Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:39

ብራድ ፒት በ50 ዓመቱ ትወና ያቆማል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ47 ዓመቱ ብራድ ፒት በ50 ዓመቱ ትወና ለማቆም ማቀዱን ለአውስትራሊያው የቲቪ ሾው 60 ሚኒትስ ተናገረ፡፡ከትወና ይልቅ በፊልም ኢንዱስትሪው በፕሮድዊሰርነት መስራት ፍላጎት አለኝ ያለው ብራድ ፒት ከአንጀሊና ጋር በመሰረተው ቤተሰብ ተጨማሪ ልጆች እንዲኖሩ ፍላጎት እንዳለውምተናግሯል፡፡ “መኒ ቦል” በተባለው ፊልሙ በቤዝቦል ስፖርት የሚሰራ ቢሊ ቤን የተባለ ገፀባህርይን በመተወን ድንቅ ብቃት ያሳየው ብራድ ፒትለኦስካርሽልማትከሚጠበቁ ተዋናዮች ተርታ ተሰልፏል፡በይዘቱ ስፖርታዊ ድራማ የሆነው “መኒ ቦል” በ50 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራ ሲሆን ባለፉት ሁለት ወራት በዓለም ዙርያ ገቢው 80 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡

Read 3218 times