖሪያን የመለወጥ ...ወዘተ ሲያጋጥም አንጎልና እንቁላልን የሚያመርተው ክፍል በሚያደርጉት ግንኙነት ወይንም መረበሽ ምክንያት የሚከሰት ችግር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕመሙ ሆርሞንን ከሚያመነጨው ክፍል እና ከማህጸን ግድግዳ ጋር በተገናኘ ከሆነ የህመም ምክንያቱ ተፈልጎ መገኘትና መታከም ይገባዋል፡፡
የተለያዩ መረጃዎች እንደT>ÁSK¡~ƒ የወር አበባ ወቅቱን አለመጠበቅ ወይንም በተዛባ ሁኔታ የሚፈስ ከሆነ ሴትየዋ፡-
ሰውነትዋ ከልክ በላይ የሆነ ውፍረት አጋጥሞታል፣
የተዛባ የምግብ ስርአትን እየተከተለች ነው፣
የአእምሮ ጭንቀት ይዞአታል፣
ከልክ በላይ የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነች፣
በተለያዩ ምክንያቶች ሕመም ገጥሞአታል፣
ረዥም ጉዞ አድርጋለች ...ወዘተ
የመሳሰሉት የወር አበባ አፈሳሰሱን ሊያዛቡ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የወር አበባን አፈሳሰስን ሊቀንሱ ወይንም ሊጨምሩ ከሚችሉ ምክንያቶች
እንደ እርግዝና መከላከያ የመሳሰሉ መድሀኒቶች፣
የሆርሞን ችግር ፣
ሱስ አስያዥ እጾችን መጠቀም፣
የአከርካሪ ወይንም የጀርባ አጥንት የደም ጋን ችግር፣
ጡት ማጥባት ...ወዘተ የወር አበባ አፈሳስን በትክክለኛው መንገድ እንዳይሆን ከሚያደርጉ መካከል ናቸው፡፡
ጡት ማጥባት እንደችግር የሚወሰድ ሳይሆን እንዲያውም በትክክል ልጆቻቸውን የሚያጠቡ እናቶች እርግዝናን እንደT>ŸLŸML†¨< መረጃዎች ÃÖlTK<፡፡›”Ç=ƒ ሴት ጡት በማጥባት ምናልባት ከ60-65 በመቶ ወሊድን መከላከል ትችላለች፡፡ ማጥባት ሲባልም ሙሉ ጊዜዋን በማጥባት ላይ ያለች ሴት እና አልፎ አልፎ የምታጠባ ሴት እርግዝናውን የመከላከል አቅማቸው የተለያየ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እቤት ውስጥ የሚውሉ እናቶች ብዙ ጊዜ ስለሚ ያጠቡ ያልተፈለገ እርግዝናን የመከላከል አቅማቸውም ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አልፎ አልፎ የሚያጠቡ እናቶች ማጥባቱ ወሊድን የመከላከሉ አቅም በዚያኑ መጠን ዝቅ ይላል፡፡
ዶ/ር ታደሰ እንደሚገልጹት የወር አበባ መምጫ እድሜ በእጅጉ እየቀነሰ በመሄዱ ዛሬ ዛሬ ለሴት ልጆች ትምህርቱ መሰጠት ያለበት እድሜያቸው አስር አመት ከመድረሱ አስቀድሞ መሆን አለበት ፡፡ በአለማችን የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ እንደሚታየው ባደጉት አገሮች በተመቻቸ ሁኔታ የሚያድጉ ልጆች በእድሜያቸው ገና አስር አመት ሳይደርሱ የወር አበባ የሚያዩበት አጋ ጣሚ ሲኖር ኑሮው እጅግ ዝቅተኛ በሆነበት አካባቢ ግን እስከ አስራራ አምስት አመትም ዘግይቶ ሊታይ ሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡ ለማንኛውም ግን ማንኛውም ወላጅ ፣ትምህርት ቤቶች ወይንም የሚመለከተው አካል ለሴት ሕጻናቱ እድሜያቸው ወደ አስር አመት ሲደርስ ትምህርት መስጠት አለበት፡፡ ትምህርቱም ማተኮር ያለበት ተፈጥሮአዊውን ሁኔታ በመግለጽ ሴት ልጅ ይህንን ተፈጥሮአዊ ክስተት በጸጋ ተቀብላ ማስተናገድ እንደሚገባት እና በምን መልክ የሚለውን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን ያካተተ መሆን ይገባዋል፡፡
የወር አበባ በእራራሱ ምንም አይነት የጤና እክልን የማያስከትል ሲሆን እንዲያውም በሰላም ጊዜውን ጠብቆ ከፈሰሰና ካበቃ የጤንነት ምልክት መሆኑን ሳይንሱ ያስረዳል፡፡ በሌላ በኩል ግን የወር አበባ በሚፈስበት ጊዜ ለጥንቃቄ ተብለው የሚለበሱ ልብሶች የጤንነት ሁኔታን የማያዛቡ መሆን እንደT>Ñv†¨< ሳይንሱ ያስረዳል፡፡ ንጽህናቸው የተጠበቁ የውስጥ ሱሪዎች አንዲሁም ከሱሪዎቹ ስር የሚደረጉ ሞዴስ ወይንም እንደ ሞዴስ የሚያገለግሉ ልብሶች ንጽህናቸው የተጠበቀ መሆን ይገባዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ እንዳስረዱት የወር አበባ በሚፈስበት ጊዜ ሊታገድ አይገባውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ከሚውሉበት የስራራ ሁኔታና ከለበሱት ልብስ እንዲሁም ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ አይነት በመነሳት ደም ሳይፈስ እንዲውል ለማድረግ አላስፈላጊ እርምጃ ይወስዳሉ፡፡ ትክክለኛ አጠቃቀም የሚሆነው ግን የሚ ፈሰው ደም ሳይታወክ እንዲፈስ ማድረግና በተወሰነ ጊዜ የሚÖkS<uƒ” መቀበያ በማስወገድ ወይንም በመለወጥ ንጽህና ሳይዛባ ማስተናገድ ነው፡፡

Read 17622 times