Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:48

ለአለቃ ገብረሃና ቋሚ መታሰቢያ እንዲሰራ ተጠየቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በቀልድ አዋቂነታቸው የሚታወቁት አለቃ ገብረሃና ቋሚ መታሰቢያ እንዲደረግላቸው ተጠየቀ፡፡
ይህ የተጠየቀው በሚዩዚክ ሜይ ዴይ የመፃሕፍት ንባብ እና የውይይት ክለብ የአለቃ ገብረሃናን ሕልውና አስመልክቶ የወግ ፀሐፊ (Essay Writer) ዳንኤል ክብረት በመሩት ውይይት ነው፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ የሥነፅሑፍ ቤተሰቦች አለቃ ገብረሀና አስተዋፅኦአቸው ብዙ በመሆኑ ቋሚ መታሰቢያ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡ ከመታሰቢያዎቹ አንዱ የሆነውን ዓመታዊ የቀልድ ውድድር በስማቸው ማዘጋጀት እንደሚቻል የገለፁት ተሰብሳቢዎች፤ ይህንኑ ከልደታቸው ወይም ከሕልፈታቸው ቀን ጋር ማጣጣም እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ የውጭ ሀገር ነገስታት ጎዳና እና አደባባይ ሌላም በስማቸው ሲሰየም ከዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ እስከ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመን ያገለገሉት አለቃ ገብረሃና ግን ምንም መታሰቢያ ያልተሰየመላቸው መሆኗ እንዳስቆጫቸው በውይይቱ አስተያየት የሰጡ ተሰብሳቢዎች ተናግረዋል፡፡

Read 2530 times