Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:50

“ደጀኔ ጥላሁን ፕሮሞሽን” ሥራ ጀመረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን ያቋቋመው “ደጀኔ ጥላሁን ፕሮሞሽን” ሰሞኑን ሥራ ጀመረ፡፡ ከመስከረም 1976 እስከ መስከረም 2003 ዓ.ም ለ26 ዓመታት በሬዲዮ ጣቢያው በመዝናኛ ዝግጅቶች ዋና አዘጋጅነት የሚታወቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን በ”እሁድ ጠዋት” ፕሮግራም፣ በ”ከመፃህፍት ዓለም” እና “የኪነ ጥበባት ምሽት” ዋና አዘጋጅነቱና ተራኪነቱም የሚታወቅ ሲሆን አሁን በሬዲዮ ኢትዮጵያ እየተተረከ ያለው የዮሐንስ ገብረፃድቅ ትርጉም በሆነው የቪክቶር ሁዩጐ መፅሐፍ “ምንዱባን”ን ከአርቲስት ሐረገወይን አሰፋ ጋር ከዓመታት በፊት ተርከውት የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በመስከረም 2004 ዓ.ም ፈቃድ የተሰጠው “ደጀኔ ጥላሁን ፕሮሞሽን” ድራማ፣ ማስታወቂያ እና ዶክመንታሪ ፊልሞችን መሥራት፣ በሕዝብ ግንኙነት የማማከር አገልግሎት መስጠት፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ዝግጅቶችን የማማከር እንዲሁም ሌሎች ኪነጥበባዊ ዝግጅቶችን የማዘጋጀት ሥራዎች እንደሚሰራም ማወቅ ተችሏል፡፡

Read 4650 times