Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 19 November 2011 14:36

ጄሚ ፎክስና ጆኒ ዲፕ ማይክልን ለመተወን ታጩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በማይክል ጃክሰን ውስን የህይወት ምእራፎች ላይ በሚያተኩር የፊልም ስራ ፕሮጀክት የሆሊውድ ባለሙያዎች እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ዘጋርድያን ዘገበ፡፡ በታላቁ የፖፕ ንጉስ የህይወት ታሪክ ላይ ፊልም የመስራቱ ሃሳብ ባለፉት 2 ዓመታት በሆሊውድ ሲመከርበት ቆይቷል፡፡ በፊልም ስራው ሞንቴሲቶ ፒከቸር የተባለ የፊልም ኩባንያ ከማይክል ጃክሰን ወራሽ ቤተሰብ ጋር መወያየቱን የገለጸው ዘገባው ይፋዊ ስምምነት አልተደረገም ብሏል፡፡ የማይክል ጃክሰንን ገፀባህርይ በሁለት ምእራፎች ሊተውኑ የታጩት ጥቁር አሜሪካዊው ጄሚ ፎክስና ጆኒ ዲፕ መሆናቸው እንደሚጠበቅ ዘገባው አመልክቷል፡፡ በሆሊውድ ከፍተኛው ተከፋይ የሆነውና በፓይሬትስ ኦፍ ካረቢያን ፊልሞች የታወቀው ጆኒ ዲፕ ማይክል ጃክሰንን በፊልም ለመተወን መቼም አስቦ እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡

ከ2 ዓመት በፊት በድንገተኛ ሁኔታ ህይወቱ ላለፈው ማይክል ጃክሰን አሟሟት የግል ሃኪሙ ዶር ሙራይ ቸልተኛ ህክምና ሰጥቷል በሚል የፍርድ ውሳኔ የተላለፈበት ከ2 ሳምንት በፊት ነው ሰሞኑን የቅጣት ውሳኔው ይበየናል፡፡ በዶር ሙራይ ላይ የ4 ዓመት ፅኑ እስርና የህክምና ፈቃዱን የመነጠቅ ውሳኔ እንደሚተላለፍ የገመተው ቢቢሲ ደጋፊዎቹ በፍርድ ውሳኔው በቂነት አለመስማማታቸውን ጠቅሷል፡፡ የማይክል ጃክሰንን የፍርድ ሂደት ለ6 ሳምንት ሲቆይ በ22 ቀናት በተሰሙ ችሎቶች 49 ምስክሮች ቃላቸውን እንደሰጡና 300 ኤክዚብት ማስረጃዎች ቀርበዋል፡፡ ማይክል ጃክሰን ለግል ሃኪሙ ዶር ሙራይ በወር 150ሺ ዶላር ደሞዝ ይከፍል ነበር፡፡

 

Read 2369 times Last modified on Saturday, 19 November 2011 14:38

Latest from