Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:41

“ነፃነት” እና “የሚሼል ኮከቦች” ይመረቃሉ “ከፀሐይ በታች” ተመረቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ግጥም በማለዳ” በተሰኘ ወርሃዊ የኪነጥበብ ዝግጅቱ “ነፃነት” የተሰኘው የተናኘ ከበደ የግጥም መፅሐፍ እንደሚያስመርቅ የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር አስታወቀ፡፡ ነገ ጧት በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ትንሿ አዳራሽ የሚቀርበውን ዝግጅት የኪነጥበባት አፍቃሪዎች እንዲታደሙ ማህበሩ ጋብዟል፡፡
በተያያዘ ዜና ማህበሩ “ጥበብ እንቃመስ” በተሰኘ ሌላ ወርሃዊ የኪነጥበብ ዝግጅቱ እንግሊዝ ሀገር ኗሪ የሆነችው አባሉ ፀጋ ዮሐንስ የፃፈችው “የሚሼል ኮከቦች” ረዥም ልቦለድ መፅሐፍ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ ረቡዕ ከቀኑ 10፡30 በሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል ፑሽኪን አዳራሽ የሚቀርበውን ይሄንን ዝግጅትም የኪነጥበባት አፍቃሪዎች እንዲከታተሉ የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር ጋብዟል፡፡ በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር አባል የሆኑት አቶ ሰለሞን ሞገስ “ከፀሀይ በታች” የተሰኘ የግጥም መፅሐፋቸውን ትናንት አስመረቁ፡፡ በሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል ፑሽኪን አዳራሽ የተመረቀው መፅሐፍ በጥቅምት ወር ገበያ ላይ የዋለ ሲሆን ዋጋውም 15 ብር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 3051 times