Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:46

አርቲስቶች ለዳያሊሲስ ታካሚዋ እርዳታ እያሰባሰቡ ነው ለአካል ንቅለ-ተከላ ሕግ አልወጣለትም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ”ሰው ለሰው” ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እየተሳተፉ ያሉና ሌሎች አርቲስቶች ለኩላሊት ሕመምተኛዋ የ25 ዓመት ወጣት ዳያሊሲስ መታከሚያ እርዳታ እያሰባሰቡ ነው፡፡ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል ምርጥ የወንድ ተዋናይ የሆነው አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ 10ሺህ ብር የረዳ ሲሆን፤ ሌሎች አርቲስቶች የዚህኑ ያህል ገንዘብ አዋጥተዋል፡፡

ወጣቷ ውጭ ሀገር ለመታከም ከ700 ሺህ ብር በላይ ተጠይቃ ባለማግኘቷ ሕይወቷ አደጋ ላይ መውደቁን ጓደኞቿ ገልፀውልናል፡፡ ከሕክምናውን ባሻገር የኩላሊት ንቅለተከላ በሐገር ውስጥ በአንፃራዊ ትንሽ ወጪ ማካሄድ የሚያስችል ማሽን እና ተዛማጅ ቴክኖሎጂ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል መኖሩን የሆስፒታሉ መስራችና ሕክምና ዳይሬክተር ዶክተር አከዛ ጣዕመ ገልፀው ሕጉ ቢኖር ንቅለተከላ (transplant) ለመሥራት ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀልናል፡፡ ይህ ቢታወቅም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሕግ ስላላወጣለት ሥራ አለመጀመሩን ማወቅ ተችሏል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቆ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመላክ ላይ መሆኑን የሚኒስቴሩ የሕግ ጉዳዮች ደይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢሳያሳይ ጌታሁን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

 

Read 2027 times Last modified on Saturday, 19 November 2011 14:50