Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:50

“የፊት አውራሪ አመዴ ለማ መፅሃፍ” ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከሁለት ዓመት በፊት ሕይወታቸው ያለፈው አንጋፋው የፓርላማ ተመራጭ ፊት አውራሪ ዓመዴ ለማ ራሳቸው ያዘጋጁት “የሕይወት ታሪኬ” መጽሐፍ ሕዳር 16 ቀን 2004 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዘመን የደሴ ከተማን በመወከል የፓርላማ አባል የነበሩት ፊታውራሪ ዓመዴ ሥርዓቱን በመሞገታቸው፣ ሮም የነበረው የአክሱም ሃውልት እንዲመለስ ከሌሎች ኢትዮትያውያን ልሂቃን ጋር ጥረት በማድረጋቸውና የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ፌደሬሽንን መስርተው በፕሬዚዳንትነት በማገልገላቸው ይታወቃሉ፡፡ 320 ገፆች ያሉት ”የሕይወት ታሪኬ” መፅሐፍ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ገበያ ላይ የሚውል ሲሆን፤ በምርቃቱ እለት ፊታወራሪን የተመለከተ መጠነኛ አውደርእይ እንደሚኖር መፅሐፉን ያሳተሙት ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል፡ ወደፊት በእንግሊዝኛ የሚተረጎመው የዚህ መፅሐፍ ሽያጭ ከአምስት አንዱ ለአብያተ መፃሕፍት ማጠናከርያ እንደሚለገሥም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2496 times Last modified on Saturday, 19 November 2011 14:52