Saturday, 20 July 2013 11:54

‹‹Tower in the Sky›› እና ‹‹ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ››

Written by  አንተነህ ተስፋዬ ለማ
Rate this item
(0 votes)

አዳም ረታ እና ሕይወት ተፈራ መንገዳቸው (ታሪካቸው) ገጥሞ (ተገጣጥሞ) አየዋለሁ፡፡ አንዱ ላንዱ ምስክር የቆሙ ይመስል . . . . በዘመን ባሕር ላይ የቁዘማ ታንኳቸውን ወደኋላ ይቀዝፋሉ፡፡ ሁለቱ ደራሲያን የዚያን ዘመን እና የዚያን ትውልድ ግብር እና ገቢር በየፊናቸው ከትበውታል፡፡ ሕይወት Tower in the Sky ብላ ጻፈች፡፡ አዳም “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ”ን ጻፈ፡፡ በነዚህ ሁለት ድርሳናት ውስጥ አጮልቄ አየሁ፡፡ ተመሳስሎው ይገርማል፡፡ ያንን ዘመን ከፖለቲካው ምሽግ ሳይሆን ከሰው (ከተራ ሰው) አንጻር ተርከውታል፡፡ ‹‹ተራ›› የሚለው ቃል አሉታዊ ትርጓሜውን እርሱት፡፡ Tower in the Sky ሲጀምር ይህች ውብ ጥቅስ አለች፤ “To speak of this is painful for me: to keep silence is no less pain. On every side is suffering” ይህ የሕይወት የኑዛዜ መክፈቻ ይመስለኛል፡፡

በ”ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” መጨረሻ ላይ ደግሞ አለሙ እንዲህ ይላል፤ ‹‹ፊት ለፊቴ ገና የምሰርዘው ጥቁር ትዝታ አለ፡፡›› ልብ በሉ፤ ጥቁር ትዝታውን የሚሰርዘው በኑዛዜው ነው፤ ‹‹ከመናዘዝ የበለጠ ላጲስ የት አለ?›› እንዲል፡፡ ‹‹ያቺ¸ ቢጫ ነቁጥ የየራሱ ኑዛዜ ናት፡፡›› ሁለት ኑዛዜዎች (ኑዛዜያት . . . ?) ዘመነ ንጽህና አዳም (በአለሙ በኩል) እና ሕይወት ኑዛዜያቸውን የሚከትቡት ዕንባቸውን እያጠቀሱ ይመስለኛል፡፡ ለከሸፈ ሕልማቸው፣ ለሞተ ፍቅራቸው፣ ለተበረዘ ንጽህናቸው፡፡ የሕይወት መጽሀፍ የመጀመርያ ክፍል፣ በአዳም አንደኛዋ ጎዳና ይመሰላል፡፡ ባጭሩ ሁሉ ነገር ንጹህ ነበር፡፡ በቃ! (የሚናፈቅ ንጽህና) (የጠፋ ንጽህና?) እየሄድን ነው . . . . ዘመነ ንቃት (‹‹ነገን ፈርተህ አትተኛ››) ንቃቱ ሲጀመር ቀላል ነበር፡፡ ከርዕዮተ ዓለም ይልቅ የማርክሲስት ቃላትን ማንቸልቸል የ‹‹ንቃት›› እና የ‹‹ዕድገት›› ምልክት ነበርና... ከዚያ ያለፈ ዓለም፣ ከዚያ ያለፈ ዓላማም አልነበረም፡፡ ነገሮች መለዋወጥ ሲጀምሩ (የአብዮት ነፋስ ሲነፍስ ይሉታል) ወደ ፖለቲካው ጠጋ ጠጋ ማለት ይጀመራል፡፡ ሕይወት በጌታቸው ትማረካለች (ትመለመላለች) አለሙ ደግሞ በእነገብረወልድ፤ ‹‹ገብረወልድን የተዋወቅሁት እዚህ ነው፡፡ ቅዱስ ከተባለ አራዳ ጋር የተዋወቅሁት እዚህ ነው፡፡ መንግስት ገልባጭ ለመሆን የተመለመልኩት እንትና ካፌ ቤት ገብረወልድ የገዛልኝን ቺዝ በርገር በቡና በወተት እያማግሁ ነው፡፡›› ይላል አዳም፡፡

ሕይወትም እንዲሁ ነች፤ ሐረር ምግብ ቤት! እና... የጓዶች ቤት... የፖለቲካን ሀሁ እንደዋዛ የቀሰመችው፡፡ የማርክሲስት ቃላትን እንደ ዋዛ ከማንቸልቸል፤ ፖለቲካን ወደ ማብሰልሰል ከፍ ሲባል፤ ‹‹ቀልዱ ቀልድ አልነበረም›› የፖለቲካው ትኩሳት በማንነት ውስጥ መብላላት ሲጀምር ወሰን አልባ ሕልም ይታለማል፡፡ ጽንፍ አልባ ዕቅድ ይታቀዳል፡፡ አዳም አንድ ጎዳናው ላይ ሆኖ እንዲህ ይላል፤ ‹‹ዓይኖቻችንን አድማስ ስፌት ላይ ተክለን ትዕንግርት ባልገባው የልጅነት ልባችን ትዕንግርት ልንሰራ የፈለግነው እዚህ ነው፡፡›› አድማስ ስፌት ላይ አይኖቻቸውን ተክለው ሊሰሩት ያሰቡትን ትዕንግርት ሕይወት ባጭሩ እንዲህ ትለዋለች፤ ‹‹Tower in the Sky! ›› ዘመነ ለውጥ ለመኖር ምክኒያት ያስፈልጋል፡፡ ለመኖር ሕልም ያስፈልጋል፡፡ የዚያ ዘመን ሕልም ለውጥ ነበር፡፡ ይህ ሕልም መንገድ ይቀይራል፡፡

ሕይወት ይቀይራል፡፡ ትምህርትም ትረሳለች፡፡ (በአዳም ቋንቋ ሳይንስ ታመልጣለች፡፡) “Perusing my education seemed selfish and inconsequential in light of the plight of the masses that needed to be lifted out of poverty. What was education when the people needed me?” - Tower in the sky ‹‹ሕዝብ እየተጨቆነ መማር ምን ይሰራል! የጎጃም፣ የባሌ፣ የኤርትራ ገበሬዎችና የአምቦ ተማሪዎች እየተጨፈጨፉ... ጎጃም ያለቀ፣ ባሌ የተደመሰሰ፣ አምቦ የተቃጠለች መሰለኝ፡፡›› - ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፡፡ እንቀጥል፤ ባቡሩ እየተጓዘ ነው፤ የፖለቲካው ስሜትና ዕውቀት፣ አቋም ይወልዳል፤ ያውም ጠንካራ አቋም፡፡ የለውጥ አማራጭን የሚቀይስ ሕቡዕ አቋም፡፡

ይህ አቋም ባደባባይ ሲገለጥ እንዲህ ነበር፡፡ “The entire city was submerged in a sea of red with banners hoisted everywhere and walls ornamented with slogans. The graffiti and banners were as much the delight of members as they were Derg’s nightmare.” Tower in the sky ‹‹አጥሮች ላይ፣ ግንቦች ላይ፣ ጣውላዎች ላይ፣ ቆርቆሮዎች ላይ በሚንቦጎቦግ ደማቄ ቀለም፤ ‹‹ሕዝባዊ መንግስት በአስቸኳይ!›› ‹‹ኢህአፓ ያቸንፋል›› እየተባለ የሚጻፈውን አንብቤ በቡድኔ ስፋት የኮራሁት እዚህ ነው፡፡ ከሚሊዮን አመታት በፊት በሴኖዞይ ክፍለ ዘመን ከተፈጠረው የሀገሬ አፈር ገነው የሚያበሩ መፈክሮች ያየሁት እዚህ ነው፡፡›› ይወስዳል መንገድያ መጣል መንገድ፡፡ እዚህ ጋ ማን ምን እንደሆነ ታውቋል፡፡ ጠላትነት እዚህ ተጠንስሷል፡፡ ጎራው ተለይቷል፡፡ ‹‹መንገዳችን ለየቅል ነው›› ያሉ ሁሉ በየፊናቸው ይመሽጋሉ፡፡ ልጅነት፣ አብሮነት እና ንጹህነት በፖለቲካ ይሰረዛል፤ የልጅነት ፍቅርም እንዲሁ፡፡ (ለበጎም ሆነ ለክፉ) ‹‹አብሮ ማደግን ፉርሽ አደረግናት፡፡ በልጅነቴ በሰበሰብኩት ዕውቀትና መታመን ገበና በማወቄ ሳራን አስገድያለሁ፣ ካሱን አሰቅያለሁ... አብሮ አደጋችንን የሚያስከነዳ አዲስ የሩቅ ጓደኛ የምንተዋወቀው እዚህ ነው፡፡›› - ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ “To my surprise, it was the friends I grew up with that I had difficulty understanding any longer. I could feel an abyss separating us. . . . It was my comrades for whom my heart leapt every time” – Tower in the sky ይሄኔ መራሩ ዕውነት ማቆጥቆጥ ይጀምራል፡፡ ንጽህናው ሲበረዝ... ‹መቸሻቸሽ› ይቀጥላል፡፡

ደም! መለየት፣ ሞት... የሚወዱትን ማጣት ጌታቸው አልፏል፣ ደበበ ሄዷል፣ መሪማ ‹አርጋለች› ባመኑት ሰው መሞት የዘመኑ ቀለም ነበር፡፡ ‹‹ለምን ሞተ ቢሉ...›› “What did he die for? For trying to save lives? Is all this in the name of the revolution... in the name of the people? Are we justified to do away with peoples’ lives in the name of the revolution?” – Tower in the Sky ‹‹መሞት ሳያስፈልገኝ ሙት አሉኝ፡፡ መሬቱን የወሰደ ገበሬ ቀኑ አልፎለት ሳላይ ከጀርባዬ እየነዱ አቻኮሉኝ፡፡ በትግል እንጂ በአዋጅ መሬት አይሰጥም ብለው፡፡ ሞቴን ወደ ሰበበኝነት ፈጠሩት፡፡›› - ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፡፡›› ጥያቄው ከባድ ነው፡፡ ያማል፡፡ ልብ ያደማል፡፡ ፍቅር፣ ትግል፣ ሰው! ሰው፣ ፍቅር፣ ትግል! ትግል፣ ፍቅር፣ ሰው! . . . . . . ውዥንብር! ዘመነ አስተውሎት ሀዘን በወለደው ስሜት ነገሩሁሉ . . . . ግራ ቀኙ ሲታይ . . . . አስተውሎት (Realization) ይከተላል፡፡ አዳም Czaykowski Bodgan የተባለ ጸሀፊ “Put your hands in the flame if you are a man” ያለው ላይ ተንተርሶ እንዲህ ይላል፤ ‹‹ወንድ ስለሆንኩ እጆቼን ነበልባል ውስጥ ጨመርኩ፡፡

ታዲያ ብርሀን ሳይሆን አንጀቴ ውስጥ ጠማማ ቁስል ቀረ፡፡›› ‹‹But, like Icarus, who flew too close to the sun and got the wings of his chariot burned, it came too close to the “Sun” for its own good too.” Tower in the Sky ግዜ ያልፋል፡፡ ነገሮች ተቀያይረው . . . የሞት ዕጣ ለሁሉ እየተዳረሰ . . . እሳቱ የበላቸው እያለፉ . . . የተረፉትም . . . ስደት!! ሕይወት እንዲህ ትላለች፤ “ . . . Others flooded European and North American cities. Wherever they lived, many of them became eternal strangers to the world and to themselves. Devoid of dreams and ideals, they lost meaning in the present or the future” ‹‹የለንደን መንገዶች አስፋልትና ሲሚንቶ ናቸው፡፡ አላውቃቸውም አያውቁኝም፡፡ የትኛውንም ቦርቡሬ ገበጣ መጫወት አልችልም፡፡ ሱፐርማርኬቱን ከላይ እስከ ታች በላስቲክና በክርታስ የተጠረዘ ምግብ ሞልቶታል... ሁሉ ነገር አዲስ ነው፡፡ እዚህ ለተወለዱትም ሁሉነገር በየቀኑ እንግዳ ነው... አዲስ ነገር አልፈራም ግንትር ጉሙን ፍለጋ እማስናለሁ፡፡›› ከዚህ ሁሉ የተረፈው ማንነት በእስር፣ በዕድሜ ሲሞረድ .... ትላንት ቁልጭ ብላ ስትታይ... (አለሙ በጠባብ ቤት ውስጥ... ሕይወት በጠባብ እስር ቤት) ራስን መመርመር ይከተላል፡፡

‹‹በዚህ መንገድ አልፌ ነበር? በዚህ መንገድ መጥቼ ነበር? እላለሁ፡፡ ልላቸውም እፈልጋለሁ፡፡ እንደምትወዱኝ ሁሉ ከልጅነቴ አትሟጨጩ፣ ከልጅነቴ ምን አላችሁ? ልጅነቴን ብትኖሩብኝም፣ ማስታወሴና ትውስታዬን መተርጎሜ ግን ዛሬ የኔ ናት›› ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፡፡ ‹‹Slowly, I felt a new person surging in me. I gained confidence in the knowledge that I can define and redefine myself. I could determine who I wanted to be and where I wanted to go.” – Tower in the Sky ይህ ምርምር ከ‹‹እኛ›› ውስጥ ‹‹እኔ›› የሚባል አዲስ ማንነት ይፈጥራል፡፡ “Why do people imitate others? Why do they follow them blindly? . . . Will I ever belong to a group again” – Tower in the Sky አዳምም በተዋሳቸው ስንኞች፤ ‹‹የወል ልቦናችን የጋራ ልባችን አደረገን ባዶ የግሉን ልቦና የግሉን ልብ ወስዶ፡፡›› ይላል፡፡ ዘመነ ንስሀ ፍጻሜው ሲቃረብ “. . . I always wanted to emulate: respect for human life, tolerance and peaceful resolution of conflict” – Tower in the Sky “ይሄ ጎዳና የይቅርታ ነው፡፡ ሁለት እግሮቼን አገጣጥሜ የምቆምባት ሰንበሌጥ መንገድ አለች፡፡ ቦታዬ አለም ይመስለኝ ነበር፡፡ ቦታዬ ግን ይህቺ ናት፡፡›› - ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ ‹‹ሕይወት›› - ‹‹ሰው›› - ‹‹አዳም›› ዕውነት ዕውነት ነው፡፡

Read 3005 times Last modified on Saturday, 20 July 2013 12:06